“ከተማዋን የሚመጥን የአደጋ መከላከል ተቋም ተቋቁሟል ወይ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል” ኮማንደር አሕመድ መሀመድ – የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አደጋን ቀድሞ መከላከል፤ ከደረሰም አደጋውን የመቆጣጠር እና የመልሶ ማቋቋም ሥራ የሚሰራ ተቋም ነው። አሁን ያለንበት ወቅት የጸሀዩ ሙቀት እየበረታ የመጣ እንደመሆኑና ነፋሱም በዚያው ልክ እየነፈሰ በመሆኑ የእሳት አደጋ ሊነሳ ይችላል ተብሎ የሚገመትበት ነው። ከዚህ አኳያ የዝግጅት ክፍላችን፤ ኮሚሽኑ አደጋን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ዘመኑ የሚጠይቀውን አቅም ገንብቷል? መዲናይቱ የመልሶ ግንባታ ላይ እንደመሆኗ በግንባታ ወቅት የደህንነት መስፈርቶች መተግበራቸው በምን መልኩ እየተቆጣጠረ ይገኛል? የደህንነት መስፈርት በማያሟሉት ላይ ምን አይነት ርምጃ እየተወሰደ ነው? በሚሉ እና መሰል የተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሀመድ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በመደመር ዕሳቤ ያለፉ ወረቶቻችን ለዛሬ መሠረቶቻችን ናቸው በሚል አቅጣጫ ቅርሶችን ከመፍራት ወደ ማፍራት የተሸጋገርንበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ ያለፉት እሴቶቻችንን በዛሬ ላይ በማከል የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን የጋራ ግብ እና የጋራ ሕልም ያለን ሕዝቦች ነን፡፡

ይህንኑ መነሻ በማድረግ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ግንባታዎች በስፋት በማከናወንና ነባር ቅርሶችን በማደስ ለቱሪዝም ዘርፉ መጠናከር የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ሀገርም ኢኮኖሚውን ወደ ፊት ያሻግራሉ ብሎ ተስፋ ከጣለባቸው የግብርና፤ ኢንዱስትሪ፤ ማዕድንና ቴክኖሎጂ ጋር በአንድነት የቱሪዝም ዘርፉ የመሪነት ሚና እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

ይህንኑ ሀገራዊ ራዕይ መሠረት በማድረግም ሀገራዊ ለውጡ ዕውን ከሆነበት 2010 ጀምሮ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማወቅ፤ በመለየት፤ በማልማትና መመጠቀም ረገድ እመርታዊ ለውጦች ታይተዋል፡፡ በዚህም የተዘነጉ ከተሞች ጭምር ዛሬ የመታየት እና የመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በከተሞች ምሥረታ ሂደት ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ነች፡፡ ሆኖም የከተሞቹ አመሠራረት እውቀትን ተከትሎ እና አስፈላጊው መሠረተ ልማት ተሟልቶ የተቆረቆሩ ባለመሆናቸው፤ ለኑሮም ሆነ ለሥራ ምቹ ሳይሆኑ ዘመናት ተሻግረዋል፡፡ ይህንኑ ችግር ከመሠረቱ ለመቅረፍም መንግሥት የኮሪዶር ልማት ፕሮጀክትን ይፋ በማድረግ ከተሞች ውብ እና ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በበርካታ ከተሞች የኮሪዶር ልማት እየተከናወነ ሲሆን፣ የኮሪዶር ልማቱም ከተሞች ለኑሮ እና ለሥራ ተስማሚ እንዲሆኑ እና በተጓዳኝም የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆኑ በር የከፈተ ነው፡፡ ይህ ዕድል ከገጠማቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው የባሕር ዳር ከተማ ተፈጥሮ ባደላት ውበቷ ላይ የኮሪዶር ልማቱ ተጨማሪ ውበትን አላብሷታል፡፡

የአማራ ክልል ዋና ከተማ እና የጣና ዳር ፈርጥ የሆነችው ባሕር ዳር ተፈጥሮ ካደላት ውበት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እድሳት ሳይደረግላት ዘመናትን ተሻግራለች፡፡ በዚህም ምክንያት ውበቷ ከጊዜ ጋር እያረጀ መጥቷል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ከተማዋ በተፈጠረላት የኮሪዶር ልማት ተፈጥሮ እና የሰው ጥበብ ተዋሕደው ባሕር ዳርን ይበልጥ ውበቷን እያወጡት ነው።

ባሕር ዳር ተፈጥሮ ከለገሳት ውበት ባሻገር በኮሪደር ልማቱ የተከናወኑት የመንገድ እና የመዝናኛ ማዕከላት ግንባታ ከተማዋን አዲስ ውበት አላብሷታል፤ ዳግም የተወለደች ያህልም ታይታ የማትጠገብ ውብ የንግድ እና የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን በቅታለች፡፡ በዛፍና በቁጥቋጦ ተሸፍኖ የነበረው የጣና ውበት በኮሪደር ልማቱ ተገልጦ ለከተማዋ አዲስ ውበት አላብሷታል፡፡ ተዳፍኖ የቆየው የጣና ውበት በስምንት አቅጣጫ ተከፍቶ ከከተማዋ የትኛውም አካባቢ የሚታይ ፀዳልን አጎናጽፏታል፡፡

ጣና ለዘመናት የነበረ ውበት ነው፡፡ ባሕር ዳር የጣና ሐይቅና የዓባይ ወንዝ መገናኛ ናት። ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የዘንባባ ዛፎች አሏት። በአጠቃላይ ባሕር ዳር ተፈጥሮ ፀጋዋን ያፈሰሰችባት እና ውበቷን ያርከፈከፈችበት ውብ ስፍራ ብትሆንም ዘመኑን የሚዋጅ ውበት ሲታከልበት በነባር ዕሴቶቻችን ላይ አዳዲስ ዕሴቶችን በመጨመር ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል ባህሕር ዳር ቋሚ መዘክር መሆን ችላለች፡፡

ባሕር ዳር ከተፈጥሮ መስሕቧ ባሻገር በጣና ዙሪያ ያሉት ታሪካዊ ሥፍራዎች፤ ከጣናና ከዓባይ ጋር ተያይዘው የተሠሩት ወደቦችና መናፈሻዎች፤ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የዓባይ ዘመናዊ ድልድይ እና ሌሎቹም ልማቶች ባሕር ዳርን የ22ኛው መክዘ የንግድና ቱሪዝም ማዕከል ያደርጓታል፡፡ ይህቺ ካሏት ውብ የተፈጥሮ መስሕቦችና ታሪካዊ ስፍራዎች ባሻገር የኮሪዶር ልማቱ የፈጠረላት ዕድል ከተማዋ ታይታ የማትጠገብ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን ያደርጋታል፡፡

ታዲያ ባሕር ዳር ይህን ሁሉ ስኬት የተጎናጸፈችው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖላት አይደለም፡፡ በክልሉ በነበረው ግጭት እና አለመረጋጋት ባሕር ዳር በችግር ውስጥ ብታልፍም ፈተናው ሳይበግራት እና የተጀመሩ ሥራዎች ለአፍታም ሳይስተጓጎሉ ውጥኗን ከዳር ማድረስ ችላለች፡፡ እንደ አዲስም ለመወለድ በቅታለች፡፡ ይህም ከተማዋን አይበገሬነት ተምሳሌት እንድትሆን እና በችግሮች ውስጥ አልፎ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ማሳያ ያደርጋታል፡፡ ልንከላከልና ልንቆጣጠር የምንችልበት መንገድ መሰራት አለበት ብለው ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት እቅዳችን እየተከለሰና ስትራቴጂክ እቅድ በመቅረጽ ቴክኖሎጂውን ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ርብርብ እያደረግን ነው።

አዲስ ዘመን፡ኮሚሽኑ ሊደርሱ የሚችሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመከላከል ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ታጥቋል ማለት ይቻላል? ሰራተኞችን የምትቆጣጠሩት በምን መልኩ ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡የቴክኖሎጂ ጉዳይ በምናይበት ጊዜ ተቋሙ ትልቅ ቴክኖሎጂ እያለማ ነው። ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ተደርጎ የከተማ አስተዳደሩም የቅድሚያ ቅደሚያ በመስጠት ትልቅ ኢንቨስትመንት አድርጎ እየሰራበት ነው። በቅርብ ጊዜ ተጠናቆ ወደ ሥራ ይገባል። ቴክኖሎጂው በርካታ አሰራሮችን ማከናወን የሚያስችል መተግበሪያዎችን የታጠቀ ነው። የትኛውም ያደገ ሀገር ሊታጠቀው የሚችለው አይነት ቴክኖሎጂ እየበለጸገ ነው። ለምሳሌ የመቆጣጠሪያ፤ የኮማንድ ማዕከል የሚኖሩት ሲሆን፣ በዋናነት አደጋ በሚደርስበት ጊዜ እና የአደጋ ስልክ በሚደወልበት ጊዜ አደጋው ከየት እደተመዘገበ፤ የት ቦታ እንደተነሳ መረጃ የምናገኝበት ቴክኖሎጂ ነው።

አደጋው እንደደረሰ ወዲያውኑ ከማዕከላትና ከማዕከላት ውጭ የወጣ የእሳት አደጋ መኪና ካለ የት እንዳለ በማየት ስምሪት መስጠት የሚያስችል ነው። የሚደወለው ጥሪ ከየት እንደሆነ አካባቢውንና የአደጋ ሰራተኞቹንና ተሽከርካሪዎቹን መቆጣጠር የሚያስችል ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን አደጋው ምን እንደሚመስል ማዕከል ላይ በመሆን አደጋው መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከታተል የሚያስችል ነው። ቢሮ በመሆኑ አደጋውን ለመከላከል አመራር የሚሰጥበት አሰራር ነው። ስለዚህ ቴክኖሎጂው ሰፊ የሆነ አሰራርን አቅፎ ያያዘ ነው። አደጋ በሚደርስበት ወቅት አደጋውን ለመከላከል በትክልል መርተናል አልመራንም፤ በየት በኩል ብንገባ አደጋው መከላከል ያስችላል የሚለው በሚታይ መልኩ ሊያሳይ የሚችል ቴክኖሎጂ እየበለጸገ ነው። እያንዳንዱ የአደጋ መከላከል መኪና ላይ ቴክኖሎጂው የሚገጠም ይሆናል። አቋራጭና አማራጭ የትኛው እንደሆነ መለየት የሚያስችል ነው።

አዲስ ዘመን፡በዋናነት የአደጋዎች መንስኤ ምንድን ናቸው? መለያ መንገዳችሁ በጥናት ላይ የተሰመሰረተ ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡በየጊዜው የአደጋ መንስኤዎች ይለያያሉ። አሁን ላይ እየደረሱ ያሉ አደጋዎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ተብለው ይከፈላሉ። በመዲናችን የሚደርሰው አደጋ የተፈጥሮ ጉዳይ አይደለም። ሰዎች የሚያደርሱት አደጋ ነው። ይህ አደጋ ደግሞ ሆን ብለው የሚያደርሱት አደጋ ብቻ ሳይሆን ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ የሚከሰት ነው። ለምሳሌ ተቀጣጣይ የሆኑና ተቀጣጣይ ያልሆኑ ነገሮችን ሁለቱ አንድ ላይ ይቀመጣሉ። ስለዚህ ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮች ሌላውን ሊያቀጣጥሉ ይችላሉ። እቃዎች ሲቀመጡ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ቁሶች ከሌሎች ቁሶች ጋር በአንድ ቦታ ላይ በምናስቀምጥት ጊዜ ንክኪ ይኖራልና በቀላሉ የእሳት አደጋ እንዲፈጠር ያደርጋል።

በተለይ በማዕድ ቤት ትልልቅ እቃዎች ይከማቻሉ። በዚህ ጊዜ እቃዎቹ መቀመጣቸው እንጂ ምን አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ የሚለውን አናስብም። ስለዚህ በግዴለሽነትና በጥንቃቄ ጉድለት አደጋ ይደርሳል። እቃዎችን ‹‹ስቶር›› ስናደርግ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልገናል። በተለይ በየቤቶቻችን ለምግብ ማብሰያነት የምንጠቀምባቸው ማዕድ ቤቶቻችን ውስጥ የምናስቀምጣቸው ቁሶች ሥራችንን መስራታችን እንጂ በሙቀት ኃይል የሚሳሳቡና በደቂቃ አካባቢው ላይ አደጋ የሚያደርሱ መሆናቸውን አናስተውልም።

በጣም የሚቀጣጠሉና በደቂቃ ውድመት የሚያስከትሉ አሉ። ለምሳሌ ቤንዚን፣ ጋዝና መሰል ተቀጣጣይ ነገሮችን በጥንቃቄ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። ለመኖሪያ ቤታችን ምናደርገው ጥንቃቄ የምናደርውን ያህል በማዕድ ቤቶች አካባቢ አናደርግም። አብዛኛው ማዕድ ቤት ሰው በማያየው መልኩ ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ መልኩ ይቀመጣል። ነገር ግን ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ቁስ እንዳለ መገንዘብ ያስፈልጋል። ለትልቁ ንብረት መውደም መንስኤ የሚሆነው የጥንቃቄ ጉድለት የተቀመጠ ተቀጣጣይ ቁስ ነው።

አሁን ላይ በሰፊው እያጋጠመ ያለው አደጋ የኤሌክትሪክ ‘ኮንታክት’ ነው። ይህ በቀላሉ በተለይም ሙቀት ደረቃማና ነፋሻማ ሁኔታ በሚሆንበት ጊዜ አደጋ ይከሰታል። ይህም የሚነሳው የምንጠቀመው የኤሌክትሪክ ሲስተማችን የሚያመጣው ነገር ነው። ብዙውን ጊዜ በማንዋል የሚጠቀም ማኅበረሰብ ይበዛል። የትኛው መስመር ከየትው መስመር ኮንታክት እንደሚያደርግ ጥንቃቄ ሳናደርግ ስንቀር ኮንታክት ይኖራል። በዚህ ላይ አደጋ ደርሶ ወደ አካባቢው ስንሄድ መግቢያ የሚጠፋበት ሁኔታ ብዙ ነው። ከሰዎች የጥንቃቄ ጉድለት ውጭ የእኛ ሀገር የአየር ንብረት ጥሩ ነው። እሳተ ገሞራ ፍንዳታ እየተነሳ አይደለም። ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተሰራ ነው። ወደፊትም ረጅም ርቀት የምንሄደውና እስከ ቅጣት ድረስ የምንደርሰው በዚህ የጥንቃቄ ጉዳይ ይናሆል። ስለዚህ ጥንቃቄ እጅግ ወሳኝ ነው። ሰዎች ብዙ ለፍተው ሀብታቸውን ከሰበሰቡና ካከማቹ በኋላ ደቂቃ በማይሞላ የእሳት አደጋ እያጡ ነው።

ሁልጊዜ ሥራችን ምን ያህል ከአደጋ ነጻ ነው የሚለውን ልናስብ ይገባል። ለምሳሌ ሕንጻ ሲሰራ ወደታች በሚቆፈርብት ጊዜ ከጎን ያለው ቤት ወይም ሕንጻ ይደረመሳል? ወይስ አይደረመስም? ከላይ ሥራ እየተሰራ ከታች ያለው ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ነው? ወይስ አይደለም? የሚል እሳቤ ሲታይ ሰፊ ክፍተት አለ። ይህ ሲታይ ዋጋ እያስከፈለ ነው። በከተማዋ ውስጥ በየቀኑ የሚደርሱ አደጋዎችን በምናይበት ጊዜ አደጋዎቹ ከጥንቃቄ ጉድለት የሚመነጩ ናቸው። ሁላችንም በየአካባያችን ስናይ ምንም ችግር የማይደርስ ይመስለናል። ነገር ግን ወደ አንድ ማዕከል ጥሪዎች በሚገቡበት ጊዜ እና አደጋዎቹን ለመቆጣጠር በምንቀሳቀስበት ጊዜ ሰፋፊ አደጋዎች እየደረሱ ነው። የጥንቃቄ ጉድለት በከተማዋ ሰፍቶ ይታያል።

አዲስ ዘመን፡በቅርቡ መርካቶ የገበያ ማዕከል ላይ የደረሰው አደጋ ተከትሎ የአደጋው መንስኤ ተጣርቶ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት ሆን ተብሎ የሚል የቃላት አጠቃቀም ነበርና ይህ ከምን የመነጨ ነው? ብዙ ጊዜ የጠራ መረጃ ለሕዝብ አይደርስም የሚል ሀሳብ ይነሳል እና በዚህ ላይ ምላሽዎ ምንድን ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡ፖሊስ ያወጣው መግለጫ እኔም አይቸዋለው፤ የአደጋው መንስኤ በምን በምን እንደሆነ የገለጸ ሲሆን፣ ምንነቱን ደግሞ ሆን ተብሎ እና መሰል የመግለጫ ቃላትን ተጠቅመዋል። ሆን ተብሎ የሚለውን ራሱ መግለጫው የሰጠው አካል ቢያብራራው ጥሩ ነው። ነገር ግን እኔም እንደ ፖሊስ ግልጽ በሆነው አማርኛ ስገልጸው እና ሁላችንም እንደምንረዳው አደጋ ሆን ተብሎ ይደርሳል ልንል እንችላለለን። ለአብነት የሆነን ቤት ጠላት ኖሮ ቢቃጠል አደጋ ነው። ነገር ግን ያቃጠለው አካል አደጋውን ያደረሰው ሆን ብሎ ነው። ይህን የማወራው ስለመርካቶው ቃጠሎ ሳይሆን ሆን ተብሎ የሚለው ቃላት ጥሬ ትርጉም ለመግለጽ ነው።

አደጋ ሆን ተብሎ እንዴት ሊደርስ ይችላል? ሲባል አንዳንድ ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች ይጓጉ እና ኢንሹራስ ያለው አሮጌ መኪና ቢኖራቸው መኪናቸውን አቃጥለው በአደጋ ወደመ ብለው ሊያወሩ ይችላሉ። ይህን አደጋ ከጥንቃቄ ጉድለት ወይም ደግሞ ሳያስበው ሊባል ይችላልና ሲመረመር ሆን ብሎ የሚለው ሊያሳይ ይችላል። ሌላው አንዱን ለመጉዳት ብሎ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የአደጋ መንስኤው ምንድን ነው? በምንልበት ጊዜ ሆን ብለው ያደረሱት ነው ልንለው እንችላለን። ምክንያቱም አደጋ በግዴለሽነት፣ ሆን ተብሎና በተፈጥሮ ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ ሆን ተብሎ የሚለው ተራ በሆነው አገላለጽ ሰዎች አስበው የሚያደርሱት አደጋ ነው። ነገር ግን የመርካቶውን አደጋ የደረሰበት ሁኔታን ትርጉም ለመረዳት መግለጫውን የሰጠውን አካል መጠየቅ ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡በመዲናይቱ ሕንጻዎችን ለመገንባት በሚቆፈርበት ወቅት ከጎን ያለው ቤት በመደርመስ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ሲደርስ ይስተዋላልና ግንባታ የሚሰሩ ዜጎች ደህንነት መጠበቂያ ሲያደርጉ አይታይም፤ በዚህ ላይ ተቋሙ ጥብቅ ቁጥጥር የማያደርገው ለምንድን ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡እውነት ነው፤ ደህንነት ወይም ሴፍቲ ላይ አድርግ የተባለው ማድረግ መቻል አለበት። ካላደረገ ግን የግንዛቤ የመፍጠር፤ የማስጠንቀቂያ፣ የእርምት እርምጃ ይወሰዳል። ይህን ለማስፈጸም እስካሁን መመሪያ አልነበረም። በቅርቡ 63/2017 ተግባራዊ እየተደረገ ያለ መመሪያ ወጥቷል። መመሪያው ወደ ሥራ ገብቷል። ነገር ግን በተገቢው መንገድ እና በሚፈለገው ደረጃ ስላልሆነ የግንዛቤ ፈጠራ በትኩረት ተጀምሮ እየተሰራ ሲሆን፣ እስካሁን ብዙ ማስጠንቀቂያ የሰጠናቸው አካላት አሉ።

ከሰሞኑ የሚዲያ ንቅናቄ አድርገናል። የሕዝብ ንቅናቄ በቅርቡ ይካሄዳል። ይህን በትክክል ለመተግበር በሰፊው የሚሰራ ሥራ ነው። ከዚያ በፊት ግን ከባለድርሻ አካላት ጋር መቀናጀት ያስፈልጋል። ለምሳሌ የግንባታ ፈቃድ በጣም ወሳኝ ባለድርሻ አካል ነው። የግንባታ ፈቃድ የመጠቀሚያ ፈቃድ በሚሰጥበት ጊዜ የደንነት ሕጎች መሟላታቸውን ማስቀመጥ መቻል አለበት። እነዚህን በማረጋገጥ የሚሰራ ይሆናል። በሌሎች ሀገራት ላይ አንድ ግንባታ በሚገነባት ጊዜ የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤቱ መስፈርቶች ተሟልተዋል? አልተሟሉም? የሚለው ሙያዊ አስተያየት ይሰጥበታል። አገልግሎት የሚሰጠው ሁሉም ነገር የተሟላና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው የሚለውን እውቅና ሲሰጥ ነው። በእኛ ሀገር ቢሆን ይህ ተግባር መቀጠል መቻል አለበት። አሁን ያን መመሪያ ይዘን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሰራን ነው። አሰራሩን በተገቢው መንገድ መሬት ላይ መተግበር ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡በመዲናችን በርካታ ሕንጻዎች የደህንነት መስፈርት እንዳላሟሉ ከዚህ በፊት የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ አድርገው ነበር፤ አሁን ላይ አስገዳጅ ሕግ አልወጣም? እርሰዎ የገለጹት መመሪያ ይህን ጥያቄ ይመልሳል?

ኮማንደር አሕመድ፡አዎ! መመሪያው ሕንጻዎች የደህንነት መስፈርት እንዲያሟሉ በአስገዳጅነት እንዲተገበር የሚያደርግ መመሪያ ነው። ይህን ለማስተግበር በሰው ኃይል ተደራሽ መሆን ያስፈልጋል። የሰው ኃይልን በማጠናከር ይህንን ሊያስፈጽሙ ከሚችሉ አጋር ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ እየተፈራረምን ወደ ሥራ እናስገባለን። ወደ ሥራ ገብቶ ወደ ቅጣት ከመግባታችን በፊት ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መሰራት መቻል አለበት። ለዚህም ነው ሰፊ ንቅናቄ በመዲናችን ለማድረግ እየተሰራ ያለው።

እስካሁን ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው አካላት አሉ። ግንዛቤ እየተፈጠረ የሄደበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን በቂ አይደለም። ይህ ሥራ ወደ ግብ ለማድረስ በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ ድጋፍ እዲደረግልን እየጠየቅን ነው። ደህንነት በጣም ያስፈልጋል። አደጋ ከደረሰ በኋላ ሳይሆን አደጋ ከመድረሱ በፊት መስራት ይገባናል። በተለይ 70 በመቶ የሚሆነው ሥራ ሊሰራ የሚችለው ሥራ አደጋ ቅነሳ ላይ ነው። ይህን ልንሰራ የምንችለው በግንዛቤ ፈጠራና በቁጥጥር ሥራ ነው።

በመከላከል ሥራው ባለድርሻ አካላት ሊያግዙን ይገባል። በአደጋ እየወደመ ያለው የሰዎች ንብረትና የሀገር ሀብት ነው። ሥራው ሰብአዊ ሥራ ነውና ለኮሚሽኑ ወይም ለተወሰነ አካል የሚሰጥ አይደለም። ስዚለህ ሰፊ የቅስቀሳ ሥራ የምሰራው እንደዜጋ ግንዛቤ ለመፍጠርና ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ለማድረግ ነው።

አደጋ በደረሰበት ቦታ ላይ ቶሎ መደወል ያስፈልጋል። ሰው እናጠፋለን ብሎ ብዙ ከለፋ በኋላ እና ከተስፋፋ በኋላ ስልክ ይደውላል። 939 ነጻ የስልክ ጥሪ መስመር በማንኛውም ሰዓት የአደጋ ምላሽ ለመስጠት ኦፕሬተሮቻችን ጆሯቸው ላይ አድርገው የሚጠብቁት ስልክ ነው። እንደ ድሮው አያነሱትም የሚባል ነገር የለም። ከማሕበረሰቡ የሚጠበቀው አደጋ ከደሰረሰ ወዲያው ለኮሚሽኑ መደወል ነው። አሁን ላይ እየሆነ ያለው ማሕበረሰቡ አቅሙን ከጨረሰ እና ከተስፋፋ በኋላ ነው። ለምን ጠራችሁን ተብሎ የሚጠይቅ አደጋ ሰራተኛ የለም። ስለዚህ ትንሽም አደጋ ይሁን ወዲያው የድረሱልኝ ጥሪ ማሰማት መቻል አለበት። ምን አልባትም ጥሪ ተደርጎልን ማሕበረሰቡ አደጋው ተቆጣጥሮ ብንደርስ የበለጠ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ስለሚሰራ ሁሉም በመልካም መልኩ እንዲጠቀምበት ያስፈልጋል።

አዲስ ዘመን፡በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ምንም ያህል ግንዛቤ ፈጠራ ቢሰራ ርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳልና ተጨባጭ ርምጃ የምትወስዱት መቼ ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡ መመሪያው ከጸደቀ ጀምሮ ርምጃ እየተወሰደ ነው። ርምጃ ማለት መቅጣት ብቻ አይደለም፤ ማስተማርንም ይጨምራል። አሁንም ማስጠንቀቂያ የሰጠናቸው አካላት አሉ። ሕጉ በመጀመሪያ አንድ አካል የደህንነት መስፈርት ያላሟላ ከሆነ በማስጠንቀቂያ እንዲቆይ ቀነ ገደብ ይሰጠዋል። በማስጠንቀቂያው መሰረት ማስተካከል ካልቻለ ወደ ቅጣት ይሄዳል። ስለዚህ አሁንም ወደ ቅጣት የገቡ አሉ። የግንዛቤ ፈጠራ ሥራው ማሕበረሰቡ በሰፈው ግንዛቤ እንዲፈጠርለት እንጂ ወደ ሥራ አልገባንም ማለት አይደለም። ነገር ግን ሕብረተሰቡ መረዳት በሚገባው ልክ ከመረዳት አንጻር ክፍተት አለ። ክፍተቱን ልንቀርፈው የምንችለው ሰፊ የግንዛቤ ሥራ ስንሰራ ነው ከሚል እሳቤ እንጂ ወደ ሥራ ገብቷል።

አዲስ ዘመን፡የአደጋ ሰራተኞች አደጋው በደረሰበት ቦታ ሄደው ይደራደራሉ የሚል ሀሳብ ሲነሳ ይደመጣልና በዚህ ላይ የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው?

ኮማንደር አሕመድ፡ከዚህ ላይ አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ጉዳይ ሁልጊዜ ወሬ አይወራም ማለት አይደለም። ነገር ግን እውነታውን ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ የመርካቶ አደጋ የደረሰበት ሁኔታ ስናይ ሁሉም አመራር ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ አመራር ድረስ በቦታው ነበርን። እኔ በወቅቱ ሌላ ተቋም ላይ የነበርኩ ቢሆንም እንደ አመራር ግን ቦታው ላይ ነበርኩ። የአደጋ ሰራተኞች ሲያፈሱ የነበረው ላብና ደም ነበር። አደጋ ውስጥ ገብተው የሚደራደሩት ከየትኛው ሰው ጋር ነው? የሚደራደሩት እንዴትስ ብለው ነው? ማንን በምን ሞራል? የትኛውን አካል ነው ገንዘብ አምጣ ብለው ድርድር ውስጥ የሚገቡት? ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ለወሬ ተብለው የሚነሱ ነገሮችን ሚዲያውም ቢሆን ሳያረጋግጥ ሀሰተኛ መረጃ ባያሰራጭ መልካም ነው፤ ላብና ደሙን እያፈሰሰ የራሱን ሕይወት ለእሳት ሰጥቶ የሰው ሕይወትና ንብረት ሊያተርፍ የሚተጋውን ሰራተኛ ልንደግፈው የምንችለው በሞራል ነው።

ሰራተኛውን በሀሰተኛ ወሬ ሞራሉን የምናሳጣው ከሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ማን ይሰራል? የሚለውን ማየት ይጠበቅብናል። እንዲህ አያደርግም አንልም፤ ፖሊስ ያጣራው ተብሎ ለፖሊስ ተሰጠ። ስለዚህ ባለን መረጃ ተራ ወሬ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ፖሊስ መግለጫ የሚሰጥበት ይሆናል። እጅግ የሚያሳዝነው ግን የሚለፉትንና የሚቃጠሉትን ሰራተኞቻችንን ያልሆነ ስም መስጠት ተገቢ አይደለም። ‘አስጠፋላችኋለሁ ገንዘብ ክፍሉ’ የሚል የአደጋ ሰራተኛ መስሎ የሚያወራ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን የአደጋን ሰራተኛ ይደራደራል ለማለት አደጋ በደረሰበት ስፍራ ምን መስሎ እንደሚሰራ መመልከት በቂ መረጃ ነው። ከውሃና ከማሽን ጋር እየታገለ ቢጠራ እንኳን የሚሰማ አይደለም። በቦታው ያለ ሰው ለመደራደር ምቹ ሁኔታስ አለ ወይ? የሚለውን ማየት በቂ ነው።

ሕብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ይዞ ለኮሚሽኑ ጥቆማ ከሰጠና አጣርተን ይህን ያደረገ ሰው ቢገኝ ከጠላት ተለይቶ አይታይም። ተጨባጭ መረጃ ሲደርስ ወንጀል የሰራው ሰራተኛ ለተቋሙ ስትራቴጂክ ጠላት ነው። ነገር ግን ብዙ የኮሚሽኑ ሰራተኞች አደጋ ለመከላከል ሌላ አደጋ እየደረሰባቸው ነው። አሁን ብዙ ሰራተኞች ጉዳት ላይ ነው ያሉት። ከአደጋ መከላከል መልስ የሥራ ግምገማ አለ፤ እያንዳንዱ ሰራተኛ ሪፖርት ያቀርባል። በዚህ ልክ ብልሹ አሰራር ውስጥ የገባ ሰራተኛ አላጋጠመንም። ስለዚህ ከወሬ ባለፈ ይህን ሲያደርግ አይቻለው ብሎ ለኮሚሽኑ ጥቆማ መስጠት ይቻላል።

አዲስ ዘመን፡ለሰጡን ማብራሪያ በዝግጅት ከፍላችን ስም አመሰግናለሁ።

ኮማንደር አሕመድ፡እኔም መረጃ እንድሰጥ ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናለሁ::

ሞገስ ተስፋ

አዲስ ዘመን ረቡዕ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You