ሱዳን እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ በአረቡ ዓለም ተቀጣጥሎ ከነበረው የሕዝባዊ ዐመጽ እንቅስቃሴ ተርፋ ዓመታትን ከተሻገረች በኋላ አምባገነን መሪዋን ከዙፋን ጠርጎ የጣለው የ38 ከተሞች ተቃውሞ አሁን ላይ እንዴት ተቀሰቀሰ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ለሱዳን ቀውስና የዐመጽ እንቅስቃሴ ግን ሁለት ዓይነት መንሥኤዎች ወይም ምክንያቶችን ማስቀመጥ ይቻላል። አንደኛው መሠረታዊ /Fundamental/ መንሥኤ የሚባለው ነው፤ ሌላው ደግሞ አሁናዊ / immediate / መንሥኤ የሚባለው ነው።
ለሱዳን ቀውስ መሰረታዊ ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ሲብላሉ የቆዩ ምክንያቶች አሉ። የአፍሪካ መንግሥታት ጉዳዮች ረዳት ሴክሬታሪ የነበሩት ሄርማን ጄ. ኮን ‹‹ The Roots of Sudan’s Upheaval›› በሚል ርእስ በጻፉት ትንታኔ እንዳመለከቱት፤ የመጀመሪያው ደቡብ ሱዳን ከሱዳን መገንጠሏን ተከትሎ ከነዳጅ ይገኝ የነበረው ገቢ መቀነሱ ዋነኛ ነበር። ደቡብ ሱዳን መገንጠሉ 75 ከመቶ ያህል የሆነውን የሱዳን የነዳጅ ገቢ አስቀርቶታል። ከአጠቃላይ ገቢዋም 46 በመቶ ያህል ቅናሽ አስከትሏል። የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶቹ /ሀብቱ/ በአብዛኛው በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ ስለነበር ኪሳራው መዘዝ አስከትሏል።
በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ጉዳዩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሚያስብለው ደግሞ የባለሥልጣናት ሌብነት መባባሱ መሆኑን ሄርማን ጄ. ኮን ጠቅሰዋል። የባለስልጣናት የሌብነት መስፋፋት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እያሳደረ ቆይቷል። የሱዳን ገዢ ኃይል ጥቅሞ ችን በፓርቲው አባላት፣ በጎሳና በተለያዩ የሀገ ሪቱ አካባቢዎች ካሉ ባልንጀሮቻቸው ጋር ተቀራ ምተው መቆየታቸውም የፖለቲካ ተንታኞች ትዝብት ነው።
ሌላው ፖለቲካዊ ምክንያት ሲሆን፣ በፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር መንግሥት ውስጥ የነበሩ ውስጣዊ ግጭቶች መንግሥቱን ሲገዘግዘው መቆየቱ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የዜጎችና የቡድኖች የመብት ጥያቄዎችም ሲብላሉ ቆይተዋል። የሃይማኖት ነጻነት፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የሠራተኞች በነጻነት የመደራጀት መብት የሲቪክ ማህበረሰቡ የመንቀሳቀስ መብቶች ታፍነው ለሦስት ዐሠርት ዓመታት በመኖራቸው መተንፈሻ ሲፈልጉ መቆየታቸው አሌ አይባልም።
አልበሽር ከቅኝ ግዛት ዘመን በኋላ ከነበሩ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ። ሀገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚመዘብሩ ሲነገርላቸው የነበሩት አልበ ሽርና ሸሪኮቻቸው በድህነት በሚሰቃዩ ብዙ ሱዳናውያን ዘንድ ቀን እየተጠበቀላቸው ነበር። በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ደረጃ አወጣጥ መሠረት በ2018 /እ.አ.አ/ ሱዳን በጸረ ሙስና ትግል ከ180 ሀገራት 172 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
አልበሽር ውጤት ባላገኙበት የደቡብ ሱዳን አማጽያንን በመዋጋት እንዲጠፋ የተደረገው የሰው ሕይወት፣ የባከነው ሀብት በብዙ ሱዳናውያን አእምሮ ውስጥ ጥቁር ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል። ያ፤ ሳይረሳ በዳርፉር አረባዊ ባልሆኑ ሱዳናውያን
ላይ የተፈጸመው ግፍ ከባድ ታሪካዊ ስህተት ሆኗል። በመቶ ሺሕዎች በሚቆጠሩ ላይ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሙ በአልበሽር መንግሥት ላይ ቂም የቋጠሩ ብዙ የሱዳን ዜጎች እንዲኖሩ ማድረጉ አያጠራጥርም።
ዴሞክራሲን ለሱዳናውያን ቅንጦት አድርገው ሲያስቡ የነበሩት አልበሽር በሚካሄዱ ምርጫዎች ሁሉ አሸናፊ የሚሆኑበትን የማጭ በርበር ድርጊት ያለይሉኝታ ሲፈጽሙ ቆይተዋል የሚለውም ሌላው ሲብላላ የቆየ ማኩረፊያ ነበር። ፍሪደም ሃውስ የተባለው ድርጅት እንደሚያብራራው አልበሽር ከ1989 /እ.አ.አ./ ጀምሮ በሥልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን፣ በምርጫ ሥርዐት ሥልጣናቸውን ለማስኬድ የጀመሩት ግን ከ2010 ጀምሮ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚህ መንገድ ለሁለት ዙር ተመራጭ ሆነው የቀጠሉ ሲሆን በ2015ቱ ምርጫ 94 ከመቶ ድምፅ እንዳገኙ ተቆጥሮ ያሸነፉ ሲሆን ዋናዎቹ ተፎካካሪዎች ከምርጫው ራሳቸውን አግልለው ነበር። በ2020 በሚካሄደው ምርጫም ተሳታፊ ሆነው የሥልጣናቸውን ጊዜ ለማራዘም ማቀዳቸው ታውቆ ስለነበር በርካታ ሱዳናውያንን አበሳጭቷል።
ሌላው የፖለቲካ ኃይል ቁጥጥሩ ከአረብኛ ተናጋሪ ልሂቃን በመለስ ሌሎችን ለማሳተፍ ያልተዘጋጀ ሆኖ መታየቱም ሌላው ራስ ምታት ሆኗል። ጥብቅ የሆነው ወታደራዊና የደህንነት መዋቅርም እነዚህን ጥያቄዎች በማፈን የዘለቀ ነበር። ደቡብ ሱዳን ከሱዳን መገንጠሏ በሱዳን ያለውን ማህበረሰብ አብዛኛው ክፍል ሙስሊም መሆኑ በጋራ በአንድ ሀገር ያቆየው እንጂ አረብኛ ተናጋሪ የፖለቲከ ልሂቃኑን ግን አናሳ ሆነው ከመቀጠል አላዳናቸውም።
ለሱዳን የዓመጽ እንቅስቃሴ መቀጣጠል የአልበሽር የውጭ ግንኙነት አለመሳካትም የሰጠው ጉልበት አለ። ከ1989/እ.አ.አ/ ጀምሮ እስላማዊ መንግሥት ሆኖ የተደራጀው የአልበሽር አስተዳደር በምዕራባውያን የተጽእኖ ጅራፍ መገረፍ ጀመረ። ሮይተርስ Residual U.S. sanctions keep Sudan’s economy in chokehold በሚል ርእስ በጻፈው ትንታኔ አልበሽር ለእስላማዊ አክራሪዎችና ሽብርተኞች ድጋፍ ያደርጋል የሚለው የአሜሪካና የተባባሪዎቿ ክስ ለአልበሽር መንግሥት አጣብቂኝ ፈጥሮበታል። አክራሪ እስላማዊ የመንግሥት ባለሥልጣኖቻቸው በርካታ አረባዊ ሙስሊሞች ወደ ሱዳን ገብተው እንዲሰሩና እንዲኖሩ የሚሰጡት ማበረታቻ ለአክራሪና ሽብርተኞች መፈልፈል አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል ምዕራባውያን አልጠፋቸውም።
ይህ ስጋት እንዳለ ሆኖ በአሜሪካ ዜጎችና ጥቅም ላይ በሱዳን የደረሱ ጉዳቶች ምእራባውያን ጥርስ እንዲነክሱ አድርጓቸዋል። ከዚያም አልፎ ኦሳማ ቢንላደንን አስጠልላ ነበር እስከመባል የደረሰችው ሱዳን ሰበብ እየተፈለገ ሀገሪቱን በኢኮኖሚ ማእቀብና መሪውንም በክስ ለማጣደፍ እነአሜሪካን አንቀሳቅሷቸዋል። የታሰበውም አልቀረ አልበሽር በዳርፉር ዘር ማጥፋት ክስ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ አወጣባቸው፤ ሀገሪቱም በኢኮኖሚ ማእቀብ ውስጥ ቆየች። ይህ ሁሉ በአልበሽር ይመራ ለነበረው የሱዳን መንግሥት ብዙ መዘዞች አስከትሏል።
አልጀዚራ ኤርትራ ወደ ሱዳን ድንበር ወታደሮቿን ያስጠጋችበትን የውጥረት ጊዜ በ2018 ላይ በተነተነበት ዘገባው በጎረቤት ግብጽ የነበረው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ያገኘውን የፖለቲካ የበላይነት በአልሲሲ መቀማቱና መሪው ሞሃመድ ሙርሲም ለእስር መዳረጋቸው ሱዳንን አላስደሰታትም ነበር። ለዚህ የወሰደችው የአጸፋ እርምጃ የሙስሊም ወንድማማቾችን እንቅስቃሴ ለምትደግፈው የግብጽ ባላንጣ ለሆነችው ቱርክ በቀይ ባህር የምትገኘውን ሱአኪም ደሴትን በሊዝ መስጠቷ ከግብጽ ጥርስ ውስጥ አስገብቷታል። ምንም እንኳን አልበሽር በየመን ጦርነት ውስጥ ሀገራቸው ከሳውዲ ጎን በመሰለፏ ግብጽ ጫናዋን ብታቀልም የሱዳን መንግሥትን ስትገዘግዝ መቆየቷ ግን አይካድም። በኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይም ለኢትዮጵያ ያደላ አቋም ማራመዷ ግብጽን አላስደሰተም።
ከኤርትራም በኩል ከሙስሊም ወንድማ ማቾች ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውን እና በቱርክ ጽሕፈት ቤት ከፍቶ የሚንቀሳቀሰውን የኤርትራ ሙስሊሞች ሊግ ለምትደግፈው ቱርክ ሱአኪምን መስጠቷ ከጎረቤቷ ኤርትራም ቁጣ ማምጣቱ አልቀረም። ሱዳን ከኢትዮጵ መንግሥት ጋር በነበራት ግንኙነት ሲበሳጭ ለነበረው የኤርትራ መንግሥት ይሄ የቱርክ አፍን ጫው ላይ መምጣት አልጣመውም፤ ስለዚህም ከሱዳን የሚያጎራብተውን ድንበር አንዴ ሲዘጋ ሌላ ጊዜ ሲከፍት ታይቷል። ስለዚህም ከግብጽ ጋር በመወዳጀት በአልበሽር ላይ ሲያሴር ቆይ ቷል። በኋላ ደግሞ በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ለኤርትራ ሰላም የሚሰጥ ሆኖ መከሰቱ በአልበሽር ይመራ ለነበረው ለሱዳን ገዢ ኃይል የሞት ሞት ነበር።
እነዚህና መሰል የተብላሉ ገፊ ምክንያቶች ለሱዳን ተቃዋሚዎች የልብ ልብ የሰጡ፣ ለአልበ ሽር አመራር በየጊዜው መላሸቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ነበሩ። እነዚህን የተዳፈኑ ብዙ እሳቶች የቆሰቆሰው ግን ምን ነበር የሚለውን እንመ ልከት።
የሱዳን ዐመጽ አሁናዊ ምክንያት
የሱዳን ዐመጽ ተሟሙቆ እንዲቀጣጠል ወሳኝ ሚና የተጫወተው በሀገሪቱ ዜጎች ሊቋ ቋሙት ያልቻሉት የዋጋ ንረት መከሰቱ ነው። ይሄንን የዋጋ ንረት እንዲወለድ ያደረጉት ከላይ የጠቀስናቸው የተብላሉ እና ውስብስብ የሆኑ የኢኮኖሚና የፖለቲካ አዳካሚ ምክንያቶች ናቸው። የሱዳን የነዳጅ ገቢ መውደቁ ምን ያህል ጉዳት እንዳስከተለ አስቀድመን የዳሰስነው ነው።
አሜሪካ በሱዳን ላይ ጥላው የነበረው የኢኮኖሚ፣ የጉዞ ማእቀብ በሱዳን ቴክኖሎጂያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ላይ ሳይቀር ጫናው ከባድ ነበር። የእንቅስቃሴ ገደቡም የትምህርትና ሥልጠና የክህሎት ልውውጡን ያወከው በመሆኑ በተራዛሚ ሱዳንን የኢኮኖሚ ልማት መቶታል።
በዩናትድ ኪንግደም ኢሴክስ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ጥናቶች ዓለም አቀፍ ተቋም ተመራማሪ የሆኑት አንድሪው ኤድዋርድ ቲ. / Andrew Edward T./ ባቀረቡት ትንታኔ እንዳመለከቱት የዓለም የገንዘብ ድርጅት ሱዳን ዕዳዋን ማቃለል የምትችልበት እድል የምታገኘው በምንዛሪ ተመኗ ላይ ማሻሻያ ስታደርግ መሆኑን በማመን ባሳደረው ግፊት የምንዛሪ ተመኑ የሱዳንን ገንዘብ ማራከሱ ከፍተኛ የዋጋ ንረት በሀገሪቱ እንዲቀጣጠል አደረገ። የሱዳንን የዋጋ ንረት ምጣኔ 70 ከመቶ እንዲደርስ አድርጎታል። በዚህ ምክንያት የሱዳን መንግሥት ድጎማ ያደርግላቸው ከነበሩ አቅርቦቶች ላይ ሁሉ ድጎማውን ሲያነሣ የዋጋ ንረቱ ለነዋሪው ክፉኛ ጉዳት አስከትሏል። በተለይ የዳቦ ዋጋ በአጭር ጊዜ በእጥፍ መጨመሩ ዕለት ዕለት ፍጆታው ላይ የመጣ ቀውስ በመሆኑ ሕዝብ ሊታገስ አልቻ ለም። እንደ አልጀዚራ ዘገባ
ዘመን መፅሔት መስከረም 2012
ማለደ ዋስይሁን