ጉበት ከደም ውስጥ መርዛማ ነገሮችን የሚያጣራና ቢያንስ ቢያንስ 500 የሚሆኑ ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን የሚያከናውን ሥራ ብዙ አባለ አካል እንደሆነ ይታወቃል። ሄፕታይተስ ወይም የጉበት ብግነት በሽታ የአንድን ሰው ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችለው እነዚህ ብዙ ሥራዎችን ሊያስተጓጉል ስለሚችል ነው።
ሄፕታይተስ አልኮል አብዝቶ በመጠጣት ወይም መርዛማ ለሆኑ ነገሮች በመጋለጥ ሳቢያም ሊመጣ ይችላል። ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ለሄፕታይተስ መንስኤ የሚሆኑት ቫይረሶች ናቸው። ተመራማሪዎች ሄፕታይተስ አምጪ የሆኑ አምስት ቫይረሶችን መለየት የቻሉ ሲሆን ቢያንስ ሌሎች ሦስት ዓይነት ቫይረሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምት አላቸው፡፡
ሄፕታይተስ
ሄፕታይተስ የሚያመጡ አምስት ዓይነት ቫይረሶች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን በስፋት የታወቁት ሄፕታይተስ ኤ፣ ቢ እና ሲ የሚባሉት ሦስቱ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ሁሉም የሄፕታይተስ በሽታዎች እንደ ኢንፍሉዌንዛ ያሉ የሕመም ምልክቶችን የሚያስከትሉ ሲሆኑ ዓይንን ቢጫ ሊያደርጉ ወይም ላያደርጉ ይችላሉ።
ብዙ ሰዎች በተለይም ደግሞ ትናንሽ ልጆች ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት አይታይባቸውም። በሽታው ሄፕታይተስ ቢ ወይም ሄፕታይተስ ሲ በሚሆንበት ጊዜ የሕመም ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ሊሆን ይችላል።
ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ
ከአምስቱ ቫይረሶች አንዱ የሆነው ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በየዓመቱ ቢያንስ 600,000 ሰዎችን እንደሚገድል መረጃዎች ያሳያሉ፤ ይህም በወባ ምክንያት ከሚሞቱ ሰዎች ጋር መስተካከል የሚችል ነው። ከሁለት ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ማለትም ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት በሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን አብዛኞቹ በወራት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ድነዋል።
በዓለም ላይ ከሚገኙ ሰዎች መካከል 350 ሚሊዮን በሚሆኑት ሰዎች ላይ በሽታው ሥር ሰዶባቸዋል። እነዚህ ሰዎች በቀሪ ሕይወት ዘመናቸው የበሽታው ምልክት ይኑራቸውም አይኑራቸው በሽታውን ወደ ሌሎች አስተላላፊ ይሆ ናሉ።
ሥር የሰደደ የሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ገና ከጅምሩ ተገቢውን ሕክምና ካገኙ በጉበታቸው ላይ የሚደ ርሰውን ከባድ ጉዳት ማስቀረት ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ለዚሁ ተብሎ በሚደረግ ልዩ የደም ምርመራ ካልሆነ በስተቀር ሊታወቅ ስለማይችል አብዛኞቹ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ እንኳ አያውቁም።
በተለምዶ የሚደረገው የጉበት ምርመራ እንኳ የበሽታውን ምልክት ላያሳይ ይችላል። በመሆኑም ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ ድምፅ አልባ ገዳይ በሽታ ሊባል ይችላል። በአንድ ሰው ላይ ግልጽ የሆኑ የሕመም ምልክቶች የሚታዩት በቫይረሱ ከተያዘ ከአሥርተ ዓመታት በኋላ ሁሉ ሊሆን ይችላል። በዚህ ወቅት ግን ሕመሙ ተባብሶ ስሮሲስ የተባለ የጉበት በሽታ ወይም ካንሰር ወደ መሆን ደረጃ ሊደርስ ይችላል።
ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ከአንዱ ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ኤድስ አምጪ ከሆነው ከኤች አይ ቪ ቫይረስ 100 እጥፍ ይበልጣል። በምላጭ ጫፍ ላይ ያለ የደም ቅንጣት እንኳ ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ ሊያስተላልፍ የሚችል ሲሆን የደረቀ የደም ጠብታ ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ቫይረሱን የማስተላለፍ አቅም ሊኖረው ይችላል፡፡
የሚታዩ ምልክቶች
ዐይንና ቆዳ ቢጫ የመሆን(Jaundice)፣ የሻይ መልክ ያለው ጠቆር ያለ ሽንት፣ ከፍተኛ የሰውነት ድካም ስሜት፣ የሆድ ሕመም፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ናቸው፡፡ የጉበት የመጀመሪያ ተግባሩ የተመገብነውን ምግብ በመሰባበር የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ማውጣት እና የምግብ መፈጨትን ያግዛል። ለጉበታችን ጤንነት እንድንጨነቅ እና እንድንጠነቀቅለት የሚያደርግ በርካታ የሆኑ ተግባሮችን/ሥራዎችን ጉበታችን በመወጣት ይጠቅማል። የሚከተሉት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፦
- የቆዳ ቀለም ለውጥ በዓይናችን ልናየው የምንችለው የጉበት ጉዳት/ በሽታ ምልክት የቆዳ ቀለም ለውጥ ነው፡፡ የቆዳዎ ቀለም ቢጫ ወይም የገረጣ/የፈዘዘ እየሆነ ከመጣ ጉበትዎ በትክክል ሥራውን እየተወጣ አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዕርዳታ ያስፈልግዎታል ማለት ነው። ይህ የቆዳችን ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር ዋነኛ ምክንያት ጉበታችን መርዛማ ነገር (ቶክሲን) ስለማይለቅ ሲሆን የዚህ መርዛማ ነገር አለመለቀቅ ቢሊሩቢን በቆዳዎች አካባቢ እንዲጠራቀም ያደርገዋል፡፡
- የሆድ ህመም ጉበታችን የሚገኝው በጎድን አጥንታችን አካባቢ ሲሆን የጉበታችን ጤናማ አለመሆን በሆዳ ችን እና በጎድን አጥንታችን አካባቢ ከፍተኛ የህመም ስሜት ይፈጥራል፡፡
- በተደጋጋሚ ማግሳት በሆድ/ አንጀት በአየር መነፋት ምክንያት በተደጋጋሚ በግሳት የሚሰቃዩ ከሆነ ጉበታችን ምግብን ለመፍ ጨት የሚሆን ኢንዛይም ማምረት ተስኖታል ማለት ነው። በተጨማሪም የምግብ መፍጨት ስርዓታችን በጉበት ችግር ምክንያት ይታወካል፡፡
- የድካም ስሜት መሰማት ጉበት ምግብን በሚሰባብርበት/እንዲፈጭ በሚያደርግበት ጊዜ በየቀኑ ሥራ ችንን ለመሥራት የሚጠቅም ኃይል/ ጉልበት እንድናገኝ ያደርጋል፡፡ በቀላሉ የምንደክም ከሆነ የጉልበት ማጣት ምልክት ነው፡፡ ይህም ጉበታችን ሥራውን በትክክል አለ መወጣቱን ያሳያል፡፡
- የሽንት ቀለም መለወጥ ጉበታችን መጎዳት በሚጀምርበት ጊዜ የሽን ታችን ቀለም ጠቆር ወዳለ ቢጫ ይቀየራል አንዳንዴም ወደ ደም ቀለም ሊወስደው ይችላል፡፡ አንዳ ንድ ሰዎች ይህ የቀለም ለውጥ ከፈሳሽ እጥረት እንደመጣ ያስባሉ፤ በቂ ውሃ ጠጥተው ይህ የቀለም ለውጥ ከተከሰተ የኩላሊት ጤና ታውኳል ማለት ነው፡፡
- ቆዳን ማሳከክ የጉበት በሽታ ማሳያ ከሆኑት አንዱ የቆዳ ማሳከክ ነው። በቆዳዎ ላይ የሚያሳክክ ቦታ ካለ እና ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ከመጣ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡
- ማቅለሽለሽ የምግብ አለመፈጨት እና የአሲድ አለመመጣጠን የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፡፡ የምግብ አለመፈጨት እና ማቅለሽለሽ የአመጋገብ ሁኔታችንን በመቀየር የማይስተካከል ከሆነ የጉበት ችግር ምልክት ነው። እየተባባሰ ሲሄድ ማስታወክ ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡
- የክብደት መቀነስ ድንገተኛ የሆነ የክብደት መቀነስ እንደ ጉበት ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ሳይፈልጉ ክብደት የሚቀንሱ ከሆነ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው ጉበታችን ደካማ ስለሚሆን ሲሆን ቀጭን እና የተጎዳ ሰው እንድንሆን ያደርገናል፡፡
- ፈሳሽን መያዝ በተላያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ፈሳሾች መቋጠር/ መያዝ በተለይ በእግር አካባቢ የደካማ ጉበት ምልክት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ኢዴማ() ይባላል እብጠት ይመስላል። ይህ እብጠት በጉልነት፣ እጅ አና እግር ጣቶች አካባቢ ይከሰታል፡፡ ያበጡትን ጣቶች ስንጫናቸው ጊዜ ለጥቂት ሰከንዶች ወደውስጥ ገብተው/ጎድጉደው ይቀ ራሉ፡፡
- የዓይነ ምድር ቀለም መቀየር የዓይነ ምድር ቀለም መቀየር አንድ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡ ትንሽ ደም ከዓይነ ምድር ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣ ከሆነ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ አለብን፡፡ ሌላው ከዓይነምድር ጋር የተያያዘ የጉበት ችግር ምልክት የሆድ ድርቀት ነው፡፡
ሄፕታይተስ ቢ ቫይረስ በበሽታው በተያዙ ሰዎች ደም እንዲሁም ከብልታ ቸው በሚወጡ ፈሳሾች ውስጥ ይገኛል። እንደነዚህ ያሉት ፈሳሾች ቫይረሱን የመከላ ከል አቅም በሌለው ሰው ሰውነት ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ቫይረሱ ይዛመታል።
ቫይረሱ በምን ይተላለፋል?
- በወሊድ ወቅት (በቫይረሱ ከተያዘች እናት ወደ ልጅ)
- በተገቢው መንገድ ከጀርም ያልጸዳ የሕክምና፣ የጥርስ፣ የንቅሳት ወይም ሰውነትን ለመብሳት የሚያገለግል ሌላ መሣሪያ፤
- መድኃኒት ለመስጠት የሚያገለግል መርፌን፣ ምላጭን፣ የጥፍር መሞረ ጃን ወይም መቁረጫን፣ የጥርስ ብሩሽን ወይም በቆሰለ የአካል ክፍል በኩል የደም ቅንጣትን ሊያስተላልፍ የሚችል ማንኛውንም ሌላ መሣሪያ በጋራ መጠቀም የለብንም፡፡
ሕክምናው
በባለሙያተኞች የቅርብ ክትትልና ዕርዳታ የሚሰጥ ነው፤ ሕክምናው በሽተኛው እንደሚገኝበት የአስጊነት ደረጃ የሚሰጥ ነው፤ ነገር ግን አንድ ሰው እንደ አዲስ በመጀመሪያ በሚለከፍበት ጊዜ በቂ ፈሳሽ፣ ተመጣጣኝ ምግብና ዕረፍት ሲያገኝ የማገገም ሁኔታው የተሻለ ይሆናል፡፡
የሄፕታይተስ ቢ በሽታ እውነታዎች
• ሄፕታይተስ ቢ በቫይረስ ልክፍት አማካኝነት የሚከሰት የጉበት በሽታ ሲሆን በሰዎች ላይ ስር የሚሰድ ዘላቂ በሽታ ያስከትላል፡፡
• ቫይረሱ በበሽታው ከተለከፉ ሰዎች ደምና ሌላም የሰውነት ፈሳሽ ጋር በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል፡፡
• ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ከ50 እስከ 100 እጥፍ ይበላጣል፡፡
• በክትባት አማካኝነት ሄፕታይተስ ቢን መከላከል ይቻላል፡፡
ማስጠንቀቂያ! ሄፕታይተስ ቢ ለሕይወት አስጊ የሆነ የጉበት በሽታ ነው፤ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሰፍኖ የሚገኝ በሽታ ነው፤ በዓመት በሄፕታይተስ ቢ ጦስ ምክንያት የሚሞተው ሰው ቁጥር 600,000 እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በቫይረሱ የተለከፉ ሰዎች ስር የሰደደ(chronic) ከሆነባቸው ሲውል ሲያድር ወደ ጉበት ብግነትና የጉበት ካንሰር በመቀየር ለህልፈተ ህይወት ይዳርጋል፡፡
በሽታው ሥር እንደሰደደ ይቆጠራል። በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም በሚፈስበት ጊዜ አንድ እጅ በረኪናን በ10 እጅ ውኃ በመበጥበጥ ጓንት አድርጎ የፈሰሰውን ደም ወዲያውኑ በሚገባ ማፅዳት ያስፈልጋል።
ምንጭ፡- ኢትዮ ጤና እና ጎሽ ሄልዝ ዶት
ኮም
አዲስ ዘመን ጥቅምት29/2012