አዲስ አበባ ፡- በሀገሪቱ በኮረና በሽታ ሳቢያ ሊያጋጥም የሚችለውን አደጋ ለማስቀረት ህብረተሰቡ ከምንም በላይ ሊተባበርና ራሱን ለዲስፕሊን ሊያስገዛ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት እንደገለጹት፤እስከ አሁን ባለው ልምድ የኮረና ቫይረስን በተቻለ መጠን መቀነስና አደጋው እንዳይከፋ ማድረግ የቻሉት ሀገሮች በትብብርና በዲስፕሊን መስራት የቻሉት ናቸው፡፡
የኮረና በሽታ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ መከላከል የሚቻለው ርቀትንና ንጽህናን በመጠበቅ
መሆኑን ጠቅሰው፣ ሁሉም ሰው በተቻለ መጠን ከንክኪ ራሱን ማራቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ህብረተሰቡ በሙሉ ይህን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በመተግበር ኢትዮጵያን ከሚገጥማት አደጋ ለመከላከል ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ኮረና አደገኛ ወረርሽኝ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡በዓለም ከ600ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ከ30 ሺ የማያንሱ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡አሁንም ብዙ ቦታ ጭንቀት፣ ስጋትና ፍራቻ ይስተዋላል፤ይህን ጭንቀት እና ፍራቻ ገንዘብ እና እውቀት ሊመክቱት አልቻሉም፡፡ ሀያል መባል ወይም ብዙ ትንሽ መባል ሊያቆመው አልቻለም፡፡
በዲስፕሊን የሚመራ ማህበረሰብ ያላቸውና በመረጃ
ፍሰት ህዝቡ የየእለት ሁኔታዎችን እንዲያውቅ በማድረግ ራሱን፣ ማህበረሰቡንና ሀገሩን እንዲጠብቅ ያደረጉ ሀገሮች በከፍተኛ ደረጃ ሊደርስባቸው ከሚችል አደጋ ራሳቸውን እና ሀገራቸውን መታደግ መቻላቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
በኛ ሁኔታ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እስከ ትናንት ጠዋት ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በዚህ በሽታ ስለመያዝ አለመያዛቸውን ለማወቅ ከተመረመሩ ከ800 በላይ ሰዎች ውስጥ 23 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መታወቁንም አስታውሰዋል፡፡ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ሁለቱ ማገገማቸውንና የሞተ እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
ከንክኪ በመራራቅና መመሪያ በመቀበል በኩል በከተሞች እየታየ ያለው ሁኔታ አሁንም በሚያረካ ደረጃ ላይ እንደማይገኝ አመልክተው፣ብዙዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሽታው በከፋ ሁኔታ ከተስፋፋ አሁን ባለው ዲስፕሊን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ሁላችሁም እንደምታውቁት የተሻለ ሀብት፣የተሻለ ሆስፒታል እና አቅም ያላቸው ሀገራትም አደጋውን በቀላሉ መከላከል አልቻሉም ‹‹ሲሉ ጠቅሰው፣ይህ ጉዳይ ለኛ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆንብን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮረናን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ ያደረጉ ወገኖችንም አመስግነዋል፡፡‹‹ሰሞኑን በገጠመን ፈተና በርካቶች የቁርጥ ቀን ዜጋ ማለት
ስለብዙዎች ሲባል መስዋእትነት የሚከፍል ነው የሚለውን ሀሳብ በተግባር አሳይተዋል፡፡››ብለዋል፡፡መስዋእትነቱ ጊዜን ፣እውቀትን ፣ገንዘብን እና ጉልበትን ከሁሉም በላይ ራስን መስጠት ሊሆን እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ሰው ስላለው ወይም ስለተረፈው ብቻ አይሰጥም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣መስጠት ለህዝብ መስዋእት ለመሆን ከመወሰን ቅን ሀሳብ፣ ጀግንነት ከተሞላበት ሀሳብ እንደሚመጣ አመልክተዋል፡፡
‹‹በዚህ ፈታኝ ወቅት ገንዘባቸውን ፣መኪናቸውን ቤታቸውን ህንጻቸውን እህላቸውን ያላቸውን ሁሉ የሚሰጡ የቁርጥ ቀን ልጆች ኢትዮጵያ እንዳላት ማየት ችለናል፡፡በቂና ብቁ መሳሪያዎች ባልተሟላበት ሁኔታ ከእኔ ለወገኔ ብለው ህዝባቸውን ለመታደግ የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች አግኝተናል፡፡ይህ ጊዜ ያልፋል፤እናንተ ሁላችሁም ኢትዮጵያውያን ከኮረና ቫይረስ የሚከላከለው ሰራዊት አባላት ናችሁ ፡፡ሁላችንም ይህን ሰራዊት ከተቀላቀልን ኮረናን የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በአጭር ጊዜ ልናሸንፈው እንችላለን፡፡›› ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮረናን የማሸነፊያው ብቸኛ መንገድ መደመርና ዲስፕሊንድ መሆኑን ከዓለም በተለይም ከቻይና መማር መቻሉን ጠቅሰው፣ ‹‹የኮረና ነገር ወደ ታሪክ መዝገብ ቤት ተልኮ ሀገር የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እንድትቀጥል ሁላችንም ዲስፕሊንድ ሆነን የሚነገረንን ማሳሰቢያ ተቀብለን መተግበር ይጠበቅብናል፡፡ይህን ማድረግ ከቻልን ትውልድ እኛን በኩራት ይጠቅሰናል፤የዚህ ዘመን ጀግኖች አድርጎ በትምህርት ቤት የሚማርብን ልንሆን እንችላለን፡፡›› ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ይህ እንዲሆን መተባበርና በዲስፕሊን መመራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተቻለ መጠን በሽታውን በአጭር ጊዜ በማስቀረት የተጀመረውን የብልጽግናና የሰላም ጉዞ ማስቀጠል እንዲቻል የቡኩሉን እንዲወጣ አስገንዝበዋል፡፡‹‹ያላችሁን ሁሉ ለሀገራችሁ በመስጠት በመስዋእትነት የተሰለፋችሁት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀገራችን ታመሰግናችሁአለች፡፡››ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2012
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኮረና በሽታን ለመከላከል ህብረተሰቡ እንዲተባበርና ራሱን ለዲስፕሊን እንዲያስገዛ ተጠየቀ