‹‹ሴቭ ዘ ቺልድረን (Save the Children)›› የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ 85ሺ ሕፃናት በረሃብ እንደሞቱ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው መረጃ አመልክቷል፡፡ በሪፖርቱ የተካተቱት ጊዜያትም እ.አ.አ ከሚያዚያ 2015 እስከ ጥቅምት 2018 ድረስ ያሉት ዓመታት ናቸው፡፡ የድርጅቱ የየመን ዳይሬክተር ታመር ኪሮሎስ፣ 85ሺ ሕፃናትን ማጣት እጅግ አስደንጋጭ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ወላጆች አማራጭ ስለሌላቸው የልጆቻቸውን ሞት እያዩ ዝም ከማለት ውጭ ምንም ማድረግ አለመቻላቸው ደግሞ የበለጠ ያሳዝናል›› ብለዋል፡፡
የሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጥምር ጦር በሐውቲ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመረበት እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2015 ጀምሮ በሁዴይዳ ወደብ በኩል ወደ የመን የሚገባውና ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕፃናትን ጨምሮ ለአራት ነጥብ አራት ሚሊዮን የመናውያን በቂ የነበረው 55ሺ ቶን ወርሃዊ የምግብ ሸቀጦች አቅርቦት በከፍተኛ መጠን ቀንሷል፡፡
የዓለም የምግብ መርሃ ግብር (World Food Program – WFP) በበኩሉ በአሁኑ ወቅት 14 ሚሊዮን የመናውያን የረሃብ አደጋ እንደተጋረጠባ ቸው አስታውቋል፡፡ በሁዴይዳ በኩል የሚገባው የምግብ ሸቀጥና አቅርቦት ከዚህ በበለጠ ከቀነሰ አሁን ካለው የባሰ አስከፊ አደጋ እንደሚፈጠርም አስጠንቅቋል፡፡
ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዋ ከፍ ያለ እንደሆነ የሚነገርላትን የሁዴይዳ ወደብን ለመያዝ በሳዑዲና ኤምሬቶቹ ጥምር ጦር በሚደገፉት የፕሬዚዳንት አብድ-ራቡ መንሱር ሃዲ ታማኞች እና በሐውቲ ታጣቂዎች መካከል የተጋጋለ ውጊያ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ይፋ የተደረገው ሪፖርት፣ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ክፉኛ አስደንግጧል፡፡
ድርጅቱ ባለፈው መስከረም ወር ይፋ ባደረገው ሪፖርትም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የየመን ሕፃናት የረሀብ አደጋ እንደተጋረጠባቸው ገልፆ ነበር፡፡ በወቅቱም ሁዴይዳ ወደብ ላይ የሚደረገው ውጊያ የሚያስከትለው መዘዝ አንድ ሙሉ የየመንን ትውልድ ሊያጠፋ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር፡፡
እስካለፈው መስከረም ወር በተደረገ ጥናት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በ68 በመቶ፣ የነዳጅ ዋጋ ደግሞ በ25 በመቶ ጨምሯል፡፡ የአገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ የመግዛት አቅሙ በ180 በመቶ ተዳክሟል፡፡ ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ መካከል ከሁለት ሦስተኛው (ከ64 በመቶ) በላይ የሚሆነው የእለት ጉርሱ ምንጭ ምን እንደሆነ እንኳ አያውቅም፡፡ 28 ሚሊዮን ከሚሆነው የአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ መካከል 22 ሚሊዮን ያህሉ (78 ነጥብ አምስት በመቶ) ሕዝብ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ መካከል 11 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ ሕፃናት ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየመን ልዩ መልዕከተኛ ማርቲን ግሪፊዝ፣ ተፋላሚ ኃይሎችን የማደራደር ጥረታቸውን ለመቀጠል ሰንዓ ገብተዋል፡፡ ባለፈው መስከረም ወር ጀምረውት የነበረው የሰላም ድርድር ሳይሳካላቸው የቀረው ልዩ መልዕክተኛው ‹‹ተፋላሚ ኃይሎቹ የሰላም ድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ እንደሚሆኑ እምነት አለኝ›› ብለዋል፡፡ ድርድሩም የአውሮፓውያኑ 2018 ከማለቁ በፊት በስዊድን እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
ልዩ መልዕክተኛው ባለፈው መስከረም ወር ጀምረውት የነበረው የሰላም ድርድር ሳይሳካ መቅረቱ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ከሐውቲ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ የሚገኙት ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የታጣቂዎቹ ይዞታ ወደሆነችው የሁደይዳ ወደብ በመግፋት የማጥቃት ዘመቻቸውን ማጠናከራቸውና የሐውቲ ታጣቂዎች ‹‹በጥቃቱ ምክንያት በድርድሩ ላይ መሳተፍ አልቻልንም›› ብለው ከድርድሩ መቅረታቸው የታቀደው ሰላም ድርድር እንዳይሳካ በምክንያትነት ተጠቅመው እንደነበር ይታወሳል፡፡
በርካታ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተንታኞች የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት የአገሪቱን ሕፃናት በማጥፋት የትውልድ ክፍተት እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ስጋታቸውን በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡
የየመን ፖለቲካዊ ቀውስ
እ.አ.አ በ2015 የየመን የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሊ አብዱላህ ሳሌህ ታማኞች ከሐውቲ ታጣቂዎች ጋር አብረው በፕሬዚዳንት አብዱ ራቡ መንሱር አል-ሃዲ ኃይሎች ላይ ጥቃት ጀመሩ፡፡ ባለፈው ታህሳሥ ወር የተገደሉት የቀድሞው የየመን ፕሬዚዳንት የአሊ አብዱላ ሳሌህ ደጋፊዎችና የሐውቲ ታጣቂዎችም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የየመንን ሰፊ ግዛት በቁጥጥራቸው ስር አደረጉ፡፡ የመንሱር ሃዲ መንግሥትም መቀመጫውን ከሰነዓ ወደ ኤደን አዛወረ፡፡ ቀጥሎም የሐውቲ ታጣቂዎች የመንሱር ሃዲን መንግሥት ለመገልበጥ እቅድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ወደ ኤደን ሲጠጉ መንሱር ሃዲ ሀገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላም በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የተለያዩ ሀገራት ጥምር ጦር የመንሱር ሃዲን መንግሥት ወደ መንበሩ ለመመለስ በሐውቲ ታጣቂዎችና በሳሌህ ታማኞች ላይ የአየር ጥቃት መፈፀም ጀመረ፡፡ ሳዑዲ መራሹ የአየር ጥቃትም በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እየጨመረ ሲመጣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጥምር ጦሩን ጥቃት ክፉኛ አወገዘው፡፡
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ጦር በሐውቲ ታጣቂዎች ይዞታዎችና ንብረቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም የሀገሪቱን ዋና ከተማ ሰነዓን ለመቆጣጠር ለሚደረገው ፍልሚያ በር ማስከፈት እንዳልቻለ ይገለፃል፡፡ በየመን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጀርባ የመካከለኛው ምስራቅን ፖለቲካ በበላይነት ለመቆጣጠር የሚሽቀዳደሙት የሳዑዲ አረቢያና የኢራን እንዲሁም ወሳኝ ጂኦ-ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለውን ይህን ቀጠና በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ምንጊዜም ቢሆን የማይተኙት የምዕራባውያን ሀገራት እጅ እንዳለበት ተደጋግሞ ይገለፃል፡፡ በእርግጥ ሳዑዲ አረቢያ ሀገር ጥለው የተሰደዱትን የመንሱር አል-ሃዲን ታማኞች ደግፋ በጦርነቱ መሳተፏና ሐውቲዎች የሺኣ እስልምና ተከታይ ናቸው መባሉ ሺአዋ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ በየመኑ ጦርነት እጃቸውን ስለማስገባታቸው እንደዋነኛ ማሳያ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡
ኢራን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አብደላ ሳሌህን ታማኞችና የሐውቲ ታጣቂዎችን እንደምትረዳ ተደጋግሞ ቢነገርም ሀገሪቱ ግን ይህን መረጃ በተደጋጋሚ ስታጣጥለውና ‹‹የሳዑዲ አረቢያና አጋሮቿ ውንጀላ ነው›› በማለት ስትደመጥ ተስተውላለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ከፍተኛ ጂኦ-ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለውን የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናን ለመቆጣጠር ለአፍታ ያህል የማይዘናጉት ምዕራባውያን በበኩላቸው በሳዑዲ አረቢያ ለሚመራው ጥምር ጦር የሎጂስቲክና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተለይ አሜሪካ ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ኢራንን ለማንበርከክ ያላት ፍላጎት በየመን በየዕለቱ የሚቀጠፈውን የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ችላ እንዲባል አድርጎታል፡፡
በየመን ለበርካታ ዓመታት ስር ሰደው የቆዩ ችግሮች የሀገሪቱን ቀውስ ከድጡ ወደ ማጡ አድርገውታል፡፡ በየመን ሰፊ ይዞታ እንዳለው የሚነገርለት ዓለም አቀፉ አሸባሪ ቡድን አልቃይዳ የየመናውያንን ሰቆቃ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ካደረገው ቆይቷል፡፡ ራሱን እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ብሎ የሚጠራው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድንም በአካባቢው ያለውን ይዞታውን ለማስፋት እንደመሸጋገሪያና መቆያ ከሚጠቀምባቸው የአካባቢው ሀገራት መካከል የመን አንዷ ናት፡፡ የንፁሃንን አንገት መቅላት የየዕለት ተግባሩ የሆነው ይህ አረመኔ ቡድን የአየር ጥቃት ለሚያሰቃያቸው የመናውያን ሌላ የሕልውና አደጋ ሆኖባቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም፣ ሀገሪቱ በነዚህ ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖች፣ በሐውቲዎች እና በመንሱር አል-ሃዲ ታማኞች ቁጥጥር ስር ተከፋፍላ ትገኛለች፡፡ የሀገሪቱ ዋና ከተማ ሰነዓ በሐውቲዎች ቁጥጥር ስር ትገኛለች፡፡
ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በየመን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመሩ ወዲህ ከ10ሺ የሚበልጡ ሰዎች እንደተገደሉና (ከነዚህም መካከል ከ60 በመቶ የሚበልጡት ሰላማዊ ዜጎች እንደሆኑና ከዚህ የሚበልጡ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ አካላት በየጊዜው ይፋ የሚደረገው የሟቾቹና የቁስለኞቹ ቁጥር የተለያየ ነው፡፡
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትንና እ.አ.አ በ2014 በሐውቲ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የወደቀችውን የሁዴይዳ ወደብን ለመያዝ የሚደረገው የተፋፋመ ውጊያ 600 ሺ ከሚሆኑት የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ከ120ሺ የሚበልጡትን ለስደት እንደዳረገ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ይፋ ያደረጉት መረጃ ያሳያል፡፡
የ‹‹ዘ ዋሺንግተን ፖስት›› ዘገባ እንደሚያመለ ክተው፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወታደሮች ከሁዴይዳ ወደብ ከ15 ኪሎ ሜትሮች ባነሰ ርቀት ላይ ይገኛሉ፡፡ በልዕለ ኃያላኗ አሜሪካ የትጥቅ ድጋፍ የሚደረግለት የሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጥምር ኃይል በየመን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ ከ16ሺ በላይ የአየር ጥቃቶችን ፈፅሟል፡፡
በእርስ በእርስ ጦርነት በምትታመሰውና ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል በድህነት የሚወዳደራት የለም በምትባለው የመን እየተካሄደ የሚገኘው የእርስ በእርስ ጦርነት ያስከተለው ረሀብና በሽታ የሀገሪቱን ዜጎች ስቃይና መከራ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎባቸዋል፡፡
በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንና የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየመን ያለውን አስከፊ ቀውስ ችላ ብሎታል በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳቸውን አሰምተዋል፡፡ ለዚህም ነው የመገናኛ ብዙኃኑና የፖለቲካ ተንታኞቹ የየመኑን ፖለቲካዊ ቀውስ ‹‹የተረሳው/የተዘነጋው ጦርነት (The Forgotten War)›› የሚል ስያሜ የሰጡት፡፡
(የመረጃው ምንጮች ፡ ‹‹አልጀዚራ››
እና ‹‹ቢቢሲ››)
ትውልዷን የተነጠቀችው የመን