ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳን የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው ላለፉት ሁለት ዓመታት ማገልገላቸው ይታወሳል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው ላበረከቱት፣ በተለይም የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌዴራል መንግሥት እውቅና እንደሚሰጣቸው ማስተወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You