እንዳታካትቱ

“እንቅፋት ደግሞ ከመታህ ድንጋዩ አንተ እንጂ እሱ አይደለም፤ እኔም ሁለት ጊዜ የደቆሰኝ ፍቅር በሦስተኛው በረከቱ ተርፎኛል” ይላሉ የዛሬው የልዩ ልዩ ዓምድ ይዞት ብቅ ያለው እንግዳ። “ፍቅር ይገለዋል መቼም የጎጃም ሰው” የሚለውን የኤፍሬም ታምሩን ዘፈን በትዝታ ፉጨት እያንጎራጎሩ።

ይነስም ይብዛም እያንዳንዱ ሰው መጽሐፍ ነውና ገጸ ሕይወታቸውን አብረን እንገልጠው ዘንድ ከሥነ ጽሑፍ ወደብ የብዕር መልሕቄን ጥያለሁና ጥበባዊ ግብዣዬን እነሆ።

ካባታቸው ባይለየኝ ቢሻውና ከእናታቸው እህትአገኘሁ መሰል 1981 ዓ.ም ታኅሣሥ 30 በምሥራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ የምትገኘው የደማን ገጠራማዋ ቀበሌ የከተማ ባይለየኝን እትብት ተቀበለች። ዓይናማ በነበሩባቸው ዓመታት የመንደር ጥጆችን እያገዱ “በመኪናው መንገድ በኮረሪማው፣

አንቺን ተከትዬ ይብላኝ አሞራው።” ሲሉ ያዜሙለትን መኪና ያወቁት ዓይነስውር ከሆኑ በኋላ ነው። ታዲያ አንድ ጊዜ ለዓይን ሕክምና ከማርቆስ አዲስ አበባ እየተጓዙ ሳለ መኪናው ሲቆም “እሾህ ወግቶት ነው አልሄድ ያለው?” ብለው አባታቸውን ሲጠይቁ የሰማ ተሳፋሪ ሲስቅባቸው ፀሐይ እንዳጠወለገው ቅጠል ኩምሽሽ አሉ። ይህም በተማሪነታቸው ዘመን ክፍል ውስጥ ያልገባቸውን እንዳይጠይቁና ለሥራ በቅተው እንኳን በስብሰባ መድረኮችም ሃሳብ እንዳይሰጡ የሥነልቦና እክል ሆኖባቸው እንደነበር አጫወቱኝ የልጅነታቸውን ምዕራፍ እያስነበቡኝ።

በውሃ ፍልቀት መንስኤነት ብርሃናቸውን ያጡት አቶ ከተማ ዘነበወርቅ ሆስፒታል ዓይናቸው እንደማይድን ነገር ግን ዓይነስውራን ትምህርት ቤት መግባት እንደሚችሉ ሲነግራቸው አባታቸው “እንዴት ተደርጎ?” አሉና ወደቀያቸው ይዘዋቸው ተመለሱ። ለምን እንቢ አሉ? ስል ጥያቄ አነሳሁላቸው። “ለመለመኛ ሊሰረቅ ይችላል፤ ለመንግሥት አንድ ጊዜ ፈርሜ ከሰጠሁ በኋላ ልጄን ዳግመኛ ባላየውስ?” በሚል የተሳሳተ አመለካከት ከቤተክህነቱም ካስኳላውም ትምህርት አራቀኝ” ሲሉ አስረዱኝ፤ ይሁን እንጂ እንደዕኩዮቻቸው እየሮጡ ሲጫወቱ ወድቀው እጃቸው ተሰበረና ቤተዘመዱም ጎረቤቱም ሲወቅሳቸው ከዘመዳቸው መሪጌታ ምንተስኖት ፈንታ ዘንድ ለቄስ ትምህርት ደብረ ኤልያስ አደረሷቸው። ከስምንት ወር ቆይታ በኋላ የእናታቸው አጎት ለዘመድ ጥየቃ በመጡበት አጋጣሚ ሁኔታውን ተገንዝበው አዲስ አበባ አመጧቸውና 1989 ዓ.ም ሰበታ መርሐ ዕውራን ትምህርት ቤት አስገቧቸው። እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ የነበረውን ቆይታ ጨረሱና በሰበታ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ቀሪ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ በ2001 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ተቀላቀሉ።

ይሁን እንጂ ገና በገቡ ማግስት ሻንጣ ሙሉ እቃቸው በመዘረፉና የመረጡት ፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ሳይመደቡ በመቅረቱ ደስታቸውን አደበዘዘው፤ ቢሆንም ግን ከስንት ሙግት በኋላ የጠፋ ሻንጣቸውን ባይመልሱትም የሚፈልጉትን የትምህርት ዓይነት አገኙና የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርትን ከነፍስያቸው ጋር ማዋሓድ ጀመሩ። የሆነው ሆኖ አንድ ዓመት አስቆጠሩና ወደሁለተኛው ሲሻገሩ 11ኛ ክፍል የጎበኛቸው ፍቅር እዚህም ደገማቸው። አጋጣሚው እንዴት ነበር? አልኳቸው የትዝታቸውን ማኅደር ወለል አድርገው እንዲያሳዩኝ በመሻት። “ሁለቱም የክፍል ጓደኞቼ ሲሆኑ በድምፃቸው እጅጉን ተማርኬ ፍቅር ቢጥልብኝም በወቅቱ በቂ የብሬል መጽሐፍት ባለመኖሩ ምክንያት አንድም ድጋፋቸውን እንዳላጣ ሰግቼ ሁለትም እንቢ ብትለኝስ በሚል ፍርሃት የልቤን ስቃይ እንደሸሸኩት ተለያየን” አሉ ከናፍቆት ሰማይ ስር በንስር ከፍታ እየበረሩ።

በእንዲህ መልኩ ተመረቁና ተማሪነት ቀርቶ አቶነት ሲተካ የሥራው ዓለምም በቅጥር ፍለጋ የኑሮ ፈተናው አሐዱ ሲል “ሕይወት እንደዚህ ናት?” ማለታቸው አልቀረም፤ ከነሱ በፊት የነበረው የአካል ጉዳተኞች ቀጥተኛ ምደባ በመቅረቱ ለእንግልት ተዳረጉ፤ ከብዙ መንከራተት በኋላ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ለትውልድ ቀያቸው ስናን ወረዳ ጻፈላቸውና በሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እቅድና የሰው ሀብት ልማት ባለሙያ ሆነው ተመደቡ።

ካባ ደርበው ወንበር ላይ ሲሰየሙ ያርባ ቀን ዕድላቸውን የረገሙ ወላጆቻቸው ሳይቀሩ ያገሩ ሰው ድንጋይ ተሸክሞ ምሕረት ለመናቸው፤ እሳቸውም “ስህተታችሁ የመጣው ካለማወቅ ነውና እኔን አይታችሁ ዓይነስውር ልጆቻችሁን ወደትምህርት ገበታ ውሰዷቸው” በማለት ምክር ለገሷቸው።

የሥራ አካባቢያቸው ምቹ ካለመሆኑ የተነሳ ከስናን አዲስ አበባ በመምጣት ሲወዳደሩ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ያካቶ ትምህርት ሥልጠና ባለሙያ ሆነው ለመቀጠር በቁ፤ ከዚህ በኋላም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ንቅናቄና የሲቪል ማኅበራትን ማጠናከር ኦፊሰር፣ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የከተሞች ምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት ጽሕፈት ቤት የሴፍቲኔት ባለሙያ እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተመሳሳይ መደብ በሀብት ማሰባሰብ ባለሙያነት በዝውውርም በዕድገትም ለመሥራት ችለዋል፤

በዚህ ሰዓት በኢትዮጵያ ዓይነስውራን ብሔራዊ ማኅበር የመምህራን ያካቶ ትምህርት ሥልጠና አስተባባሪ ሆነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

ጥሩም ይሁን መጥፎ የሥራ ገጠመኝ እንዳላቸው ያጫውቱኝ ዘንድ በጠየኳቸው ጊዜ ይህን አካፈሉኝ። ፈገግታን የሚጭረው ገጠመኛቸው የተከሰተው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሳሉ ነው። ያዘጋጁትን ደብዳቤ ረዳት ጸሐፊያቸው እንድታርመው ቢነግሯትም እሷ ግን በኮምፒውተር ችሎታቸው በመተማመንና በተደጋጋሚ ቀናት ስታይ ስህተት ስላላገኘችባቸው የሰጧትን ጽሑፍ ፕሪንት አድርጋ ለአቻ ጽሕፈት ቤቶች አሰራጨችው፤ ታዲያ የተበተነው ደብዳቤ ከኃላፊዎች እጅ ደርሶ ኖሮ መሥሪያ ቤቱ ውስጥ አቧራ አስነሳ። “የሥርዓተ ፆታን ጉዳይ በእቅዳችሁ ውስጥ እንድታካትቱ ስለመጠየቅ” እላለሁ ብለው ፊደል ገደፉና “እንዳታካትቱ” ሆነባቸው፤ ይህን ሲያወሩኝ ከጭልፊት ያመለጠች ጫጩት ይመስሉ ነበር።

አቶ ከተማ ሲዳ የተሰኘው ግብረሠናይ ድርጅት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ከስዊዲን መንግሥት ጋር በመቀናጀት ለአካል ጉዳተኞችና ሴቶች የሚሰጠውን ስኮላር አግኝተው በልዩ ፍላጎት (ስፔሻል ኒድ) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተማሩ ሲሆኑ ዛሬ ላይ ከባለቤታቸው አታላይ አብዩ ጋር ጉልቻ መሥርተው የሁለት ልጆች አባት ሆነዋል።

የስልክ ልውውጥ በኋላ አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ይዛው የነበረውን አቋም ማለዘቧ ሲሰማ በቀጣይ ሁለቱ መሪዎች ጦርነቱን ለመግታት ተጨማሪ ንግግሮች እንደሚያስፈልጉ መስማማታቸው ተሰምቷል:: ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ እለት ጅዳ የተገኙት የአሜሪካው ልዑካን የዩክሬን ባለሥልጣናት በፍጥነት ተግባራዊ የሚደረግ ያሉትን የሠላሳ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈርሙ ማሳመናቸው ይታወቃል::

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ዘለንስኪ ለኦፊሻላዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ፊንላንድ መዲና ሄልሲንኪ ያቀኑ ሲሆን ዩክሬን የኃይል አማራጮችን ያካተተ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረው ሆኖም ግን ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚፈልጉ ተናግረዋል:: እንደዚሁም ከሰሞኑ በዩክሬን ላይ የበረታ የአየር ላይ ጥቃት እያደረሱ ያሉት የሩሲያ ወታደሮች ፑቲን የተኩስ አቁም ስምምነት ያለመፈለጉ ምልክት ነው ሲሉ መውቀሳቸው ይታወሳል::

ከሰሞኑ ሩሲያ ባካሄደችው የድሮን ጥቃት ዒላማ ከተደረጉት መካከል ሱሚ የሚገኝ ሆስፒታል እና በስሎቭያንስክ የሚገኙ የኃይል ማመንጫዎች

ሃብታሙ ባንታየሁ

አዲስ ዘመን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You