አሜሪካ በአልሞ ተኳሾች የሚፈጸም የሞት ቅጣትን ዳግም ጀመረች

የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን (ሜይንስትሪም ሚዲያዎች) ጋር ቦታ የተቀያየሩ ይመስላል:: ማህበራዊ ገጾች ሊሠሩት የሚገባውን እንቶ ፈንቶና ዋዛ ፈዛዛ የሆኑ ቀላል ነገሮችን ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ላይ፤ በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ይተነተናሉ::

ይሄ ነገር እየተለመደ ይመስላል:: ለዚህም ነው አሁን አሁን ማህበራዊ ገጾች ላይ የሚደረግ ነገር እንደ ቁም ነገር ተቆጥሮ ትችትና ወቀሳ እየተደረገበት ያለው:: ማህበራዊ ገጾች ላይ ቀልድና ዋዛ ፈዛዛ የበዛበት ነገር ሲጻፍ ብዙ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት ‹‹ለምን ቁም ነገር አትጽፍም?›› የሚል ነው::

አዎ! ቁም ነገር ቢጻፍ የበለጠ ጥሩ ነበር፤ ዳሩ ግን እንቶ ፈንቶ ነገሮች ደግሞ ከማህበራዊ ገጾች ሊጠፉ አይችሉም:: የማህበራዊ ሚዲያን ባሕሪ እየዘነጋነው ይመስላል::

ማህበራዊ መገናኛ (ሶሻል ሚዲያ) ማለት ልክ እንደ ማህበራዊ ሕይወታችን ማለት ነው:: ‹‹ማህበራዊ›› የሚል ስያሜ የተሰጠውም ለዚህ ነው:: በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ ደግሞ ብዙ ነገሮች አሉ:: ማህበራዊ ሚዲያ ልክ እንደ ማህበራዊ ሕይወታችን ነው ካልን፤ በማህበራዊ ሕይወታችን የሚደረጉ ነገሮች ይደረጉበታል ማለት ነው፤ በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን የምናደርገው ብዙ አሰላስለን ሳይሆን ትዝ እንዳሉን ነው::

በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ ከጓደኛችን ጋር፣ ከሥራ ባልደረባ ጋር፣ ከጎረቤትና ከቤተሰብ ጋር ሁልጊዜ ጠንካራ ጉዳዮችን አናወራም:: ካፌ ውስጥ ወይም መዝናኛ ቦታ ወይም ቤት ውስጥ ሰብሰብ ስንል ቀልድና ጨዋታዎች ናቸው የሚበዙት፤ ማህበራዊ ሚዲያ ልክ እንደዚያ ማለት ነው:: ተራ ገጠመኞች ሲያጋጥሙን አጠገባችን ላለ ጓደኛ እንናገራለን፤ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንታችንም ልክ እንደዚያ ማለት ነው፤ ተራ ገጠመኞችን ሁሉ ልናጋራበት እንችላለን:: ይሄ ማለት ግን ለሰዎች ምንም ስሜት የማይሰጥ ወይም ከባሕልና ወጋችን ውጭ የሆነ ነገር ሁሉ ይደረግበት ማለት አይደለም፤ እንደዚያ ከሆነ የራሳችንን ክብር ነው የሚያወርደው::

ማህበራዊ ሚዲያ የማህበራዊ ሕይወታችን ነፃብራቅ ነው:: ይሄ ማለት ሀሜትና አሉባልታም ይኖርበታል ማለት ነው:: ዲያቆን ዳንኤል ክብረት (አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪና የፓርላማ አባል) በአንድ ወቅት በአርትስ ቴሌቭዥን የደረጀ ኃይሌ ‹‹በነገራችን ላይ›› ፕሮግራም ላይ የተናገረውን በየአጋጣሚው ደጋግሜ አስታውሰዋለሁ:: ደጋግሜ ያስታውስኩበት ምክንያት የልቤን ስለተናገረልኝ ነበር::

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሃሳብ ሲጠቃለል፤ ማህበራዊ ሚዲያ አዲስ ነገር ይዞብን አልመጣም፤ በማህበረሰባችን ውስጥ የነበረውን ነገር ተደራሽ እንዲሆን ነው ያደረገው፤ ሜዳውን ነው የፈጠረው:: ከማህበራዊ የትስስር ገጾች መፈጠር በፊት በጎረቤት፣ በአካባቢ፣ በገበያ፣ በአጠቃላይ በሰሚ ስሚ ይዛመት የነበረን ነገር አሁን በአንድ ጊዜ እንዲጥለቀለቅ አደረገ:: ቡና ላይ ይወራ የነበረ ሀሜት አሁን በብዙ ሺህ ሰዎች ዘንድ በአንድ ጊዜ እንዲታይና እንዲሰማ ሆነ:: ይህ ሲሆን ግን መተግበሪያው ባሕሪዎቻችንን ጭምር ይዞብን የመጣ መሰለን:: እንደ ማህበረሰብ ስንለወጥ ነው የማህበራዊ ገጾቻችን ገጽታም የሚለወጠው:: ምክንያቱም ገጾች ላይ የሚጽፉትም ሆነ የሚያወሩት በየመንገዱና በየመንደሩ ነውር ነገር ሲያደርጉ የምናያቸው ሰዎች ናቸው::

በቀልድና ዋዛ ፈዛዛ ነገሮች በኩል ግን በኢትዮጵያ ብቻ ያለ አይደለም:: በሌሎች የዓለም ሀገራትም ማህበራዊ ሚዲያ ቀለል ላሉ ነገሮች ነው የሚያገለግል፤ እንዲያውም ጠንካራ ሃሳቦችን በማሰራጨት በኢትዮጵያ ያለው ድርሻ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም::

እስኪ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የማህበራዊ ገጾቻቸውን ተመልከቱ:: የሚሰጣቸው ግብረ መልስና የዕይታ ብዛት(view) ከሀገራችን መገናኛ ብዙኃን በታች የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: ይሄ ማለት በሀገራችን ማህበራዊ ገጾች ንቁ ተሳታፊ አላቸው ማለት ነው::

ማህበራዊ ገጾች ለምን የጠንካራ ሃሳቦች ማንሸራሸሪያ ሆኑ ቢባል ምናልባትም የዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ጠንካራ አለመሆን ነው:: ፖለቲካዊ ጉዳዮች በስፋትና በድፍረት ስለማይተነተኑ፣ በሀገሪቱ የሚከሰቱ ክስተቶች በፍጥነት ሽፋን ስለማያገኙ ሰዎች ወደ ማህበራዊ ገጾች አዘወተሩ ማለት ነው:: ይህ ነገር ልማድ እየሆነ መጣ፤ አሁን ላይ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ራሱ ‹‹ሰበር ዜና›› የሚያስተዋውቁት በማህበራዊ ገጻቸው ሆነ:: ማታ ቴሌቭዥን ወይም ሬዲዮ ስንከፍት ምንም አዲስ ነገር አናገኝም:: በማህበራዊ ገጾቻቸው ስናየው የቆየነውን ዜና ነው ማታ ሲያነቡት የምንሰማው:: በማህበራዊ ገጾቻቸው የሚለቁት ደግሞ ላለመቀደም ሲሉ ነው:: ይህ ዘመኑም የሚያስገድደው ሁኔታ ነው::

በሌላ በኩል ማህበራዊ ገጾች ልቅ የሆነ ነፃነት ስላላቸው ሰዎች ያዘወትሯቸዋል:: ዋናዎቹ የኤዲቶሪያል ሕግ አላቸው፣ ያልሆነ ነገር ቢናገሩ ተጠያቂነት አለባቸው፤ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው:: ማህበራዊ ገጾች ግን ባለቤታቸው ማን እንደሆነ ራሱ አይታወቅም፤ ተጠያቂነታቸው ጠባብ ነው:: የሚለቀቀው መረጃ በኤዲቶሪያል ውሳኔ ሳይሆን በአንድ ግለሰብ ፍላጎት ሊሆን ይችላል:: ችግሩ ግን ማህበረሰባችን ደግሞ ይህን አያገናዝብም:: የተባለ ነገር ሁሉ እውነት የሚመስለው ብዙ ነው::

ከምንም በላይ ግን ማህበራዊ ገጾችና ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ቦታ እየተቀያየሩ መሆኑ መጥፎ ልማድ ነው:: የውሃ መራጨትና ከዶሮ ጋር መሯሯጥ የመሳሰሉ የሕጻናት ጨዋታ የሚመስሉ ፕሮግራሞችን በቴሌቭዥን መስኮት እያየን፣ ቀጠናዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ትንታኔዎችን ከፌስቡክና ዩትዩብ መከታተል የተገላቢጦሽ ነው::

በርግጥ ዲጂታል ሚዲያው በዓለም አቀፍ ደረጃም ዓይነቱና ተጠቃሚው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ነው:: ‹‹ስማርት ኢንሳይት›› የተባለው ድረ-ገፅ ከዓመት በፊት የማህበራዊ ገጾችን መረጃ አውጥቷል:: በዚህ መረጃ 60 በመቶ (4 ነጥብ 80 ቢሊዮን ሕዝብ ማለት ነው) የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ ማህበራዊ ገጾችን ይጠቀማል:: በቀን ያለው አጠቃቀም በአማካይ 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ነው:: በፊሊፒንስ ተሠራ በተባለ ጥናት ግን አንድ ሰው በቀን 4 ሰዓት ይጠቀማል:: ከማህበራዊ ገጽ ፕላትፎርሞች ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው ፌስቡክ ነው (ይህ እንኳን በግምትም ቢሆን ያስታውቃል):: ቀጥሎ ግን ዩትዩብ ነው::

በሀገራችን ያለው አጠቃቀምም ዓለም አቀፉን ሁኔታ የተከተለ ቢመስልም፤ አሁን ግን ቲክቶክ ሳይበልጥ አይቀርም:: ሆኖም ግን ለጠንካራ ጉዳዮች አገልግሎት ላይ የሚውሉት ፌስቡክና ዩትዩብ ናቸው:: ችግሩ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሀሰተኛ መረጃዎች እየዋለ ነው:: ይህን ልማድ ማስቀረት አለብን:: ይህን ልማድ ለማስቀረት ደግሞ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን መብለጥ አለባቸው:: መብለጥ ሲባል ማህበራዊ ገጾች ላይ ያለውን ግሳንግስ ሁሉ ይዞ መሄድ ሳይሆን ጠንካራ ጉዳዮችን መተንተን ማለት ነው:: ምክንያቱም የተሻለ ታማኝነት ያላቸው ዋናዎቹ ናቸው:: በማህበራበዊ ገጾች የሆነ ዜና ሲሰራጭ ለማረጋገጥ ወደ ዋናዎቹ ነው የምንሄደው:: ስለዚህ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ይህን ክብደታቸውንና ታማኝነታቸውን ማስቀጠል አለባቸው::

ለማህበራዊ ገጾች የምንሰጠው ክብደት ግን ልብ መባል አለበት:: ማህበራዊ ሚዲያ በባሕሪው ቀላል ለሆኑ ነገሮች ነውና የግድ ቁም ነገር ብቻ ይጻፍበት ማለት አያስችልም:: ለቁም ነገርና ለጠንካራ ጉዳዮች መገፋፋት  ያለብን ዋናዎቹን ነው!  በጥይት እንዲገደል የተበየነበት ብራድ ሲግሞን ጋዜጠኞች፣ የሕግ ባለሙያዎች እና የሞት ቅጣት የሚፈጸምበት ቤተሰቦች ከሞት ክፍሉ ፊት ለፊት በመስታወት በተከፈለ ስፍራ ላይ ይቀመጣሉ። የዓይን እማኞቹ ታራሚው፣ ሲግሞን ሞቷል እስኪባል ድረስ መመልከት ይችላሉ። በደቡብ ካሮላይና በሚገኘው ማክሊን በተሰኘው የጦር መሣሪያ ማሠልጠኛ አካዳሚ የጦር መሣሪያ መምህር የሆኑት ድሪው ሶፍት በጥይት ስለመገደል የሞት ቅጣት ላይ ያላቸውን ስጋት ለአሜሪካው የዜና ወኪል ኤንፒአር አጋርተዋል።

“አሰቃቂ እንደሚሆን አያጠራጥርም” የሚሉት መምህሩ፤ “ሦስቱም ጥይቶች በታራሚው አንድ የአካል ክፍል ላይ የሚተኮሱ ከሆነ ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል። ይህም ከፍተኛ የደም መፍሰስ ያስከትላል” ብለዋል።

በተጨማሪም የጥይት ፍንጣሪዎች ሰዎችን እንዲሁም የቤት ዕቃዎችን ሊመቱ እንደሚችሉ ያላቸውን ስጋት አጋርተዋል። በአንድ ክፍል ውስጥ ግድያው በሚፈጸምበት ወቅት መርዛማ ጋዞች የመለቀቅ ስጋት እና ከፍተኛ ድምፅም በአልሞ ተኳሾቹ ላይ የመስማት ችግር ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ገልጸዋል።

ዓርብ ምሽት በጥይት በተፈጸመው የሞት ፍርድ ሲግሞን በሰባት ደቂቃ ውስጥ መሞቱ በአንድ ዶክተር ተረጋግጦ ሂደቱ አብቅቷል። በስፍራው በሲግሞን የተገደሉት ሰዎች የቤተሰብ አባላት፣ የፍርደኛው መንፈሳዊ አማካሪ እና ሌሎችም በምሥክርነት ተገኝተው ነበር። ሲግሞን ከመገደሉ በፊት በሰጠው የመጨረሻ ቃል የዓይን እማኞቹ የሞት ቅጣት እንዲቀር እንዲጥሩ በመጠየቅ ወንጀሉን በፈጸመበት ጊዜ “በጣም ስሜታዊ” እንደነበር በመጥቀስ ድርጊቱ ምን ያህል የተሳሳተ መሆኑን በጸጸት ገልጿል።

የመጨረሻ ቃሉን ከሰጠ በኋላም ፊቱ እንዲሸፈን ተደርጎ አልሞ ተኳሾቹ በደረቱ ላይ በተቀመጠው የዒላማ ምልክት ላይ በማነጣጠር ሦስት ጊዜ ተኩሰው ፍርዱን ተፈጻሚ አድርገዋል። ከአውሮፓውያኑ 1977 ጀምሮ በአሜሪካ ሦስት ፍርደኞች በአልሞ ተኳሾች የሞት ቅጣት ተፈጻሚ ሆኖባቸዋል። ሦስቱም የተፈጸሙት በዩታ ግዛት ሲሆን፣ የመጨረሻውም በአውሮፓውያኑ 2010 ነበር።

ነገር ግን በጥይት መገደል በአሜሪካ ረጅም ታሪክ አለው። በአሜሪካ የርስ በርስ ጦርነት ወቅት ቢያንስ 185 ሰዎች በጥይት መገደላቸውን በክሊቭላንድ ሎው ሪቪው ላይ የወጣ ጽሑፍ ያመለክታል። በርስ በርስ ጦርነቱ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በአልሞ ተኳሾች በጥይት መግደልን እንደ የአደባባይ ትርዒት በመጠቀም ወታደሮች ከትዕዛዝ እንዳያፈነግጡ ለማሸበሪያነት ይጠቀሙበት እንደነበር በደቡብ ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር የሆኑት ማርክ ስሚዝ ተናግረዋል።

አዲስ ዘመን ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You