አብዛኛው ሰው በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ጠዋት ወጥተው ወደ ሥራ አልያም ወደ ጉዳዩ ለመሄድ ሲያስብ ቀድሞ ፊቱ ድቅን የሚለው እንዴትና ምና ዓይነት የትራንስፖርት አማራጭ ያሰብኩበት እደርሳለሁ የሚለው ነው? ምናልባትም ረጅም ሰልፍ መሰለፍ አልያም በበርካታ ሰዎች መካከል ከላይ ታች እያሉ ትራንስፖርት ለመያዝ መጋፋት ይጠበቅብኝ ይሆን የሚለውም ሌላው ጭንቀት የሚያሲዝ ጉዳይ ነው?
ይህንን ችግር ለመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ከሌሎች የሚመለ ከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን በርካታ ሥራዎችን ቢሰራም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሳይቻል ቀርቶ ህዝቡ በትራንስፖርት ችግር መማረሩን ቀጥሏል? ችግሩን ለመፍታት ያልተቻለበት እንዲሁም በዚህ ሁኔታ የከተማው የትራንስፖርት ችግር የት እንደሚደርስና የታሰበ የመፍትሔ አማራጭ እንዳለ ስንል የከተማ አስተዳደሩን ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድን አነጋግረናል።
አዲስ ዘመን፦ የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነትን ከመ ወጣት አንጻር ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለጻል?
ኮማንደር አህመድ ፦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዋነኝነት ሁለት ዘርፎች አሉት ? አንደኛው ስምሪትና ቁጥጥሩ ሲሆን ሁለተኛው መሰረተ ልማቱ ነው? ከዚህ አንጻር ስምሪቱና ቁጥጥሩ ላይ የህዝብ ትራንስፖርትና የጭነት ትራንስፖርት በሚል ለሁለት ተከፍሏል።
በመሰረተ ልማት ዘርፉ ላይ ሼዶች፣ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች እንዲሁም የብዙሀን ትራንስፖርቶችን የምናቆምባቸው? የምናሳድርባቸውና የምንጠግንባቸው( ተርሚናልና ዴፖ) ናቸው?
ሆኖም ስልጣንና ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ፍላጎትና አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር ይስተዋላል? ለዚህ መነሻው ደግሞ በቂ የሆነ የመንገድ መሰረተ ልማት አለመኖር ሲሆን ይህ ደግሞ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት መኪኖች በፍጥነት ተመላልሰው አገልግሎት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል?
አሁን በቅርብ ያደረግነው ጥናት እንደሚያሳየው ለከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ከ 4 ሺ ያላነሱ የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ቢያስፈልጉም አሁን ያለን 1ሺ አካባቢ ነው? ታክሲዎችና ሌሎችም ያረጁና የተጎዱ በመሆናቸው ከህዝቡ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ አንጻር በቂ አይደሉም።
ሌላው ትልቅ ችግር የአሽከርካሪዎች ስነ ምግባር፣ የአገልጋይነት ስሜት ማጣት በዚህ የተነሳ ደግሞ ከታሪፍ በላይ መጫን ?አቋራጭ መንገዶችን መጠቀም? ተሳፋሪን ማመናጨቅና ሌሎችም የዘርፉ ከፍተኛ ፈተናዎች ናቸው።
ሌላው ዘርፉ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት ላይ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት አለበት? ከዚህ አንጻር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ ተወጥቷል ለማለት አያስደፍርም?ሆኖም ሁኔታውን ለማሻሻል እየሰራ ነው።
አዲስ ዘመን፦ በሥራው ላይ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችስ እንዴት ይገለጻሉ?
ኮማንደር አህመድ፦ አሁን ባለው ሁኔታ የመንግሥት ቁርጠኝነት ጥሩ ነው የትራንስፖርት ችግርም የከተማዋ ቁልፍ ችግር ነው ብሎ ለይቷል?ከዚህ ችግር ተስፈንጥረን መውጣት አለብን በሚልም ሥራዎች እየተሰሩ ነው?ይህን መሰል ትኩረት ማግኘት ደግሞ ለሥራ አስፈላጊ ነው? ሌላው ትራንስፖርት ባለስልጣኑ አሁን እንደ አዲስ በሰው ኃይልና በሚያስፈልጉ ግብዓቶች እየተደራጀ ነው፤ ሌላው ትራንስፖርትን የምናሰማራበት ከ 4 መቶ መስመር በላይ መነሻና መድረሻ እንዲሁም መጫኛ ቦታዎች መኖራቸው ነው?ምክንያቱም አንድን የትራንስፖርት ተሽከርካሪ ከየት ወዴት እንደሚላክና በየት እንደሚያልፍ ለማወቅም የሚያስችል በመሆኑ፤ ስለዚህ በቂ ኃይል ብናገኝ በመስመሮች ላይ አሰማርተን ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንችላለን።
አዲስ ዘመን፦ ግን አደረጃጀቱ እንደገና እየተሰራ ነው ብለዋልና ለጊዜው ይህንን ሥራ ለመስራት የሚያስችል ቁመናስ አለው?
ኮማንደር አህመድ ፦ አደረጃጀቱ ላይ ራሱ የስምሪትና የቁጥጥር የሰው ኃይል በቅርንጫፍ እንዲሁም በማዕከል በሁለት ዳይሬክተር የሚመራ ነው?ይህ ደግሞ በስምሪት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ የሚያደርግ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቋሚ ፍተሻን የሚያደርግ ነው፡፡
ለምሳሌ ባሳለፍነው መስከረም ወር ሰሌዳ ቁጥር (ኮድ) 1 ላይ ወደ 171 ተሽከርካሪዎች ከስምሪት ውጪ በመሄድ? በታሪፍ ጭማሪ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የተቀጡ ሲሆን ሰሌዳ ቁጥር (ኮድ) 3 ትም 1ሺ 139 አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ቅጣት ተቀጥተዋል?
አዲስ ዘመን ፦ ሰው ላጠፋው ጥፋት መቀጣት ያለበት ቢሆንም ግን ቅጣት ብቻውን መፍትሔ ይሆናል? ያለውንስ የትራንስፖርት ችግር ይፈታዋል ብለው ያምናሉ?
ኮማንደር አህመድ፦ ቅጣት አስተማሪ ነው ለማለት አይደለም፣ ቢያስተምርማ ኖሮ ከቅጣት ብቻ በወር ውስጥ 6 እና 7 መቶ ሺህ ብር መሰብሰቡ ብዙዎችን ያስተምር ነበር?ከዛ ይልቅ ሰዎች አእምሮ ላይ መስራት ያስፈልጋል።
አዲስ ዘመን ፦ የትራንስፖርት ዘርፉ የብዙ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነውና፤ በዚህ ላይ ያለው የቅንጅት ሥራስ እንዴት ይገለጻል?
ኮማንደር አህመድ ፦ የትራንስፖርት ዘርፉ በአንድ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ብቻ የሚሰራ አለመሆኑ ግልጽ ነው፤ እኛም ከትራፊክ ፖሊስ ፣ ደንብ ማስከበር፣ ከፖሊስ እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየሰራን ቢሆንም በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡
ለምሳሌ በሞተር ሳይክልና በከባድ መኪኖች እንቅስ ቃሴ ላይ የተጣለውን እገዳ ተፈፃሚ ለማድረግ በጋራ ሰርተናል፤ ሌሎችም ሥራዎችን ከእኛ ይልቅ እንደውም እነሱ ናቸው በትኩረት እየሰሩበት ያሉት ይህንን አካሄድ ደግሞ ወደፊትም የመግባቢያ ስምምነትበመፈራረምለማጠናከር እናስባለን፡፡
አዲስ ዘመን፦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራሱ የትራንስፖርት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ችግሩ ግን ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ነው፤ የዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? መፍትሔውስ?
ኮማንደር አህመድ፦ እዚህ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀድሞ የነበረበትና አሁን ያለበት ሁኔታ ለውጥ አለው፤ ይህንን የምንለው ደግሞ እኛ ውስጣችንን ፈትሸን ባየነው ልክ ነው፤ አሁን ላይ ለዘርፉ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየወጣ ነው ፤ ግን ደግሞ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ዛሬም ህዝብ ለትራንስፖርት ጥበቃ ረጅም ሰለፍ ይሰልፋል፣ ያልተገባ ታሪፍ ይከፍላል፣ ይሰደባል፣ ትርፍ ይጫናል ?ብዙ ችግሮችን አልፎ ነው ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሰው፤ ስለዚህ ይህ በዘላቂነት መፈታት እንዳለበት ተቋሙ ያምናል፤ ችግሮቹንም ለይቷል፣ አሁን ላይ ህብረተሰቡ ከጉዳቱ አንጻር ለውጡ ባይታየውም አይፈረድበትም?
አዲስ ዘመን፦ ዘላቂ መፍትሔው ምንድን ነው ብላችሁ ነው ያስቀመጣችሁት?
ኮማንደር አህመድ፦ በአጭር ጊዜ የማንፈታቸው አሉ፤ ለምሳሌ የመንገድ ችግር በጣም ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል፤ነባር መንገዶችን ማፍረስ ይፈልጋል ትራንስፖርት ባለስልጣን ምንም አድርጎ ሊፈታው አይችልም፣ ሆኖም በሂደት ከስር ከስር ጊዜያዊ መፍትሔ እየሰጠን መቆም ያለበትም እንዲቆም እያደረግን እንሰራለን።
አዲስ ዘመን፦ መንገድ ማስፋት ከእናንተ አቅም በላይ ሊሆን ይችላል ግን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ መስራት አይቻልም?
ኮማንደር አህመድ፦ ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር እንገናኛለን፤ ምን ይደረግ በማለትም እንወያያለን፤ ግን እነሱም ከአቅም በላይ ሆኖባቸዋል፤ አሁን ባለው ሁኔታ አንድ መንገድ ለመስራት ሌላ ችግር መፍጠር ነው የሚሆነው ምናልባትም አንድና ሁለት ዓመት የበለጠ ችግር ይፈጠራል?
አዲስ ዘመን፦ አዎ መንገዶች ሲሰሩ መጨናነቅ ይፈጠር ይሆናል፤ ግን በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቁበትን እንዲሁም ሌሎች አቋራጮች የሚዘጋጁበት ሁኔታ አብሮ ማየት አይሻልም? ወይስ የበለጠ ችግር ይፈጠራል ብሎ መተው ነው አማራጩ?
ኮማንደርአህመድ፦ዘላቂመፍትሔውማ መንገዶችን መስራትና ማስፋት ነው ፤ ለምሳሌ የአቃቂ ቃሊቲ መንገድ ስራው በመጀመሩ አሁን ላይ በጣም ችግር ተፈጥሯል ግን ወደፊት ብሩህ ተስፋ ነው ያለው ፤ እነዚህ በጣም ትልቅ ተስፋ ያላቸው ሥራዎች ጊዜ ስለሚወስዱ ወቅታዊውን የህብረተሰቡን ችግር ሊፈቱ አይችሉም ፤ አሁን ያለው ሁኔታ እንደውም ወደፊት እንኳን በመኪና በእግር ለመሄድ አስቸጋሪ ይሆናል? ይህንን ደግሞ ቦታው ላይ እንዳለ ሰው ሆነሽ ስታስቢው እንቅልፍ የሚነሳ ነው፡፡
ይህንን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት ግን የብዙሀን ትራንስፖርትን ማሳደግ እንደ አማራጭ ተይዞ እየተሰራ ነው? ይህንንም ለመተግበር ያግዝ ዘንድ ካቢኔው በተያዘው በጀት ዓመት 3 ሺ አውቶቡሶች እንዲገዙ ወስኗል፡፡
አዲስ ዘመን፦ጥሩ ነው የብዙኃን ትራንስፖርት ማስፋቱ ግን መንገዶች የሉንም እያልን በየትኛው መንገድ ላይ ልንጠቀምባቸው ነው እነዚህን ሁሉ አውቶቡሶች የሚገዙት?
ኮማንደር አህመድ፦ አዎ የታሰበው ለአውቶቡስ ብቻ ተብሎ የተከለለ መንገድ እናመቻቻለን የጀመር ናቸውንም እናጠናክራለን በማለት ነው? እነዚህ መንገዶች መጠናከራቸው ደግሞ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎቹ ቶሎ ቶሎ እየተመላለሱ ህብረተሰቡን በሚገባ እንዲያገለግሉ ከማድረጉም በላይ በሌላ አገር የተለመደና አዋጭ የትራንስፖርት አማራጭ ነው።
ሌላው አሁን በቅርብ ፈጣን የሆኑ የአውቶቡስ መንገዶችን እንሰራለን፤ ከፍጥነታቸው አንጻር ደግሞ ህብረተሰቡን በተገቢው መንገድ ያገለግላሉ ምናልባትም አውቶቡሶቹ መኪና ያለውንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠቅሙ ስለሚሆን ሰው መኪናውን አቁሞ በእነሱ በመገልገል ያለውን የመንገድ መጨናነቅ በዛው ልክ ሊፈታው ይችላል።
አዲስ ዘመን ፦ አሁን ያሉኝ ፈጣን የአውቶቡስ መንገድ ከታሰበ ብዙ ጊዜ አልፏል፤ እስከ አሁን ወደ ሥራ ባይገባም ከዚህስ በኋላ ለሥራው ያለው ቁርጠኝነት እስከምን ድረስ ነው?
ኮማንደር አህመድ ፦ የከተማዋ ትልቁ ችግር የትራንስፖርት ነው ተብሎ በበላይ አመራሮችም ስለታመነበት አሁን ላይ ለሥራው ያለው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ዛሬ ነገ የሚባልበት ምንም ምክንያት የለም፤ በተያዘው በጀት ዓመት ግዢውም ይፈጸማል ሥራውም ይጀመራል?
እስከዛ ድረስ ደግሞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለአውቶቡስ ብቻ ተብለው የተለዩ መንገዶች እንዲከበሩና የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል?በሌላ በኩልም በግራና በቀኝ እየቆሙ መንገዶችን የሚያጨናንቁ መኪኖችን በተለይ በሥራ መውጫና መግቢያ ሰዓት እንዳይቆሙ ይደረጋል ።
አዲስ ዘመን ፦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ይፈታል ያለውን እርምጃ በተለያየ ጊዜ ይወስዳል እየወሰደም ነው በተለይም ከዓመታት በፊት የጀመረው ዞናዊ ስምሪት (ታፔላ) አሁን ላይ ስታዩት ምን ያህል ችግር ፈቷል ትላላችሁ?
ኮማንደር አህመድ፦ ዞናዊ ስምሪት አጀማመሩ በሁሉም አካባቢዎች እኩል የሆነ የታክሲ ትራንስፖርት ክፍፍል እንዲኖር ማስቻል ነው፤ ምናልባትም ይህ የስምሪት አካሄድ ባይኖር ኖሮ ሁሉም ጥቅም አገኝበታለሁ ብሎ በሚያስብበት አካባቢ ብቻ በመከማቸት የበለጠ ችግር ይፈጠር ነበር?እውነት ለመናገር የዞናዊ ስምሪት (ታፔላ) ጉዳይ በጣም አስፈላጊና ከአተገባበር ክፍተት ሌላ ችግር ፈቺ ነው ሊባል ይችላል።
በዚህ ሥራም በተቻለ መጠን ታክሲዎች በሁሉም አካባቢ ተደራሽ እንዲሆኑ፣አንድ ቦታ ላይ ብቻ እንዳይከማቹና በሚሰጣቸው ዙር በተመደቡበት ቦታ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ሆኗል፣ እንደውም አሁን ላይ ዙሩ በራሱ ከሰዎች ንክኪ ነጻ እንዲሆን በማሰብ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ እየተሰራ መሆኑ ሥራውን የበለጠ የተሳለጠ እንዲሆን አድርጎታል?
የዞናዊ ስምሪት (ታፔላ) ውጤት እንግዲህ ‘ ከባዶ ይሻላል’ በሚለው ብንይዘው ጥሩ ነው፣ ዞናዊ ስምሪቱ አሁን ላይ ቢቀር ብለን ብናስብ የባሰ ችግር ውስጥ ነው የምንገባው፤ ከዚህ ይልቅ ተቋሙ ስምሪቱን ሲሰጥ ምንድን ነው ያለበት ድክመት ብሎ መመርመር አዋጭ ነው ።
አዲስ ዘመን፦ እስከ አሁን በስምሪቱ ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን አልመረመራችሁም?
ኮማንደር አህመድ ፦ መርምረናል ከክፍተቶቹ መካከል ዞናዊ ስምሪቱን (ታፔላውን) ሆን ብሎ መደበቅ? መጣል እንዲሁም ጥፋት አጥፍተው ሲቀጡበትም ገንዘቡን ከፍሎ ከመውሰድ ይልቅ ጠፋብኝ ብሎ ሌላ ማውጣት ይጠቀሳሉ?
አዲስ ዘመን ፦ እነሱ ጠፋብን ይበሉ ግን ጥፋት አጥፍተሀል ብሎ ታፔላውን የቀማው ሰራተኛ ይህንን ሪፖርት አያደርግም በዛ መሰረትስ መስተናገድ የለባቸውም?
ኮማንደር አህመድ፦ ሪፖርት ያደርጋል ሆኖም አፈጻጸሙ ላይ ከፍተኛ የሆነ ማጭበርበር ስላለ ጠንከር ብሎ መስራት ይጠይቃል ?ለምሳሌ ከዚህ ቀደም የትራፊክ ህግ ጥሰት የፈጸሙ አሽከርካሪዎች ይከሰሳሉ የክስ ወረቀት ይቆረጥላቸዋል። ግን ማንም ገንዘቡን ለመክፈል ፍቃደኛ አልነበረም? ምክንያቱም መንጃ ፈቃዳቸው እነሱ ጋር ስለሚሆን? አሁን ታፔላ ላይ ያለው ሂደትም ይህ ነው፤ ጥፋት ያጠፋሉ ይከሰሳሉ ታፔላቸው ይወሰዳል እነሱ ግን ቅጣቱን ከመክፈል ይልቅ በጎን ጠፋብኝ ብለው ሌላ ይወስዳሉ? ይህ አካሄድ በአሰራር ሊፈታ የሚገባው እንደሆነ ተማምነናል? ወደፊትም ጥብቅ ቁጥጥር እናደርጋለን ብለን በእቅድ ከያዝናቸው የሥራ ሂደቶች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።
አዲስ ዘመን፦ዞናዊ ስምሪትን ከየለም ይሻላል ያሉትን እኔም እጋራዋለሁና ግን አገልግሎት ሰጪው አምኖበት እንዲያገለግል ተጠቃሚውም በአገልግሎቱ እንዲረካ አስተሳሰብን መቀየር ላይ የተሰራ ሥራ አይታይም ለምን?
ኮማንደር አህመድ ፦ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራው በተገኘው አጋጣሚ ይሰራል ግን በቂ አይደለም፤ መገናኛ ብዙሀንን ተጠቅሞም በመስራቱ በኩል ብዙም የተሄደበት ነገር የለም፤ ሆኖም አገልግሎት ሰጪው ከመስመሩ ውጪ በመጫን ሰውን ሲያጉላላ ታሪፍ በራሱ ፍቃድ ሲጨምር የእሱም ቤተሰብ በተመሳሳይ ሁኔታ እየተጎዳ መሆኑን መገንዘብ ነው የሚያስፈልገው።
በሌላ በኩልም ተጠቃሚው አእምሮ ላይም መሰራት ይጠይቃል፤ ምክንያቱም መንግሥት በቀጣይ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር የምፈታው የብዙሀን ትራንስፖርትን በማስፋፋት ነው ይላል የኛ ማህበረሰብ ባዶ አውቶቡስ ቀርቦለት ታክሲ ካላገኘሁ ብሎ ረጅም ሰልፍ የሚሰለፍ ነው፤ በመሆኑም አእምሮ ላይ የሚሰራው ሥራ በጣም ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይ የምንሰራው ይሆናል።
አዲስ ዘመን፦አብዛኛው የከተማው ትራንስፖርት ስምሪት በቀጥታ የሚመለከተው እናንተኑ ነውና እንደው የስምሪት ሰዓታችሁ የተገደበ ይመስላል፤ እንቅስቃሴ እስካለ ድረስ ለምን ባለሙያ መድቦ ማሰማራት አልተቻለም?
ኮማንደር አህመድ፦ የእኛ የስምሪት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ማታ 3 ሰዓት ድረስ በሁለት ሽፍት ነው? የትኩረት ሰዓታችን ጠዋት እስከ 4 ሰዓትና ከ10 ሰዓት በኋላ ያለው ነው?ግን ሁሉንም ነገር በሚገባው ልክ ለመቆጣጠር ባሉን 5 መቶ ባለሙያዎች ላይ ተጨማሪ 5 መቶ ባለሙያዎች ያስፈልጉናል?
አዲስ ዘመን፦ ባለሙያዎቻችሁ ላይ ከስነ ምግባር ጉድለት እንዲሁም ከሙስና ጋር ብዙ የሚባሉ ነገሮች አሉና ምን ያህል ትቆጣጠሯቸዋላችሁ?
ኮማንደር አህመድ፦ በዋነኝነት እነሱን የሚቆጣጠሩት ቅርንጫፍ ላይ ያሉት አካላት ናቸው?ሆኖም ግን በማዕከል መደበኛ የሆነና ድንገተኛ ቁጥጥር የሚያደርጉ ሁለት ዳይሬክተሮች አሉ።
እነዚህ ዳይሬክተሮችም ባለሙያው በተመደበበት ቦታ ላይ አለ ወይስ የለም ?እርሱ ባለበት ቦታ አግባብነት በሌለው ታሪፍ ይጫናል? በመስመሩ መግባት ያለባቸው ተሽከርካሪዎች ገብተዋል? ረጅም ሰልፍ አለ የሚሉና ሌሎች ነገሮች ይታያሉ።
ግን በዚህ ልክ ሙሉ ነው ወይ ቢባል ለሥራው ብዙ ምቹ ሁኔታ ካለመኖሩ እንዲሁም በጸሐይና አቧራ ላይ ስለሚሰራ፣ የሰዎችን ባህርይ መቻል ከማስፈለጉ አንጻር ሙሉ ነው ለማለት አይቻልም፤
በዚህ ሂደትም በሥራ ቦታቸው ላይ ያልተገኙ ወይም ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር አግባብነት የሌለው የጥቅም ግንኙነት ያደርጋሉ ተብለው በሚጠረጠሩና መረጃ በተገኘባቸው ባለሙያዎች ላይ እስከ ማባረር የደረሰ እርምጃ ወስደናል።
አዲስ ዘመን፦ የእናንተ ባለሙያዎች አብዛኞቹ ከአገልግሎት ሰጪው ጋር የጥቅም ትስስር እንዳላቸው አታውቁም ?
ኮማንደር አህመድ፦ ማንም ቢሆን በግልፅ አይሰርቅም ፤ ይኼ መረጃ ነው እንሰማለን ሀሜቶች አሉ ግን ደግሞ አይደረግምም አንልም፤ ምክንያቱም ይህንን ሲያደርጉ ተገኝተው የተባረሩም ስላሉ? አሁን ላይ ታክሲዎች በስምሪታቸው መሰረት መግባት አመግባታቸውን ይፈርማሉ። ግን አንዳንዶች ይህንን ሳያደርጉ በሳምንት አንድ ቀን ከባለሙያው ጋር ተገናኝተው ያስፈርማሉ ይህ እንግዲህ ምንም ማለት አይደለም ባለሙያው በሳምንት እቁብ ይጣጥለታል ማለት ነው፤ በእርግጥ ሁሉም ይህንን አያደርግም የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ የሚያደርጉ እንዳሉ እናውቃለን።
ይህንን ለማስተካከልም ለምንድን ነው ሰዎችን በየቀኑ የሚቆጣጠሩበትን ቦታ የማንቀያይረው በማለት አሰራሩን ጀምረናል፤ በዚህም አንድ ባለሙያ ዛሬ የተመደበበት ቦታ ላይ የሰራበትን ይዞና አስተላልፎ ወደ ሌላ ምድብ ይሄዳል በዚህ ደግሞ ማን የት እንደሚመደብ አይታወቅም ይህንን አሰራር ላለፉት ሁለት ወራት ሰርተንበት ውጤት አምጥቷል።
ይህ በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ አሽከርካሪዎች አልተፈረመልኝም እያሉ እኔ ጋር ሳይቀር መደወል ጀምረዋል?ስለዚህ ሙስናውን የመፈጸም ሂደቱን በዚህ አጥብበነዋል።
በቀጣይ ግን ይህንን አሰራር በቴክኖሎጂ መደገፍ ስለሚያስፈልግ አሁን የሞባይል አፕልኬሽን እየሰራንና እየሞከርን ነው? ይህ ወደ ሥራ ሲገባ መኪናው የት እንዳለ በመስመሩ መግባት አለመግባቱን ወዲያው የሚያሳውቅ በመሆኑ ለሰዎች አድሏዊ አሰራርም ስለማይመች ጥሩ ውጤት ይመጣበታል የሚል እምነት አለኝ።
አዲስ ዘመን፦ እዚህ ላይ ግን ይህ የትራንስፖርት ዘርፍ ከዚህ ቀደምም አሁንም የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች ቢሰሩለትም ውጤቱ ግን የሚታይ አይደለምና እንዴት ነው ማደግ መለወጥ የሚችለው ይላሉ?
ኮማንደር አህመድ፦ እንደ ትራንስፖርት ባለስልጣን በዘርፉ የተማሩና የብዙ ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው ሙያተኞች አሉ፤ እነሱን በመጠቀምም ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ነው፤ ሁል ጊዜም እንዴት እናሳድገው የሚሉ ውይይቶች ይደረጋሉ፤ ግን ትልቁ ችግር ሥራው እየተሰራ ስላልመጣና ብዙ የተከማቹ ችግሮች ያለበት ዘርፍ በመሆኑ በአንድ ጊዜ ይህንን ዓይነት ለውጥ አመጣበታለሁ ማለት ከባድ ነው?
በሌላ በኩል ፍላጎትንና አቅርቦትን ለማጣጣም ብዙ መስራትን ይጠይቃል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ብዙ ክፍተቶች ያሉ ቢሆንም ግን እንደ ትራንስፖርት ባለስልጣን ብዙ ለውጦችም አሉ ብለን ነው የምንወስደው?ሆኖም ህብረተሰቡ ሁሌም ለሚፈጠሩት እንግልቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ነው የሚወቅሰው ፤እንግዲህ የእድል ጉዳይ ሆኖ በዚህ ሥራ ላይ አንድም ቀን ደስተኛ መሆን አይቻልም፤ ለውጥ ቢኖርም በተጨባጭ ህብረተሰቡን የሚያረካ ነገር አልመጣም?
አዲስ ዘመን፦ የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ሥምሪት (ኢታስ) አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች ምንድን ናቸው?
ኮማንደር አህመድ፦ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ህግን ተከትሎ ነው የሚሰራው፤ በዚህም መሰረት የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ሥምሪት (ኢታስ) መመሪያ አውጥቷል፤ ይህ መመሪያም ተፈጻሚ መሆን አለበት ብሎ እየሰራ ነው።
አዲስ ዘመን፦እስከ አሁን መመሪያው አልነበረም?
ኮማንደር አህመድ ፦ እስከ አሁን አዋጆች ምናምን ሊኖሩ ይችላሉ ግን መመሪያው አዲስ የወጣ ነው፤ ቴክኖሎጂው በወጣ ጊዜ ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ ወቅቱን ጠብቆ ነው የሚወጣው?አሁን ዘመኑ ላይ ያሉትን በቴክኖሎጂ ተደግፉ አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን ለመቆጣጠር መመሪያው ወጥቷል?መመሪያውም የታክሲ መመሪያ ነው፤ ታክሲዎች ኤሌክትሮኒካል በሆነ ሲስተም እንዴት ይሰማራሉ የሚል ነው፤የሥራ ቅኝቱ ታክሲ ላይ ብቻ ነው?
አዲስ ዘመን ፦ በኢታስ ሲስተሙ ግን እኮ ሶስት ቁጥር ሰሌዳ ያላቸው ተሽከርካሪዎች የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ፍቃድ ሰጥታችሁ ሲሰራበት ነው የቆየው?
ኮማንደር አህመድ ፦ አዎ ድርጅቶቹ በኤሌክትሮኒክስ ሲስተሙ አማካይነት ታክሲ እንዲያሰማሩ ፍቃድ ተሰጥቷል። በመሆኑም አሁን የተባለው ታክሲ ተብለው በህግ ከሚታወቁት ውጪ ያሉትን ማሰማራት አትችሉም ነው ? ይህንን ያልንበት ዋናው ምክንያት ደግሞ ሰሌዳቸው አንድ ቁጥር ሆኖ የታክሲ ንግድ ፈቃድ እውጥተው ህጉን ተከትለው ወደ ሥራ የገቡ እያሉ በ ሁለትና ሶስት ቁጥር ሥራው የሚሰራ ከሆነ እነዛ አካላት ምን ይሆናሉ የሚለውንም በማጤን ነው መመሪያው የተዘጋጀው?
ስለዚህ ህግና ስርዓትን ከማስፈን አንጻር መመሪያው ተግባራዊ መሆኑ የግድ ነው? ያሉንን ታክሲዎች ዘመናዊ ማድረግና ከቴክኖሎጂ ጋር ተናበው የመስራት አቅማቸውን ማሳደግ ላይ መሰራት እንዳለበት እኔም እስማማለሁ ፤ ከዛ ውጪ ግን ሁሉም እየተነሳ የታክሲ አገልግሎት እሰጣለሁ ካለ ህጋዊውን አካል ከመስመር ማስወጣት ነው የሚሆነው።
አዲስ ዘመን፦ ይህ ሁሉ ግርግር ከመከሰቱ በፊት በተለይም ሶስት ቁጥር ሰሌዳ የለጠፉ አካላት ወደ አገልግሎቱ ሲገቡ መቆጣጠር አይቻልም ነበር?
ኮማንደር አህመድ ፦ መጀመሪያም ሰሌዳ ሲያስቀይሩ እኮ በሚሰጣቸው የባለቤትነት መታወቂያ (ሊብሬ) ላይ ለምን አገልግሎት መጠቀም እንደሚችሉ በግልጽ ተቀምጧል?እኛ ጋር ያለው መረጃና የሚሰራው ሥራ ነው ልዩነት የፈጠረው?በእርግጥ ወደታክሲ ሲገቡም መቆጣጠር ይቻል ነበር፤ እገዳም ያስፈልግ ከነበረ ስምሪት የሚሰጠውን አካል ነበር ማገድ የሚቻለው፤ ይህንን እንዳናደርግ ደግሞ እነሱን ለመከልከል የሚያስችል ህግ አልነበረም? ህጉን ለማውጣትም በጣም ብዙ ጊዜ ወስዷል?ግን መቼም ይሁን መቼ የወጣውን ህግ በተግባር መተርጎም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ነገ ከነገ ወዲያ ሥራው ድብልቅልቅ ነው የሚለው።
አዲስ ዘመን ፦ከቴክኖሎጂ አመንጪዎቹ ጋር አሁን በምን አይነት የሥራ ግንኙነት ላይ ናችሁ ?
ኮማንደር አህመድ፦ አሁን ከእነሱ ጋርም በጣም ተግባብተናል ፤ ህጉም ያሰራናል በዛ መሰረት መቀጠል አለብን የሚል መግለጫም እየሰጡ ነው?
አዲስ ዘመን፦ በቀጣይ የትራንስፖርት ዘርፉን ችግር የሚፈቱ ምን አዳዳስ ነገሮች ይጠበቃሉ ?
ኮማንደር አህመድ፦ እንግዲህ ዋናው መሰረተ ልማትን ማልማት አለበን የሚል ነው፤ ምክንያቱም ለትራንስፖርት አገልግሎት መሳለጥና ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣው እርሱ በመሆኑ? ይህ ሲባል ደግሞ ቴክኖ ሎጂንም ይጨምራል ተርሚናሎችና ዴፖዎች ደግሞ በጣም ወሳኝ ናቸው?እነዚህ ነገሮች ደረጃቸውን ጠብቀው በዘመናዊ መልኩ ከተዘጋጁ እንኳን መንግሥት ግለሰቦችም አውቶቡሶችን የማያስገቡበት ምክንያት አይኖርም።
ሌላው የብዙሀን ትራንስፖርት አቅርቦትን ማፋጠን ነው፤ ከታክሲዎች ጋርም በተያያዘ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ በእቅድ ተይዟል? በአጠቃላይ “በሽታውን ያወቀ መድኃኒት ይገኝለታል” እንደሚባለው አሁን ላይ የዘርፉ ችግሮች ተለይተዋል ስለዚህ ለእነሱ የሚመጥን መፍትሔን የማፋጠንና ያለማፋጠን የትግበራ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሥራውን ወደኋላ የሚያሰኝ ነገር የለም።
ህብረተሰቡም ታሪፍ ሲጫንበት አገልግልት ሰጪው ሲያጉላላው መቃወምና ለሚመለከተው አካል ማመልከት በራሱም መብቱን ማስከበር መቻለ አለበት?ሌላው ደግሞ ህዝቡ የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎትን የመጠቀም ልምዱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያዳብር ይገባል፤ ይህንን ማድረግ ከቻልን ችግሩን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንፈታዋለን?ግን እንደ አገር የትራንስፖርት ችግር ባልተፈታበት ሁኔታ እድገት አለ ማለት ውሸት ነው?
አዲስ ዘመን፦ በጣም አመሰግናለሁ።
ኮማንደር አህመድ፦ እኔም አመሰግናለሁ
አዲስ ዘመን ጥቅምት 19/2012
እፀገነት አክሊሉ