የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል መንግስት ያወጣቸውን መመሪያዎች በአግባቡ በማይተገብሩ ዜጎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር አስታወቀ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግስት ዜጎች መጨባበጥን እንዲያቆሙ፣ ርቀትን እንዲያስጠብቁና ስብሰባ እንዲያቆሙ መመሪያ ቢያወጣም በአግባቡ እየተተገበረ አይደለም ብለዋል።
በመሆኑም የፌዴራል ፖሊስ በቅድሚያ የመምከርና የማሳወቅ ይህም አልፎ ካልተተገበረ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል ነው ያሉት።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ የምሽት መዝናኛ ቤቶች በወጣው መመሪያ መሰረት ስራ እንዲያቆሙ እያደረገ ቢሆንም አሁንም በመደበኛ ስራ ላይ የሚገኙ በመኖራቸው በቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልጸዋል።
በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ክልሎችን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ 5 ሺህ በሚደርሱ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ፣ ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ እና የንግድ ፈቃዳቸውን የመሰረዝ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም ጠቅሰዋል።
ቫይረሱን በተመለከተም ህብረተሰቡን የሚያደናብሩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በሚነዙ ግለሰቦች ላይ ኮሚሽኑ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ሃሰተኛ መረጃዎችን በሚያሰራጩ ብሎገሮች ላይም እርምጃ ለመውሰድ መረጃ የማሰባሰብ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት19/2012
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን በማይተገብሩ ዜጎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው