አልዛይመር በተወሰኑ በሽታዎች ላይ የሚከሰት የአንጎል ተግባር ማጣት ነው። የማስታወስ፣ አስተሳሰብ፣ ቋንቋ፣ ፍርድን እና ባህሪን ይነካል። የአልዛይመር በሽታ (ኤዲ) ከጊዜ በኋላ ቀስ በቀስ እየባሰ የሚሄድ አንድ ዓይነት የመርሳት በሽታ ነው። ይህ በሽታ በአዛውንቶች ላይ የማስታወስ ችሎታን መታወክን ጨምሮ ሌሎች የተያያዙ ችግርችን በማስከተል ቀዳሚ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።
የበሽታው መንስኤዎች
በሽታው የአዕምሮ እንደመሆኑ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የነርቭ ሴሎችን (ኒውሮንስ) የሚያጠቁ የተለያዩ ፕሮቲኖች መኖራቸው ይታወቃል። በተለይም ከዚህ በሽታ ጋር የተያያዙ ሁለት ፕሮቲኖች በእንግሊዝኛ β-amyloid and tau ተብለው የሚጠሩ በአንጎል ሴሎች ላይ ጉዳት እንደሚያስከትሉ ይታወቃል።
የእነዚህ ፕሮቲኖች በነርቭ ሴሎች ውስጥ መከማቸት ከጊዜ ብዛት የነርቭ ሴሎቹ እንዲሞቱ ያደርጋል። የአንጎል ነርቭ ሴሎች መሞት ደግሞ በተራው የአንጎል ጤናማ ስራን ስሊሚያውክ በእንግሊዝኛ አጠራር (Dementia) ተብሎ የሚታወቀውን የአዕምሮ መዳከምን ሁኔታ ያስከትላል። በአማርኛ ትክክለኛ ትርጉም ባይኖረውም በተለምዶ በሀገር ቤት አዕምሮ ስቷል ተብሎ አንደሚነገር ይታወቃል። እንግዲህ ለመስማማት ዲሜንሽያ ወይም አዕምሮ መሳት ብንለው ይመረጥ ይሆናል።
አዕምሮ መሳት ከመርሳት ጀምሮ በትክክል ማሰብ አለመቻል ወይም የማገናዘብ ጉድለትና የቋንቋ ችሎታ መቀነስንም ይጨምራል። በብዛት የሚታወቀው ግን በመርሳት ነው። ይህም አንድ ሰው የመርሳት ሁኔታ ሲፈጠርበት ሌሎች ቶሎ ማወቅ መገንዘብ ስለሚችሉ ነው።
ይህ በሽታ በትክክል በምን ምክንያት አንደሚቀሰቀስ አይታወቅም። በሽታው በቤተሰብ ማለትም በዘር የሚተላለፍ መሆኑ ይታወቃል ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዛት ያላቸው የዘር ሰንሰለት (ጂኖች) መኖራቸውም ይታወቃል። እነዚህ የዘር ሰንሰለቶች በትውልድ ከወላጆች ወደ ልጆች በሚተላለፉበት ጊዜ ዝርያው ያለባቸው ሰዎች ለዚህ በሽታ ይጋለጣሉ ማለት ነው። ይህ በሽታ የሚከሰተው እድሜያቸው 65 አመት ያለፋቸው ሰዎች ላይ ቢሆንም በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፈው ከሆነ ከዚህ እድሜ ቀደም ብሎ ሊከሰት ይችላል።
የበሽታው ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ በሆነ መልክ ሊገለፁ ይችላሉ። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ከእድሜ ጋራ በተያያዘ የሚከሰቱ የመርሳት ወይም የመዘንጋት ሁኔታዎች ሊኖሩ አንደሚችሉ ነው። እነዚህ ግን በሽታው እንዳለባቸው ሰዎች መቆጠር የለባቸውም።
የበሽታው ምልክቶች ከሆኑት አንዱ የመርሳት ሁኔታ ነው በተለይም በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ነገሮች መርሳት ወይም ሰዎችን ማስታወስ አለመቻል ቀደም ብሎ የሚከሰት የበሽታው ምልክት ነው (ሰዎች የድሮ ነገሮችን የማስታወስ ችሎታቸው እንደተጠበቀ ሊቆይ ይችላል)።
መርሳት የሚጨምረው ነገር እቃዎችን ያለቦታቸው ማስቀመጥ፤ አቅጣጫና ቦታን መዘንጋት በተለይም ከዚህ ቀደም በሚያውቁት ሰፈር ሆነ ቤት አካባቢ መጥፋት፤ ድሮ ይሰሩ የነበሩ ነገሮችን ማከናወን አለመቻል ለምሳሌ የወር የሚከፈሉ እዳዎችን መክፈል አለመቻል፤ የፀባይ መቀየር ያልተለመደ ወይም አዲስ ባህሪ ማሳየትን ይጨምራል።
በሽታው እየከፋ ሲሄድ ደግሞ የተባባሰ የመርሳት ወይም የመዘንጋት ሁኔታ መከሰት፤ በመርሳት ምክንያት ደግሞ ግራ መጋባት፤ ባህሪ መቀየርና በተጨማሪም ሰዎችን መጠራጠር አለመተባበር እንዲሁም ሰዎችን የማጥቃት የመደባደብ ሁኔ ታን ይጨምራል።
በዚህ ደረጃ ደግሞ የቤተሰብ አባላትን ማወቅ አለመቻል ጓደኞችንም መዘንጋት ይጨምራል። ልብስ በደንብ አለመልበስ ወይም ለመልበስ የሰው እርዳታ ማስፈለግን የመፀዳዳት ችሎታም አለመኖር ማለትም በተገኘበት ቦታ ሽንትም ሆነ ሠገራን መልቀቅ ይጨምራል። በጣም የከፋ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ የመነጋገር ችሎታም ማነስና ለማንኛውም ነገር የሌሎች ሰዎችን እርዳታ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይፈጠርና ለመልበስ፤ ለመብላት፤ ለመፀዳዳት የሰዎች እርዳታ አስፈላጊ ወይም የግድ ይሆናል።
በእድሜ ምክንያት የመዘንጋት ሁኔታ ቢፈጠርም ከላይ ለተጠቀሱት እለት ከእለት ለሚደረጉ ሁኔታዎች ግን የሰዎች እርዳታ አስፈላጊ አይሆንም። ለመድገም ያክል በእድሜ ምክንያት የሚዘነጉ ሰዎችን ይህ በሽታ እንዳለባቸው አድርጎ መቁጠር ተገቢ አይደለም።
ምርመራዎች
የተለያዪ አእምሮንና አንጎልን የሚመለከቱ ምርመራዎች ይደረጋሉ። የምርመራዎች አንዱ ምክንያት የተከሰተው በሽታ በሌሎች ምክንያቶች አለመሆኑን ማረጋገጥ ይጨምራል። የአእምሮ መዘንጋት ወይም መሳትን (ዲሜንሽያን) የሚያስከትሉ ሌሎች ሁኔታዎች እንዳሉ ማወቅ ተገቢ ነው። እንግዲህ ሀኪሞች ደሞ ምርመራዎችን ጨምሮ ከሰረሰር ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራዎችን ሊያደርጉ ይችላሉ።
ህክምና
የአልዛይመር ፈውስ የለም እና በህይወትዎ ሁሉ መታከም አለበት። ሕክምናው የሚከናወነው በ ነው መድሃኒት የነርቭ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን፣ አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች (በሽተኛው በቅን ልቦና ተነሳሽነት የሚሠቃይ ከሆነ) እና ፀረ-ተባይ መድሃኒቶች (በታካሚው ውስጥ የበሽታው ስሜታዊ መቋረጥ በሚከሰትበት ጊዜ) ።
በተጨማሪም ህመምተኛው ልምምድ እንዲያደርግ ሊበረታታ ይገባል የአካል እና የእውቀት እንቅስቃሴ በማንበብ ፣ እንደ ስዕል፣ ሙዚቃ ያሉ ኮርሶች እና ሌሎችም እና ታዋቂው የመተላለፊያ (እንቆቅልሽ) እንቆቅልሽ። የሥነ ልቦና ባለሙያ መከታተል እንዲሁ በጣም ይመከራል።
ይህን በሽታ የሚያድን ህክምና በአሁኑ ጊዜ የለም። በሽታውን የሚያዘገዩ መድሃኒቶች ቢኖሮም በሽታውን መመለስ አይችሉም። ከበሽታው ጋራ በተያያዘ የሚፈጠሩ የአዕምሮ መጨነቅ መረበሽ እንቅልፍ ማጣትን የመሳሰሉትን ሁኔታዎች በህክምና ማርገብ ይቻላል።
ይህ በሽታ አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ቤተሰብ ላይ የሚፈጥረው ጭንቀት ከባድ ነው። በተለይም አብረው የኖሩት ሰው ሚስቱን ወይም ባሉን አለማወቅ ደረጃ ሲደርስ፣ በኖረበት ቤት እንግዳ ሆኖ መታየት ከባድ ነው። በዚህ በሽታ ችግር ከደረሰባቸው ከሚታወቁ ቤተሰቦች አንዱ የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬገንን ይጨምራል። በሽታው በአግባቡ ክትትል ከተደረገበት እና የህክምና እርዳታ ማግኘት ከተቻለ ማገገም ይቻላል።
ምንጭ- goshhealth.org