ለዜጎችን ቀልጣፋና ጥራት ያለው ፍትህ ለመስጠት የዳኝንት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን እያሻሻለ መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታቋል።
ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ስርዓቱን በማዘመን የተገልጋዮች ዕርካታ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ገልፀዋል።
ፍርድ ቤቱ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ረቂቅ መመርያ ለማፅደቅ ከፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በህግ ማእቀፎችን በተለይም በፍትሐብሔር እና በወንጀል ስነ ስርኣት ህጎችን ጉዳዮች እንዴት እልባት ሊሰጥባቸው እንደሚገባ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆንም እነዚህን በህጉ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮች ሂደት ስነ ስርኣት ባለመከተላቸው ምክንያት መፍትሄ ለማግኘት ከተገቢው ጊዜ በላይ ይወስዳሉ።
በተጨማሪም አንድ ጉዳይ የማቋጫ ጊዜውን ምንያህል እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ሁኖ ቆይተዋል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንትዋ ይህም የዜጎችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት በእጅጉ የሚጎዳ እና የተቋሙን ተአማኒነት ዝቅ የሚያደርግ መሆኑ ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ አሰራሩን በመሻሻል እና በማዘመን የዳኝነት ስርኣቱን ማጠናከር እና የተገልጋዮችን እርካታ ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እደሚገኝ ተቅሰዋል።
የዳኝንት ስርኣቱን ለመሻሻል በመከናወን ከሚገኙ ተግባራት መካከልመ የጉዳዮች ፍሰት አስትዳደርን ለመተግበር የሚያስችል ተቋማዊና ህጋዊ ማእቀፎች የተዘጋጁ መሆኑን ገልፀዋል።
በመአርግ ገ/እግዚአብሔር