የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በ2003 ዓ.ም ተጀመረ።
• ግድቡ ሲጠናቀቅ ከ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በላይ ቦታ ይይዛል።
• የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመሙላት የሚወስድባት ጊዜ እስከ ሰባት አመት ነው።
• በሚመጣው ክረምት የውሃ ሙሌት ይጀ መራል።
•ታህሳስ 2013 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ። እያንዳንዳቸው የኃይል ማመንጫ ተርባይን 375 ሜጋዋት በጠቅላላው 750 ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨ ይችላሉ።
• በእያንዳንዱ ኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ የሚገነባና የሁሉም ዜጋ አሻራ ያረፈበት ነው።
• ግድቡ ሲጠናቀቅ 6ሺህ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።
• በርካታ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደልብ በማያገኝባት ኢትዮጵያ ግድቡ ሲጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል።
• ከዚህ ባለፈም እያደገ ለመጣው የማኑፋ ክቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ ይሆናል።
• ኢትዮጵያ ግድቡ ሙሉ በሙሉ ኃይል ማመንጨት ሲጀምርላት ለጎረቤት ሀገራት ኮረንቲ መሸጥ ትችላለች። በተለይ ደግሞ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ጂቡቲ ከሕዳሴው ግድብ ጥቅም የሚገኙ ሀገሮች ናቸው።
• ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሒደት 72 በመቶ ደርሷል።
• በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎቹ ከ42.3 በመቶ በላይ ተጠናቀዋል።
•የሲቪል ስትራክቸር የግንባታ ሒደትም ከ20 በመቶ በላይ አፈጻጸም አስመዝግቧል።
•መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ዘጠነኛ አመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም