አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ አየር ኃይል ‘’ጸሐይ 2’’ የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሠራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ሥራ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት የጣለ ነው ።የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።
አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ‘’ጸሐይ 2’’ የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሠራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች መሆኗንም ጠቁመው፤ ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ህዳር 20/2017 ዓ.ም