በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት መድረሱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ ኮቪድ 19ኝን በተመለከተ በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት የደረሰ ሲሆን በበሽታው የተያዙትም ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ናቸው።
የመጀመሪያው ታማሚ የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ ሲሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው። መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማድረጉ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 6 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል።
ሁለተኛው ታማሚ የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ከታማሚው በተገኘው መረጃ መሠረት ግለሰቡ የውጭ የጉዞ ታሪክ ባይኖራቸውም በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ግለሰቡ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቻውን አግልለው እንደቆዩና መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ሪፖርት ባደረገው መሰረት በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል።
ሶስተኛዋ ታማሚ የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የመጨረሻ ጉዞዋም መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም እስራኤል ሀገር ደርሳ የተመለሰች ናት። ግለሰቧም በ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዝዋ ተረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል። ከታማሚዋ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 7 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን ማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል።
አራተኛዋ ታማሚ የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ቢሆንም የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ እና ግለሰቧም በመጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዝዋ ተረጋግጧል። በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል።
አዲስ ዘመን መጋቢት19/2012
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሰ