‹‹ታማኝ ግብር ከፋዮች የኢትዮጵያን ክብር የሚያስጠብቁ ናቸው›› – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Normal
0

false
false
false

EN-US
X-NONE
X-NONE

አዲስአበባታማኝግብርከፋዮችየኢትዮጵያንክብርየሚያስጠብቁናብልፅግናእንዲረጋገጥየሚተጉናቸውሲሉጠቅላይሚኒስትርዐቢይአሕመድ (/) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) 6 ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት መርሐ ግብር ትናንት በአንድነት ፓርክ ሲካሄድ እንደገለጹት፤ ግብር መክፈል ለታማኝ ግብር ከፋዮች ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ማኖር ነው። ታማኝ ግብር ከፋዮች የኢትዮጵያን ክብር የሚያስጠብቁና ብልፅግና እንዲረጋገጥ የሚተጉ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልፅግና የሚረጋገጠው በኢትዮጵያውያን ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብልፅግናን ለማረጋገጥና የሀገር ክብር ለማስጠበቅ የሚቻለው በታማኝነት ግብር በመክፈል እንደሆነ ተናግረዋል።

በታማኝ ግብር ከፋዮች ልክ መንግሥትም እንደሚታመን አመልክተው፤ ከግብር የተገኘውን ገቢ በዓይን በሚታዩና በእጅ በሚጨበጡ የልማት ሥራዎች ላይ በማዋል በከተሞች፣ በግብርና እና በመሠረተ ልማት ግንባታዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ግብር መክፈል ለአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ የሀገር ግንባታ ለማካሄድ እንደሚጠቅም ጠቁመው፤ በከተሞች ሆነ ከከተሞች ውጪ መሠረተ ልማቶች የተገነቡት በታማኝ ግብር ከፋዮች በተገኘ ገንዘብ መሆኑን አውስተዋል። ያደጉ ሀገራት እዚህ የደረሱት ጥረው ግረውና በታማኝነት ግብር ከፍለው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ታማኝ ግብር ከፋይ ኩባንያዎች አሁን ያለው ትውልድ ለሀገር ታማኝና ታታሪ እንዲሆን ልምዳቸውን ማስተላለፍ እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ግብር የመሰብሰብ መጠንና የግብር ከፋዮች ቁጥር እያደገ እንደመጣ ገልጸው፤ ይህን ገቢ ይበልጥ ለማሳደግና የሀገር ግንባታን ለማፋጠን በታማኝነት ግብር የመክፈል ባሕል እየዳበረ ሊመጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመንግሥት በኩል የተጀመረውን የገቢ አሰባሰብ የአሠራር ማሻሻያን በማጠናከር፣ ሌብነትን በመቀነስና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራርን በማስፋፋት ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ለማሳደግ እንደሚሠራም ጠቁመዋል።

በስድስተኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የእውቅና ሽልማት መርሐ ግብር በተለያዩ መስፈርቶች 66 ኩባንያዎች በፕላቲኒየም፣ 165 ኩባንያዎች በወርቅ፣ 319 ኩባንያዎች የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆኑ ባለፉት አራት ዓመታት በታማኝነት ከፍተኛ ግብር በመክፈላቸው ተሸላሚ የሆኑ 20 ኩባንያዎች ደግሞ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዕለቱም 2016 በጀት ዓመት የተሻለ የታክስ ሕግ ተገዢነት ላስመዘገቡ 550 ግብር ከፋዮች እውቅናና ምስጋና የተሰጠ ሲሆን ለሀገሪቱ የገቢ ዕድገት የእነዚህ ግብር ከፋዮች ሚና ትልቅ መሆኑም ተጠቅሷል።

በሁለቱም ተቋማት በተደረጉ ጥረቶች 2016 በጀት ዓመት ግብር ለመሰብሰብ በእቅድ ከተያዘው 529 ቢሊዮን ብር ውስጥ 512 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል። ይህ አፈጻጸም 2015 በጀት ዓመት ከነበረው 442 ቢሊዮን ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ እድገት እንዳለው ታውቋል።

በተያያዘ ዜና እጅግ አስደናቂ የሆነውን አንድ ሚሊዮን ቶን ቡና የማምረት ግባችንን አሳክተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።

ቡናችን ለብልፅግናችን በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት በተካሄደው ሀገራዊ የቡና ኤግዚቢሽንና የዕውቅና መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡና ምርት ላይ ለተሠማሩ ውጤታማ አርሶ አደሮች፣ አልሚዎች፣ ቡና ላኪ ማኅበራት እና ባለሀብቶች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እጅግ አስደናቂ የሆነውን አንድ ሚሊዮን ቶን ቡና የማምረት ግባችንን መተናል ብለዋል።

ጌትነት ምሕረቴ

 አዲስ ዘመን ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You