የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን (ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም) መጠናቀቅ ከነበረባቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ቢሆንም፤ ግንባታው ተጓቶ እስካሁን` ድረስ አፈጻጸሙ ከ44 በመቶ ማለፍ አልቻለም፡፡ የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ተባባል ውድነህ ፕሮጀክቱ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እና የወደፊት አቅጣጫውን አስመልክቶ ከአዲስ ዘመን ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡:
አዲስ ዘመን፡- የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መቼ ተጀመረ? አቶ ተባባል፡- የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በሀገራችን ከሚከናወኑ ሜጋ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡ በዓመት 300ሺ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ የግንባታ ሥራው በ2004 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ በሁለት ዓመት ማለትም በ2006 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ነበር እቅድ የተያዘው፡፡ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ደግሞ የተቋቋመው በ2005 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ስራውን የጀመረው በ2006 ዓ.ም ሲሆን ኮርፖሬሽኑ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክትን በባለቤትነት እንዲያስተዳድር የተደረገው በግንቦት 2006 ዓ.ም ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እና ፕሮጀክቱን በሚገነባው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) መካከል የነበረው ስምምነት ምን ዓይነት ነው? አቶ ተባባል፡- የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ገንብቶ ወደ ሥራ አስገብቶ ማስተላለፍ ወይም ቢውልድ ኦፕሬት ኤንድ ትራንስፈር (BOT) በሚባለው መንገድ ከኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ፈጽሞ ነው ሲሰራ የነበረ፡፡ በ2006 ዓ.ም የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አንድ ላይ ተገናኝተው የመጀመሪያ የፕሮጀክት ግምገማ ሲደረግ ፋብሪካው 22 በመቶ ተገንብቶ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ አዲስ የመርሐ ግብር ክለሳ እየተደረገ ፕሮጀክቱ እንዴት ይቀጥል የሚለውን በማማከር የሚያግዝ አማካሪ እንዲቀጠር ተደርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እያማከረ ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም እንደ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች ሁሉ ትልቅ ተግዳሮት የሆነው ፕሮጀክቱን በሚገነባው አካል (ሜቴክ) የፕሮጀክት አስተዳደር ክህሎት እጦት ፋብሪካው በታቀለበት ጊዜ መጠናቀቅ አልቻለም፡፡ በተለይ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለእኛ ሀገር አዲስ መሆኑ፤የፋብሪካው ግንባታ ውስብስብ ቴክኖሎጂና ጥንቃቄ መፈለጉ በታሰበው አኳኋን እንዳይጠናቀቅ አድርጓል፡፡ ሜቴክ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ከዚህ ቀደም ከተሰሩት ተመልክቶ ሊገነባ ይችላል፡፡ ለአብነት ያህል የስኳር ፋብሪካ በሚገነባበት ወቅት ከዚህ ቀደም ካሉ የስኳር ፋብሪካዎች ተሞክሮ መቅሰም ይችላል፡፡ በእኛ ሀገር ልምድ ለመውሰድ የሚያስችሉ የማዳበሪያ ፋብሪካዎች በሌሉበት የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በመጀመሩ በታቀደው መልኩ ለማስኬድ አላስቻለውም፡፡ አዲስ ዘመን፡- ፕሮጀክቱ አሁን በምን ደረጃ ላይ ነው ያለው? አቶ ተባባል፡- በአሁኑ ወቅት ግንባታው 44 በመቶ ተጠናቋል፡፡ በታቀደው መሰረት በ2006 ዓ.ም ስላለቀ፤ የተከለሰ መርሐ ግብርን መሰረት በማድረግ በ2008 ዓ.ም ይጠናቀቃል የሚል ግብ አስቀምጠን ነበር፡፡ በ2008 ዓ.ም ባለማለቁ በ2009 ዓ.ም ያልቃል የሚል ሌላ መርሐ ግብር ነበረን፡፡ ከዚያ ደግሞ በ2010 ዓ.ም ነሐሴ ያልቃል የሚል ሌላ ግብ ተቀምጦ ነበር፡፡ ከአማካሪያችን ጋር የነበረን ስምምነትም ነሐሴ 2010 ዓ.ም የፋብሪካው ግንባታ ይጠናቀቃል የሚል ስለነበር፤ ከተቋሙ ጋር ያለውን ስምምነትም እስከ ጥቅምት 2011 ዓ.ም ድረስ ስናድስ ነበር፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ ሂደት እጅግ አዝጋሚ ነው፡፡ አዋጪነቱንም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ ፋብሪካው በባንክ ብድር የሚራ በመሆኑ፤ ኮርፖሬሽኑን በየወሩ 90 ሚሊዮን ብር የባንክ ወለድ ለመክፈል ተገዷል፡፡
በእዚህም የተነሳ የሥራ አመራር ቦርዱ እና ማኔጅመንቱ ከአማካሪው ጋራ በመሆን የመፍትሄ ሀሳብ ለቀድሞው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር አቅርቦ፤ ሚኒስትሩም የችግሩን ን አሳሳቢነት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስተላልፎ ነበር፡፡ የማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ ውል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቋርጦ በሽርክና የሚቀጥልና የፋይናንስ ምንጭ ይዞ የሚመጣ አካል ተፈልጎ ሥራው እንዲሰጥ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በመስከረም 2011 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ሜቴክም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር አማካኝነት በግልባጭ እንዲያውቀው ተደርጓል፡፡ አሁን በእኛ በኩል የርክክብ ሂደቱን በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ማከናወን ይጠበቃል፡፡ ሜቴክ፣ አማካሪ ድርጅቱ እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የርክክብ ሂደቱን እንዴት ነው የምንፈጽመው የሚለውን በጋራ ተነጋግረናል፡፡ የርክክብ ሂደቱ ሁለት አይነት መልክ ይኖረዋል፡፡ አንደኛው የሰነድ ርክክብ ሲሆን፤ የዲዛይንን ጨምሮ የማንኛውም ሶፍት እና ሀርድ ኮፒ ሰነድ ርክክብ ይፈጸማል፡፡ ሲቪልና መካኒካል ምህንድስናን የተመለከቱ ሰነዶች ርክክብ ይፈጸማል፡፡ ሜቴክ በንዑስ ኮንትራክተርነት የሚያሰራቸው አካላት አሉ፡፡ እኛ የምንፈልጋቸው የሜቴክን የቴክኒክ ሰነዶችን ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ ንዑስ ኮንትራክተሮች ጋር ሜቴክ የተፈራረማቸው ህጋዊ የሆኑ የስምምነት ሰነዶችንም ጭምር ነው፡፡ አንዳንድ ለማዳበሪያ ፋብሪካ አስፈላጊ የሆኑ ከውጭ ሀገራት የመጡና የተተከሉ ዕቃዎች አሉ፤ እነዚህ የተገዙበት ሰነድ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን በህጋዊ መንገድ ርክክብ መፈጸም ይገባል፡፡
በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ ወደ 20 ሚሊዮን ብር አካባቢ ኮርፖሬሽኑ የካሳ ክፍያ ፈጽሟል፡፡ ስለ ካሳ ክፍያውም መረጃ እንፈልጋለን፡፡ በርክክቡ የሚካተቱ ሌሎች ሰነዶችም አሉ፡፡ የሰነዶቹ ርክክብ ተጀምሯል፡፡ የእነዚህን ሰነዶች ርክክብ ከጨረስን በኋላ የሳይት ርክክብ ይፈጸማል፡፡ ሳይት የተተከሉ መሳሪያዎችና በወርክ ሾፕ ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች አሉ፡፡ እነዚህን ቼክ ሊስት በማዘጋጀት ርክክብ እናካሂዳለን፡፡ እስከ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሳይቱንም የሰነዱንም ርክክብ ለመጨረስ አቅደናል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል አቅሙ ላለውና ፋይናንሱን ይዞ ለሚመጣ ድርጅት ስራውን ለመስጠት የሰነድ ዝግጅት በመከናወን ላይ ነው፡፡ በአጋርነት የሚገነባ ድርጅትም እየተፈለገ ሲሆን፤ ካልተሳካ አነስተኛ የወለድ ምጣኔ ካለውና ገንዘብ ይዞ ከሚመጣ ድርጅት ጋር ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ መንግሥት ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል ፍላጎት አለው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሀገር ውስጥ ማዳበሪያ ፋብሪካ ማቋቋም ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውና ፋይዳውም ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡ 85 በመቶ አርሶ አደር ማህበረሰብ ይዞ ማዳበሪያ ከውጭ እያስገቡ መቀጠል አይቻልም፡፡ የፕሮጀክት አስተዳደር ክህሎት እና ችሎታ ያለውን አካል ፈልጎ ያለመስራት ክፍተት እንጂ ችግር የፈጠረው፤ ማዳበሪያ ፋብሪካ ለሀገራችን እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ አቅም ካለው አካል ጋር በመሆን ፋብሪካው ይገነባል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ለማዳበሪያ ፋብሪካው ግንባታ የተያዘው በጀት ምን ያህል ነበር፤ የገንዘብ ምንጩስ ከየት ነው? አቶ ተባባል፡- ለማዳበሪያ ፕሮጀክቱ የተበጀተው 9 ቢሊዮን 639 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በባንክ ብድር የሚሰራ ሲሆን፤ እስካሁን ወደ 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ ይህም 60 በመቶ ክፍያ እንደተፈጸመ ያሳያል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ፕሮጀክቱ ገና 44 በመቶ እንደሆነ ቀደም ብለው ገልጸውልኛል፡፡ አሁን ደግሞ 60 በመቶ ክፍያ እንደተፈጸመ አንስተውልኛል፡፡ ፋብሪካው 44 በመቶ ላይ እያለ 60 በመቶ ክፍያ እንዴት ልትፈጽሙ ቻላችሁ? አቶ ተባባል፡- አዎ አፈጻጻሙ 44 በመቶ እንደሆነ አንስቼያለሁ፡፡ ያለ ምክንያት አይደለም 60 በመቶ ክፍያ የፈጸምነው፡፡ ህግና ህግን ተከትለን ነው፡፡ ከህግ ውጭ የፈጸምነው ክፍያ የለም፡፡ የክፍያ ስርዓታችን እንዲሻሻል አድርገን ነው የፈጸምነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በ2004 ዓ.ም የተጀመረውን ሥራ በ2006 ዓ.ም አፈጻጸሙ 22 በመቶ ብቻ እያለ ነበር የተረከበው፡፡ በውሉ መሰረት ግን 2006 ዓ.ም የፋብሪካው ግንባታ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ ለዚህ መዘግየት ምንም አንኳን የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም የፕሮጀክት አስተዳደር ክህሎት ማነስና የኮንትራክተሩ አቅም ውስንነት ዋነኞቹ ምክንያቶች መሆናቸውን ብናውቅም በወቅቱ ሲገመገም ከተነሳው ውስጥ የክፍያ አፈጻጸም ስርዓቱ እንዲሻሻል የሚል ነው፡፡ የአከፋፈል ስርዓቱ ተሻሽሎ ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ ማሽነሪዎችና እቃዎችን ከውጭ ሀገር ለማስመጣት ኤል ሲ መክፈት ያስፈልጋል፤ ገንዘቡንም ቅድሚያ መክፈል አለበት፡፡ በዓይን የሚታየውን ብቻ መሰረት አድርጎ በተሰራው ሥራ ልክ ክፍያ እንፈጽም ከተባለ ለስራው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችን ማስመጣት አይቻልም፡፡ ስለዚህ የክፍያ ስርዓቱን ብናሻሽለው በሚል ከፊዚካል አፈጻጸም ይልቅ ፋይናንሱን እንዴት ተጠቀመበት የሚለው እየታየ እንዲለቀቅለት የኮንትራት ስምምነቱ ተሻሻለ፡፡ በመጀመሪያም እንደማንኛውም ኮንትራክተር በዓለም አቀፍ ደረጃም በተለመደው አሰራር መሰረት 30 በመቶ ቅድመ ክፍያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በባለቤትነት ፕሮጀክቱ ከመያዙ በፊት በቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተፈጽሞ ነበር፡፡ አዲስ የተሻሻለው የፋይናንስ ስምምነት፤ በፊት የወሰደው ገንዘብ ሥራ ላይ መዋሉ ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀጥለው ዙር ይለቀቃል ይላል፡፡ ስለዚህ በአዲሱ ስምምነት መሰረት የትኛውንም አይነት ክፍያ አማካሪያችን እያረጋገጠ ገንዘቡ ሥራ ላይ ውሏል ባለው መሰረት ነው የለቀቅነው፡፡ እንዲያውም ለሦስተኛ ጊዜ ገንዘብ እጥረት አለብኝ፤ በ60 በመቶ ላይ ተጨማሪ 20 በመቶ ክፍያ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ስጡኝ ሲል፤ አይሆንም ስምምነቱ ቢኖርም እንኳን ሥራው አጥጋቢ ስላልሆነና በተደረገው ምርመራ የሁለተኛውን ክፍያ መቶ ፐርሰንት እንዳልተጠቀመበት አማካሪው ስላረጋገጠ አይከፈልም ብለን ከልክለናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- በየወሩ 90 ሚሊዮን ብር የባንክ ወለድ እየተከፈለ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ የተከፈለው የባንክ ወለድ ምን ያህል ነው? አቶ ተባባል፡- እስካሁን ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የባንክ ወለድ ተከፍሏል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በተሻሻለው መርሐ ግብር መሰረት ነሃሴ 2010 ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ታስቦ ስለነበር፤ ዋናው የብድር ገንዘብ መመለሻ የፊታችን ግንቦት 2011 ዓ.ም ነው የሚጀመረው፡፡ በየሦስት ወሩ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ለባንክ እንድንመልስ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡
ስለዚህ አሁን እኛ ለመንግሥት ልዩ ውሳኔ እንዲሰጠው እናቀርባለን፡፡ ፕሮጀክቱ ገና 44 በመቶ ላይ ባለበት ለባንክ ግን በየወሩ እየተከፈለ ያለውን 90 ሚሊዮን ብር ብቻ ሳይሆን፤ ዋናውንም ብድር ከግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በውለታ ቱ ከመያዙ በፊት በቀድሞ የፕራይቬታይዜሽን እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተፈጽሞ ነበር፡፡ አዲስ የተሻሻለው የፋይናንስ ስምምነት፤ በፊት የወሰደው ገንዘብ ሥራ ላይ መዋሉ ከተረጋገጠ በኋላ የሚቀጥለው ዙር ይለቀቃል ይላል፡፡ ስለዚህ በአዲሱ ስምምነት መሰረት የትኛውንም አይነት ክፍያ አማካሪያችን እያረጋገጠ ገንዘቡ ሥራ ላይ ውሏል ባለው መሰረት ነው የለቀቅነው፡፡ እንዲያውም ለሦስተኛ ጊዜ ገንዘብ እጥረት አለብኝ፤ በ60 በመቶ ላይ ተጨማሪ 20 በመቶ ክፍያ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ስጡኝ ሲል፤ አይሆንም ስምምነቱ ቢኖርም እንኳን ሥራው አጥጋቢ ስላልሆነና በተደረገው ምርመራ የሁለተኛውን ክፍያ መቶ ፐርሰንት እንዳልተጠቀመበት አማካሪው ስላረጋገጠ አይከፈልም ብለን ከልክለናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- በየወሩ 90 ሚሊዮን ብር የባንክ ወለድ እየተከፈለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ የተከፈለው የባንክ ወለድ ምን ያህል ነው? አቶ ተባባል፡- እስካሁን ወደ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የባንክ ወለድ ተከፍሏል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በተሻሻለው መርሐ ግብር መሰረት ነሃሴ 2010 ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ታስቦ ስለነበር፤ ዋናው የብድር ገንዘብ መመለሻ የፊታችን ግንቦት 2011 ዓ.ም ነው የሚጀመረው፡፡ በየሦስት ወሩ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ለባንክ እንድንመልስ ታሳቢ ተደርጎ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን እኛ ለመንግሥት ልዩ ውሳኔ እንዲሰጠው እናቀርባለን፡፡ ፕሮጀክቱ ገና 44 በመቶ ላይ ባለበት ለባንክ ግን በየወሩ እየተከፈለ ያለውን 90 ሚሊዮን ብር ብቻ ሳይሆን፤ ዋናውንም ብድር ከግንቦት 2011 ዓ.ም ጀምሮ በውለታ ስምምነት መሰረት ለመክፈል እንድንዘጋጅ ደብዳቤ ከአበዳሪው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጽፎልናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- እስካሁን 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የባንክ ወለድ ተከፍሏል፡፡ በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ ግማሽ እንኳን አልተጠናቀቀም፡፡ ታዲያ ይህ ፕሮጀክት ምን ያህል አዋጭ ነው ተብሎ ይታሰባል? አቶ ተባባል፡- በፊት በነበረው ጥናት መሰረት የዚህ ፕሮጀክት የአዋጭነት ጊዜው ያለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ነው፡፡
የፕሮጀክቱ አዋጭነት በተመለከተ ያጋጠመውን በተለያዩ መድረኮች ስናነሳ ቆይተናል፡፡ በየሩብ ዓመቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ግምገማችንን ስናቀርብ የፕሮጀክቱ አዋጭነት ጊዜ ማለፉን ስናሳውቅ ነበር፡፡ ለሥራ አመራር ቦርዳችንም ይህንኑ ስናነሳ ቆይተናል፡፡ ይህን በሚመለከት አንዱ የቤት ሥራ የሚሆነው የፕሮጀክቱን ጥናት እንደገና መከለስ ነው፤ ጥናቱ ሲከለስ የፕሮጀክቱን ትክክለኛ ስዕል ለማየት ይረዳናል፤ አማካሪያችን ይህን ሥራ እንዲሰራ እናደርጋለን፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አዲስ በሚደረገው ጥናት አዋጭነቱ አጠራጣሪ ሆኖ ቢገኝ እንኳን፤ መንግሥት እንደመንግሥት ስትራቴጂ ይተወዋል ብዬ አላምንም፡፡ ምክንያቱም እስካሁን 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የሚሆን ወጪ ወጥቶበታል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢው ማህበረሰብ በጉጉት የሚጠብቀው ፕሮጀክት ነው፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ ብቻም ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ አርሶ አደር ማዳበሪያ በሀገሬ ተመርቶ ተጠቃሚ እሆናለሁ የሚል ተስፋ ሰንቋል፡፡ ስለዚህ መንግሥት እንኳን መደጎም ካለበት እስከተወሰነ ዓመት የተወሰነ ድጎማ ተደርጎለትም ቢሆን ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል፡፡ ሀገራት የተለያዩ የድጎማ አይነቶች አሏቸው፡፡
ይህንን ፕሮጀክትም የተወሰነ ወቅት ድረስ ደጉሞ እውን ማድረግ ይጠበቃል፡፡ የመንግሥትም ሃሳብ ይህ ይሆናል ብዬ ነው የምጠብቀው፡፡ በነገራችን ላይ ያዩ የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት ከተጀመረ በኋላ ከሞሮኮ መንግሥት ጋራ በኦጋዴን ላይ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ተጠቅሞ ከእዚያው ሀገር እንደ ግብዓት የሚያስፈልግ አሲድ በማምጣት በሽርክና የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ታቅዶ ነበር፡፡ ያዩ ላይ የሚገነባውን በድንጋይ ከሰል የሚሰራውንና የኦጋዴን ነዳጅ በመጠቀም ማዳበሪያ ለማምረት ፋብሪካ ለመገንባት የታሰበውን ስናነጻጽረው በኢንቨስትመንትም በኦፕሬሽናል ወጪውም ተፈጥሮ ጋዙን ተጠቅሞ የሚመረተው ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ በአማራጫችን ለመንግሥት ውሳኔ እኛ ፕሮፖዛል ስናቀርብ አንድ ቶን በድንጋይ ከሰል ማዳበሪያ ለማምረት ከሚወጣው ወጪ በተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያ ለማምረት የሚወጣው ወጪ አነስተኛ እንደሆነ በመረጃ አስደግፈን አቅርበናል፡፡ ይህ መረጃም እየታወቀ ጭምር ነው ፕሮጀክቱ ይቀጥል የሚለው የመንግሥት ውሳኔ የተላለፈው፡፡ አዲስ ዘመን፡- እርሶም እንደገለጹልኝ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክትን ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በባለቤትነት ተረክቧል፡፡ ግንባታው ሲጓተት፤ የጥራት ችግር መኖሩ ሲነሳና የህግ ጥሰቶች ሲፈጸሙ ኮርፖሬሽኑ ለምን እርምጃ መውሰድ አልቻለም? ዶ ነበር፡፡
ያዩ ላይ የሚገነባውን በድንጋይ ከሰል የሚሰራውንና የኦጋዴን ነዳጅ በመጠቀም ማዳበሪያ ለማምረት ፋብሪካ ለመገንባት የታሰበውን ስናነጻጽረው በኢንቨስትመንትም በኦፕሬሽናል ወጪውም ተፈጥሮ ጋዙን ተጠቅሞ የሚመረተው ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ በአማራጫችን ለመንግሥት ውሳኔ እኛ ፕሮፖዛል ስናቀርብ አንድ ቶን በድንጋይ ከሰል ማዳበሪያ ለማምረት ከሚወጣው ወጪ በተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያ ለማምረት የሚወጣው ወጪ አነስተኛ እንደሆነ በመረጃ አስደግፈን አቅርበናል፡፡ ይህ መረጃም እየታወቀ ጭምር ነው ፕሮጀክቱ ይቀጥል የሚለው የመንግሥት ውሳኔ የተላለፈው፡፡ አዲስ ዘመን፡- እርሶም እንደገለጹልኝ የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክትን ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በባለቤትነት ተረክቧል፡፡ ግንባታው ሲጓተት፤ የጥራት ችግር መኖሩ ሲነሳና የህግ ጥሰቶች ሲፈጸሙ ኮርፖሬሽኑ ለምን እርምጃ መውሰድ አልቻለም? አቶ ተባባል፡- ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጠናቀቅ ከነበረባቸው ፕሮጀክተሮች አንዱ ነው፡፡ እኛ የፋብሪካው ባለቤት ብንሆንም የኛ ተቋም የተመሰረተው ፕሮጀክቱ ከተጀመረ በኋላ ነው፡፡ እኛ ከመምጣታችን በፊት ለሜቴክ የፋብሪካው ግንባታ የተሰጠው ‹‹ቢውልድ ኦፕሬት ኤንድ ትራንስፈር›› በተሰኘ የስምምነት ሞዴል እንዲሰራ ነው፡፡
ይህ የስምምነት ሞዴል ኮንትራክተሩ ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ፋብሪካውን ገንብቶ ወደ ሥራ አስገብቶ ለባለቤቱ እንዲያስተላልፍ ይፈቅዳል፡፡ ስለሆነ ሁሉንም ነገር ሲሰራ የነበረው ሜቴክ ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመ በኋላም በባለቤትነት ይዞታል ቢባልም፤ ለፕሮጀክቱ አማካሪ የመቅጠር፤ አስተያየቶችን የመስጠትና ፋይናንስ የማመቻቸት ኃላፊነት ብቻ ነው በመንግሥት የተሰጠው፡፡ ከዚህ ስምምነት የተነሳ አንዳንድ ጊዜ አማካሪው አስተያየት ሲሰጥ እንኳን ተፈጸሚ አይሆንም፡፡ ከአማካሪው ጋር ያለን ስምምነት ራሱ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ስራውን በሚመለከት አስተያየት እስከመስጠት እንጂ አስገዳጅ ትዕዛዝን ማስተላለፍን አላካተተም፡፡ ምክንያቱም ስምምነቱ ‹‹ቢውልድ ኦፕሬት ኤንድ ትራንስፈር›› ነውና፡፡
ስለዚህ ከዲዛይን ጀምሮ ባለቤቱ ራሱ ሜቴክ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በተለመደው የኮንትራክተርና የባለቤት አስራር ውል የተፈጸመ ቢሆን በታቀደለት ዕቅድ መሰረት እየሄደ ስላልሆነ ፕሮጀክቱን እቀማለሁ ማለት ይቻላል፡፡ በዚህኛው ውል ግን ያንን ማድረግ አይቻልም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በስምምነቱ መሰረት ሁለታችንም የመንግሥት ድርጅት በመሆናችን ስራውን በተመለከተ መግባባት ባይቻል ችግራችን የሚፈታው መንግሥት ጋር በመቅረብ ነው፡፡ እኛ ግን በተለያዩ መድረኮች ይህ ፕሮጀክት እየዘገየ ነው፤ ሜቴክም ሥራውን በታቀደለት ፍጥነት እየሠራ አይደለም፤ የጥራት ችግሮችም አሉ ብለን ስናሳውቅ ነበር፡፡ ችግሩ ለምን ተከሰተ እንዴትስ ይፈታል በሚል ትንተና ነው ለመፍታት የምንሄደው፡፡ ችግሮች እንዳሉ በሦስትዮሽ ስብሰባም (ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ ሜቴክና አማካሪ ድርጅቱ) ፤ በተለያዩ መድረኮች ላይም ስናነሳና ግብረ መልስ ስንሰጥ ነበር፡፡ ከዚያ አልፎም ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ አሳውቀናል፡፡ የአገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት እስከሆነው የተወካዮች ምክር ቤት ድረስ ይህ ጉዳይ ደርሷል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የሀገር ውስጥ አቅም ለመፍጠር በሚል በልዩ የፖለቲካ ውሳኔ ነው ለሜቴክ የተሰጠው፡፡ ሌሎችን አስጠግቶ ሊማር የሚችልበት ዕድልም ተሰጥቶታል፤ ግን አልተጠቀመበትም፡፡ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተለያየ ጥረት አላደረገም ማለት ግን አይደለም፡፡ አቅሙ የሚፈቅደውን ሲያደርግ ነው የነበረው፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ስምምነቱ የሚፈቅድልን ይህን ብቻ ነውና፡፡ አዲስ ዘመን፡- ሜቴክ ከ60 በመቶ በላይ ክፍያ ወስዷል፡፡ በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ ከ 44 ከመቶ አላለፈም፡፡ ስለዚህ ሜቴክ የወሰደው እላፊ ገንዘብ የለም፤ ካለስ ምን ይደረጋል? አቶ ተባባል፡- ከርክክብ በኋላ ግምገማ (ኢቫሉዌሽን) ይኖራል፡፡ ርክክብ ከተደረገ በኋላ ተመን ይወጣል፡፡ የፕሮጀክቱ አፈጻጸምና ለሜቴክ የተከፈለው ገንዘብ መጠን ተገናዝቦ መንግሥት እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡
የእኛ ድርሻ የሚሆነው ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ማሳወቅ ነው፡፡ የሚረከበው ድርጅት ባለው ላይ የሚቀጥላቸው ሥራዎች ይኖራሉ፤ ለእነዚህ ዋጋ ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ አንዳንዶቹን ሥራዎች ደግሞ አልቀበላቸውም ሊል ይችላል፡፡ አልቀበላቸውም ካለ ምን አልባት እነዚያ የተሰሩ ስራዎች ከጥቅም ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አዲስ ዘመን፡- ፕሮጀክቱ በእርግ ጠኝነት መቼ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል? አቶ ተባባል፡- መጀመሪያ አማካሪውም ሆነ ሜቴክ የመውጫ ወይም የመዝጊያ ሪፖርት ለባለቤቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሪፖርቱ መጀመሪያ የታሰበው ምንድን ነው? እስካሁን ምን ተሰርቷል? ምን ይቀራል? የሚለውን ይለያል፡፡ አቅም ያለው የውጭ ድርጅት ስንጋብዝ ቀሪውን ሥራ እንዴት ነው የሚሰራው? በምን ያህል ዋጋ ይሰራል? በምን ያህል ጊዜ ይጠናቀቃል? የሚለውን ማወቅ ይቻላል፡፡ እኛ አሁን ላይ የያዝነው ፕሮግራም ግን እስከ ጥር 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ከሰነድ እስከ ሳይት ያለውን የፕሮጀክት ርክክብ ለመፈጸም ነው፡፡ አዲስ ዘመን፡- ለሰጡን ሰፊ ማብራሪያ በጣም እናመሰግናለን! አቶ ተባባል፡- እኔም አመሰግናለሁ !
አዲስ ዘመን ታህሳስ 4 ቀን 2011ዓ.ም
መላኩ ኤሮሴ