በዚህ ምክንያትም ሰዎች የመመገቢያ እና እረፍት የማድረጊያ ስፍራን ሲያስቡ ቅድ ሚያ ምርጫቸው እያረጉ የመጡት ስማርት ስልኮቻቸውን በመነካካት መኪና መከራየትን ሆኗል፡፡
የኤንአይቲ ዶኮሞ የመኪና አከራይ ድርጅት ኃላፊ መኪና ለግል አገልግሎት ሊውል ይችላል፤ ሰዎች መኪናዎቻችንን እኛ ከምናስበው ውጪ ለሌሎች በርካታ ተግባሮቸ ሲጠቀሙባቸው ይስተዋላሉ ሲል ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል፡፡
ሌላው በጃፓን በመኪና ኪራይ መሪ ከሚባሉት ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የታይምስ 24 መኪና አከራይ ኩባንያ እንዲሁ በመኪና ተከራዮች ዘንድ ተመሳሳይ ተግባር ማየቱን ይገልጻል፡፡ በተከራዮቹ ላይ ያደረገውን ቅኝት አስመልክቶ ሲናገርም ተከራዮች በተከ ራዩት መኪና ውስጥ እረፍት እንደሚያደርጉ አንዳንዶቹም ስራዎቻቸውን እንደሚሰሩም ገልጿል። አንዳንዶች እቃዎችን ለተወሰነ ጊዜ ለማቆያነት እንደሚጠቀሙባቸውም አመልክቷል።
አሪክስ የተሰኘው መኪና አከራይ ድርጅት በበኩሉ ያከራያቸው መኪናዎች ብዙ ርቀት አለመጓዛቸውን አንዳንዶቹም ተንቀሳቅሰዋል የሚያስኝ እንቅስቃሴ አለማድረጋቸውን ማረጋገ ጡን ጠቅሶ ከዚያ በመለስ ግን ለምን አገልግሎት እያዋሏቸው ስለመሆኑ የደረሰበት ግምገማ እንደሌለው ተናግሯል፡፡
በጃፓን መኪና ተከራይቶ ከትራንስፖርት እና መኪና ከማሽከርከር አገልግሎት ውጪ ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋል የተጀመረው እኤአ በ2011 በሀገሪቱ ተከስቶ ከነበረው ሱናሚ ማግስት አንስቶ መሆኑን ዘገባው ጠቁሞ፣ በወቅቱም መኪና መከራየት የሚያስፈልገው ሞባይል ቻርጅ ለማድ ረግ ብቻ እንደነበርም አመልክቷል፡፡ በጃፓን መኪና ተከራይቶ ማሽከርከር የተለመደ ቢሆንም ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን መኪና እየተከራዩ ለሌሎች የተለያዩ ተግባሮች ማዋል እየተለመደ መምጣቱን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የፊንላንዷ ከተማ ሶነካጀርቪ በየዓመቱ አንድ የተለየ ውድድር ታዘጋጃለች፡፡ ይህ ውድድር በርካታ ተመልካቾችን እያተረፈ የመጣ ሲሆን፣ ዘንድሮም ለ24ኛ ጊዜ በቅርቡ ውድድሩ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ውድድር ባል ሚስቱን በትከሻው ላይ ተሸክሞ በርካታ መሰናክሎችን ማለፍ እንደሚጠበቅበት ሮይተርስ ያሰራጨው ዘገባ ያመለክታል፡፡
በፊንላንዷ ከተማ 4 ሺ ነዋሪዎች ብቻ የሚገኙ ቢሆንም ፣ በየአመቱ ወድድሩን ለመከታተል ከተማዋ በሺዎች በሚቆጠሩ ጎብኚዎች ትጨናነ ቃለች፡፡
ውድድሩ በዓለም ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣ ሲሆን፣ በአንዳንድ ሀገሮችም የፊንላንዱ ውድድር ከመካሄዱ አስቀድሞ ውድድሮቹን ማካሄድ ተጀምሯል፡፡ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ፖላንድ፣ እንግሊዝ ዘንድሮ አስቀድሞ ውድድሩ የተካሄደባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡
በዚህ ከባድ ፉክክር በሚታይበት ውድድር ታዲያ ዘንድሮ የሉቲኒያን ዜጎች የሆኑት ጥንዶች ሻምፒዮና በመሆን ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ማጣጣም ችለዋል፡፡
በውድድሩ ከተሳተፉ ከ12 በላይ ጥንዶች መካከል ቪይታውታስ ኪርክሊያስካስ እና ባለቤቱ ኔይያንጋ ኪሪክሊዩስከየኔ አንደኛ በመውጣት ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በውድድሩም 253 ነጥብ 5 ሜትር ርቀት ኩሬ እና የመሳሰሉት መሰናክሎች ባሉበት ሮጠዋል፡፡ ውድድሩንም በአንድ ደቂቃ ከስድስት ሰከንድ ነው ያጠናቀቁት፡፡
አዲስ ዘመን ሐምሌ 9/2011