የፌዴራል ስነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን የ21ሺ 363 ሹመኞች፣ ተመራጮችና መንግስት ሰራተኞችን ሀብት መዝግቧል፤ ለ256 መረጃ ፈላጊዎች የሃብት ምዝገባ መረጃ ሰጥቷል፤ የ485 ከፍተኛ አመራሮችን የሃብት ምዝገባ እድሳት አደረገ ፡፡
የፌዴራል ሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በ2011 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም እና የ2011 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡ በመድረኩ እንደተገለጸውም ኮሚሽኑ በሃብት ማስመዝገብ፣ ማደስና ማሳወቅ ረገድ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው ሙስናን ለመከላከል ከተቀመጡ ስልቶች መካከል አንዱ ተመራጮች፣ ተሻሚዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ሀብትና ጥቅማቸውን እንዲያሳውቁ እና እንዲያስመዘግቡ ማድረግ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ሀብት ማስመዘገብ ያለባቸው ሁሉንም የስራ ሃላፊዎች ለመመዝገብ ታቅዶ 21ሺ363 ሀብታቸውን አስመዝግበዋል እንዲሁም የሀብት ምዝገባ መረጃን እንዲሰጣቸው በጽሑፍ ጥያቄ ላቀረቡ ለ256 መረጃ ፈላጊዎች መረጃው እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
ሀብታቸውን ማሳደስ ከሚገባቸው የሀብት አስመዝገቢዎች መካከል የከፍተኛ አመራሮችን የሐብት ምዝገባ ዕድሳት ለማካሄድ ታቅዶ 485 አስመዝግበዋል እንዲሀም የ400 ሀብት አስመዝጋቢዎችን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ በማንዋሉ መሰረት ዝግጁ ተደርገዋል።
የ80 ሀብት አስመዝገቢዎች የሀብት ምዝገባ መረጃ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ ታቅዶ 23 የተጠናቀቁ ሲሆን 59 በሂደት ላይ ይገኛሉ።
በሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዙሪያ ለ2000 ሰልጣኞች የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ3913 ግንዛቤ ተሰጥቷል። የሚመዘገቡትን የምዝገባ መረጃዎች በሙሉ (14711) በመረጃ አደረጃጀት ማኑዋል መሰረት በየተቋማቱ በመለየትና በሃርድ እና በሶፍት ኮፒ በማደራጀት ለተደራሽነት ዝግጁ ለማድረግ ታቅዶ የ12, 832 አስመዝጋቢዎች በሙሉ ዝግጁ ተደርገዋል።
የጥቅም ግጭት አስተዳደር የሕግ ማዕቀፍ ለማሟላት ጥናት ማካሄድ የህግ ረቂቅ እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በፌደራልና በክልሎች ደረጃ ወጥ የሆነ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል አንድ የሚያሰራ ሰነድ ለማዘጋጀት ታቅዶ ተከናውናል።
ከዚህ በተጓዳኝ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻያ ስራ ያከናወነ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የሃብትና ጥቅም ማስመዝገብ አዋጅ እና የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ደንብ ማሻሻያ፣ የከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የስነምግባር ደንብ ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡ በዕለቱ መድረክም የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
አዲስ ዘመን ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም
በወንድወሰን ሽመልስ