አዲስ አበባ፡- በፓርኪንግ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሐሠተኛ ደረሰኞች የሚጠቀሙ ነአካላት በኤጀንሲው ሥራ ላይ ጫና እየፈጠ ሩበት መሆኑንና መንግሥትን የሚገባውውን ገቢ እያሳጣው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ትራፊክና ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የፓርኪንግ ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር ወይዘሮ ማዕርነት ገብረፃዲቅ በተለይም ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለፁት፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተደራጅተው በፓርኪንግ ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት ሐሰተኛ ደረሰኞችን በማዘጋጀት አግባብነት የጎደለው ተግባር እያከናወኑ ነው። በዚህም የተነሳ በኤጀንሲው ሥራ ላይ ጫና ከማሳደሩም በላይ መንግሥት ማግኘት የሚገባው ን ገቢ እያሳጡ መሆኑን አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማስጠንቀቂያዎች ሲሰጧቸው ፈቃደኛ አለመሆንና የማስፈራራት ሙከራ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል። ይህም ሥራውን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ ነው ብለዋል።
ዳይሬክተሯ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት 500 ወጣቶች በፓርኪንግ ሥራ የተሰማሩ ሲሆን 50 ማህበራትንም አቅፈዋል፤ ለወጣቶችም ሰፊ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በቂ ባይሆንም በከተማዋ ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥርዓት ለመተግበር ‹‹ስማርት ፓርኪንግ›› የተሰኙ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው። ቀደም ሲል በመገናኛ አካባቢ የተገነቡ ስማርት ፓርኪንጎች በአንድ ጊዜ እስከ 200 ተሽከርካሪ እንደሚ ያስተናግዱም ጠቁመዋል። ችግሩን ለማቃለል ሲባልም በቀጣይ በከተማዋ ውስጥ በተመረጡና ከማስተር ፕላኑ ጋር የተናበቡ 70 የሚሆኑ ቦታዎች ላይ ዘመናዊ የፓርኪንግ ግንባታዎችን ለማከናወን ታቅዷል።
በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ ፓርኪንግ ሥራ ዎች ባለመከናወናቸው መንገዶች የፓርኪንግ አገልግሎት እየሰጡ ነው። መንገዶቹን ከፓሪክንግ ነፃ ለማድረግ ቢታቀድም ካለው ችግር አኳያ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። በተለይም የፓርኪንግ እጥረት እና የሚመለከታቸው አካላት ትብብር አናሳ መሆን ችግሩን እንዳባባሰው ወይዘሮ ማዕርነት ገልፀዋል።
ስማርት ፓርኪንጎችን ለማልማት ከመንግሥት ባሻገር ባለሃብቱ እንዲያለማ አመቺ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይ በከተማዋ 10 ቦታዎች ላይ በጋራ የማልማት ውጥን መኖሩን አብራርተዋል። በዚህም ረገድ ባለሃብቱ በንቁ ሁኔታ እንዲ ሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህም ባሻገር ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥርዓት በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋና ህገ ወጥ አሠራሮች እንዲቃለሉ የመገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመፍጠርና ህግ አስከባሪዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲ ወጡም ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ህዳር 6/2012
ክፍለዮሐንስ አንበርብር