
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የብዙዎችን ትኩረት ከሚስቡ የዓለማችን ክስተቶች መካከል ዘመናዊ ባርነት አንዱ ነው። በሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ዘመናዊ ባርነት የሰው ጉልበት የሚበዘበዝበት እና ለሥራው ብሎ ከአካባቢው የሚርቅበትን ሁኔታ የሚፈጥር ነው። በተለምዶ “የሰዎች ማዘዋወር” ወይም “የግዳጅ የጉልበት ሥራ” እና በዋናነት “ነፃ ያልሆነ” ከሚሉት ቃላት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው አልጀዚራ በድረገፁ ያስነበበው ዘገባ ያሳያል፡፡
እ.ኤ.አ ከ1990 ዎቹ ጀምሮ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ውስጥ ይህንን ዘመናዊ ባርነት ለመዋጋት የተሳተፉ ተቋማት እስከ ዛሬ ድረስ ቁጥራቸው እያደገ መጥቷል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የዓለም አገራት የተባበሩት መንግሥታት ዘላቂ የልማት ግቦች አካል በመሆን ባርነትን ለማጥፋት ፀረ-ባርነት ሕጎችን አፅድቀዋል፡፡
በፀረ-ባርነት ፖሊሲዎች ላይ በመንግሥት፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በየዓመቱ ያጠፋል፣ መገናኛ ብዙሃን ደግሞ የችግሩን ስፋት የሚያሳይ ዘገባ ስሜትን በሚኮረኩር መልኩ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ሆኖ የዘመናዊ ባርነት ፅንሰ ሐሳቦች እና የፖሊሲ አውጭዎች መፍትሔ በተለያዩ መንገዶች እየተተቹ ይገኛሉ፡፡
ምሁራን እንዳመለከቱት በተግባር ብዙ ሰዎች እራሳቸውን ዘመናዊ ባርነት በሚያጠቃልለው ጉዳይ ውስጥ ቢገኙም እራሳቸውን ዘመናዊ ባሪያ ብለው ለመጥራት አልደፈሩም፡፡
የዘመናዊ ባርነት ፅንሰ-ሐሳብ
“ዘመናዊ ባርነት” እንደ አንድ ፅንሰ-ሐሳብ ከአውሮፓና አሜሪካ የመጣ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1990 ዎቹ ብቅ ያሉት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ገንዘብ ለማሰባሰብ ይጠቀሙበት የነበረ የአስተሳሰብና መረጃ የማሰራጫ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚይዘው ዓለም አቀፋዊ ባርነት ዝርዝር አካሄድን ያወጣው ኬቨን ባሌስ ነው፡፡ የኬቨን ባሌስ ጽሑፍ እና ድጋፍ በሕዝባዊ ንቃተ-ህሊና ውስጥ የዘመናዊ ባርነት ሐሳብ እንዲመሠረት አግዟል።
ዘመናዊ ባርነት በነጮች፣ ሊብራል እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች በመምረጥ እና መስመር በማበጀት የሚከፋፍል ሐሳብ ነው፡፡ የምዕራባውያን ያልሆኑ ክስተቶች እንደ ችግር አለማየት ማለትም የደቡብ አካባቢዎች የድሀ ሰዎች መኖሪያ አድርጎ መውሰድ እና በተመሳሳይ ወይም ይበልጥ ችግር ውስጥ ያሉ የምዕራባውያን ክስተቶች በተለይም እንደ የስደተኞች ማቆያ ማዕከላት አሳሳቢነት አይመለከተንም የማለት አዝማሚያ የፈጠረ ክስተት ነው። እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በሊብራል ርዕዮት ዓለም ውስጥ ነፃነት ማለት አንድ ሰው በአካሉ ምንም አይነት መብት እንደሌለው ያትታል፡፡ ይህ ማለት በምዕራባዊያን ዓለም ዕይታ ውስጥ ማንም ቢሆን አንድ ነገር እንዲያደርግ የሚያስገድደው ነገር እስኪፈጠር ነፃ ሰው ነው፡፡
በመጀመሪያ ትንተናቸው ተመሳሳይ ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶችን ያስወግዳሉ። ሁለተኛ ደግሞ በውስጣቸው ለሚኖሩ ሰዎች ችግር ሊያስከትል የማይችሉ ክስተቶች በተለይም የኑሮ ዘይቤዎች ያዘጋጃሉ፡፡ ሦስተኛ ደግሞ የሁሉም ችግር ሊሆኑ የሚችሉ የሥራ ግንኙነቶች በማስተካከል እንዲሁም በሥራ ላይ ችግር ሊፈጠሩ የሚችሉ ግለሰቦች ላይ በማተኮር ሥራዎች በአግባቡ እንዲሠሩ ያደርጋሉ፡፡
በምዕራብ አፍሪካ እና በደቡብ አውሮፓ በተደረገው የመስክ ምልከታ በዘመናዊ ባሪያ አስተዳዳሪዎች ወይም በሕገ-ወጥ የሰዎች ማዘዋወር ወንጀል በተሳተፉ ባለሥልጣኖች ምክንያት ሕይወ ታቸው የተበላሸ ድሀ ሠራተኞች ቃላቸውን ሰጥተዋል።ሆኖም አብዛኛዎቹ ሁኔታዎች እነዚህ ሠራተኞች ራሳቸውን በሥራ መጠመዳቸውን ተገንዝበዋል ምክንያቱም ከዚህ ውስጥ የከተታቸው በጣም ውስን የሆኑ አማራጮች ስላሏቸው ነው፡፡
ነፃነት ማለት እምቢ የማለት ኃይል ነው የሚል ፅንሰ ሐሳብ በዘመናዊ ባርነት ውስጥ ተካቷል፡፡ ይህም ሰዎች ውጤታማ የሆነ አቅም እና ማንኛውንም ደስ የማይላቸውን ሁኔታ ውድቅ የማድረግ መብት አላቸው የሚል ነው፡፡ ይህንን መብት ለመጠቀም ነፃ መሆን አይጠበቅባቸውም፡፡ ይህ ማለት ማስገደድ እንደ መዋቅራዊ እንጂ ግለሰብ ላይ ብቻ ያተኮረ አይደለም፡፡የግለሰቡ ተጋላጭነት ደግሞ አንድ ሰው ያለውን ኃይል መዋቅራዊ በሆነ መልኩ የሚገድበውን ለመፍታት በማህበራዊ ቅደም ተከተል ውስጥ መኖር ይጀምራል ማለት ነው።
በዚህ ረገድ በኅብረተሰቡ ውስጥ ላለው አለመጣጣም ችግር የትኛውም የፖሊሲ ምላሽ ዘመናዊው ባሪያዎች ብቻ ተብለው የተጠሩትን ሳይሆን ለሁሉም ሰዎች መፍትሄ ያመጣል ማለት ነው፡፡
መሰረታዊ ገቢ በተለይም ከሠራተኛ ብዝበዛ ጋር በተያያዘ የሰዎች ነፃነት እንዲስፋፋ አንድ የፖሊሲ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለሁሉም የፖለቲካ ማህበረሰብ አባላት ዋስትና፣ መደበኛ እና ቅድመ-ሁኔታዊ ያልሆነ የገንዘብ ክፍያ ተብሎ ይገለፃል፡፡
ቀደም ብለው የነበሩ ምሁራን በተለይ ከ18 ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መሰረታዊ ገቢ መኖር አለበት ብለው ያምናሉ፡፡ ቢሆንም ደግሞ ሰዎች ከባድ ሥራን የመምረጥ ነፃነት ያላቸው በመሆኑ ጠንክረው እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል፡፡ በከባድ ሥራ ወቅት የሠራተኞች አቅርቦት ስለሚቀንስ የሚከፈለው ደመወዝ በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ይችላል። በተጨማሪም የእንክብካቤ ሥራን፣ ትምህርትን ወይንም የህብረተሰብ አገልግሎትን እንደ አማራጭ እንዲታዩ ያደርጋል፡፡
አዲስ ዘመን ታህሳስ 13/2012
መርድ ክፍሉ