ኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ያላት አበርክቶ ለአፍሪካ የፀጥታ ምክር ቤት እንድትመረጥ አስችሏታል

አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በአፍሪካም ሆነ በተባበሩት መንግሥታት የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ፕሮግራም ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ውስጥ በመሳተፍ ያላት ተሞክሮ የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት አባል ሆና እንድትመረጥ አስችሏታል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገለጹ።

46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ከየካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ኢትዮጵያ የሰላምና ደህንነት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧን አስመልክተው ትናንት ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የአፍሪካ ህብረት በአጀንዳ 2063 እውን ለማድረግ ከያዛቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ ነው።

ሕብረቱ ሥራውን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን እንዲያስችለው የአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አቋቁሞ እየሠራ መሆኑን አንስተው፤ ኢትዮጵያ ከ15ቱ አባል ሀገራት አንዷ በመሆን የበኩሏን አስተዋጽኦ እንድታደርግ ተመርጣለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ አባል እንደመሆኗ ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር በመሆን የድርሻዋን እንደምትወጣ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል ከሊግ ኦፍ ኔሽንስ ጀምሮ የጋራ ደህንነት ሃሳብን በዲፕሎማሲዋ ስታራምድ የቆየች ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስጠበቅ ዘመቻዎች የኢትዮጵያ ሠራዊት በተለያዩ ሀገራት የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በማንኛውም ጊዜ ሰላምና ጸጥታን በሚመለከቱ ጉዳዮች በጎ አመለካከትን ስታራምድ የቆየች ሀገር መሆኗ የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አባል ሆና እንድትመረጥ አስችሏታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አባልነቷን ከተያዘው ዓመት ጀምሮ ገፍታ እንደምትሠራበት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በማንኛውም ጊዜ ሰላምና ጸጥታን በሚመለከቱ ጉዳዮች በጎ አመለካከትን ስታራምድ የቆየች ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ በጋራ ደህንነት ላይ በነበራት አበርክቶ የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አባል ሆና እንድትመረጥ አስችሏታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከ15ቱ አባል ሀገራት አንዷ በመሆን የተመረጠች ሲሆን ምክር ቤቱ በቀጣይ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር በመሆን የድርሻዋን እንደምትወጣ ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስጠበቅ ዘመቻዎች የኢትዮጵያ ሠራዊት በተለያዩ ሀገራት የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት አባልነት እኤአ ከ2025 እስከ 2027 እንደሚቆይ ተናግረዋል ።

ሰሚራ በርሀ

አዲስ ዘመን ዓርብ የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You