የኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ አሰራጨ

አዲስ አበባ፡- የኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማሰራጨቱን አስታወቀ፡፡ 803 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለስርጭት መዘጋጀቱንም አመለከተ፡፡

በቢሮው የግብርና ግብዓት ፍላጎትና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ታከለ ቁሩንዴ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ በክልሉ አዲስ የገባውን እና ከባለፈው ዓመት የተረፈውን ማዳበሪያ ጨምሮ ስድስት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ይገኛል፡፡ ከእዚህ ውስጥ እስካሁን ለመኸር ምርት ዘመን አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልጸዋል፡፡

ለምርት ዘመኑ እንደ ክልል 10ነጥብ አምስት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ የታቀደ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ታከለ፤ እስካሁንም አምስት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልል ለማስገባት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

አዲስ የገባውን እና ከባለፈው ዓመት ካደረው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ጋር እንደ ክልል ስድስት ነጥብ አንድ ኩንታል ማዳበሪያ ለማሰራጫ ጣቢያዎች መቅረባቸውንም ገልጸዋል።

ጣቢያዎች ከቀረበው ማዳበሪያ ሁለት ነጥብ አንድ ኩንታሉ ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ያሉት አቶ ታከለ፤ ከእዚህም 592 ሺህ ኩንታል ለበልግ፤ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ለመኸር እርሻ የሚውል ነው፤ የተቀረው ለመስኖ እርሻ የተሰራጭ ነው ብለዋል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት የአፈር ማዳበሪያን በጊዜ ከማዳረስ አንጻር የሚነሱ ቅሬታዎች እንደነበሩ ያነሱት አቶ ታከለ፤ ይህን ችግር ለመፍታት ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚሆን ማዳበሪያ በጊዜ ወደ ክልሉ እንዲገባ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ወደ ክልል ከገባ በኋላም በጊዜ አርሶ አደሩ እጅ ላይ እንዲደርስ ቀደም ብሎ ከማህበራት ጋር ውይይት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው፤ ዘንድሮ ከማሰራጨት አንጻር የተሻለ አፈጻጸም እንዳለ አመልክተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፤ በምርት ዘመኑየኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ አሰራጨ

ለሦስቱም የዘር ወቅቶች እንደ አጠቃላይ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ምርጥ ዘር ለማሰራጨት የታቀደ ሲሆን፤ ለመኸር እርሻ 803 ሺህ ኩንታል የተለያዩ የዘር ዓይነቶች ተዘጋጅተዋል፡፡

የበቆሎ ዘር የመደልደል ሥራ ቀደም ብሎ መጀመሩን፤ 139 ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዘር ለዞኖች መደልደሉን፤ 102 ሺህ ኩንታል ከዘር ጣቢያዎች ወደ ክልሎች መላኩን፤ በአጠቃላይ ከተላከው የምርጥ ዘር 78 ሺህ ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር አርሶ አደሩ ጋር መድረሱን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በመኸር ወቅት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጥራጥሬ እና የዘይት እህሎች በዋናነት እንደሚዘሩ የገለጹት አቶ ታከለ፤ ከበቆሎ ውጪ ያሉ የምርጥ ዘር ዓይነቶች ለዞኖች እየተደለደሉ ነው፤ በቀጣይ ጊዚያትም የማሰራጨቱ ሥራ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

አርሶ አደሩ ወደ ኅብረት ሥራ ማህበራት የደረሰውን የአፈር ማደበሪያ በጊዜ ገዝቶ ሊጠቀም ይገባል ያሉት አቶ ታከለ፤ ከዘር ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ ምርት ሊያቀርቡ የሚችሉ ሊኖሩ ስለሚችሉ ከታወቀ የምርጥ ዘር ጣቢያ የቀረበ ዘር መሆኑን አረጋግጠው እንዲገዙ ለአርሶ አደሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዓመለወርቅ ከበደ

አዲስ ዘመን ሐሙስ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

 

Recommended For You