የፋሽን ዲዛይን ሕይወትን የጀመረችው ገና በአስራዎቹ እድሜ ላይ ሳለች ነው:: በልጅነቷ ለስዕልም የተለየ ፍላጎት ነበራት፤ በተለያዩ አጋጣሚዎች የምታያቸው የልብስ ዲዛይኖችም ይስቧት ነበር::
ሙዚቃም በልጅነቷ የተሳበችበት ቢሆንም፣ ከሙዚቃ ይልቅ በሙዚቃ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ የምታያቸው ሞዴሎች እና የሙዚቀኞች አልባሳት ዲዛይኖች ወደ ፋሽን ኢንዱስትሪው እንድትሳብ አድርጓታል:: ዲዛይነር ማሕሌት አፈወርቅ::
ዲዛይነሯ ለረጅም ጊዜ የቆየ ማፊ ማፊ የተሰኘ የፋሽን ብራንድ ገንብታለች:: በማፊ ማፊ የፋሽን ብራንድ የኢትዮጵያን ባሕል ከዘመናዊ ዲዛይን ጋር በማቆራኘት በዓለም አቀፍ መድረክ ሥራዎቿን ስታቀርብም ቆይታለች:: ዓለም አቀፍ እውቅናን ማግኘት መቻሏን ገልጻለች::
ዲዛይነር ማሕሌት በሥራው ላይ የ15 ዓመት ልምድን አካብታለች፤ ሥራዋን በጀመረችበት ወቅት ጥራት ያለው የፋሽን ዲዛይን ትምህርት ቤት በሀገሯ አለማግኘቷ ፈተና ሆኖባት እንደነበር ታስታውሳለች:: ‹‹እኔ ፋሽን ዲዛይንን ስጀምር ስለ ፋሽን ዲዛይን ራሴን በራሴ ማስተማር ነበረብኝ›› ስትል ትገልጻለች ::
ይህም ጥራት ያለው የፋሽን ዲዛይን ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ መገንባት የረጅም ጊዜ ሕልሟ እንዲሆን አደረገ:: የማፊ ማፊ የፋሽን ዲዛይን ብራንድ ሥራ እየሰፋ ሲመጣ በፋብሪካው ውስጥ ለፋሽን ዲዛይን ፍላጎት ላላቸው ወጣቶች ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ወደ ሥልጠናውም መግባት እንደ ጀመረች ተናግራለች ::
‹‹ሥልጠና በምንሰጠበት ወቅት ፋሽን እያደገ እንደመጣና ብዙ ፍላጎት፣ ችሎታና አቅም ያላቸው ወጣቶች ማየት ቻልኩ›› የምትለው ዲዛይነር ማሕሌት፣ ትምህርት ቤቱ በሀገራችን እና በሌላው ዓለም ዘንድ ያለውን የእውቀት ክፍተት ለመሙላት ማለሙን ገልጻለች::
እሷ እንዳለችው፤ የፋሽን ኢንዱስትሪ በሌላው ዓለም ትኩረት ተሰጥቶት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት እና ውበት ብቻ ሳይሆን ታሪክን ጭምር መናገር የሚችል ኢንዱስትሪ መሆን ችሏል::
በሀገሪቱ ይህን ዘርፍ ለማሳደግ ጥራት ያለው የፋሽን ዲዛይን ትምህርት ቤት ያስፈልጋል የሚል ሕልምም የነበራት ዲዛይነሯ፣ ይህ ሕልሟ እውን ሆኖ የማፊ ፋሽን አካዳሚ እና ቤተሙከራ በአዲስ አበባ እውን መሆኑን አስታውቃለች::
የአካዳሚውና ቤተሙከራው እውን መሆንን አስመልክቶ በተሰጠ መግለጫ ላይ እንደተጠቆመው፣ አካዳሚው በአፍሪካ የተሳካ ዓለማቀፋዊ ብራንዶችን መፍጠር የሚችሉ እና በከፍተኛ ሁኔታ የሠለጠኑ የፋሽን ባለሙያዎች የሚሠለጥኑበት ነው::
አካዳሚው አዳዲስ የፋሽን ዲዛይን አሠራሮችን ስኬታማ ማድረግ ከሚያስችሉ የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች ጋር በማጣመር የፋሽን ትምህርት ይሰጣል:: ሥርዓተ ትምህርቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የፋሽን አማካሪዎች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው:: ‹‹15 ዓመት ከቆየሁበት የፋሽን ኢንዱስትሪ እንዲሁም በሀገሪቱም ሆነ በአፍሪካ ያሉትን የዘርፉን ክፍተቶች በመለየት የተዘጋጀ ነው›› ብላለች::
ትምህርት ቤቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ዘመናዊ የመማሪያ ማሽኖችን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ብቁ የሆኑ የፋሽን አስተማሪዎችን ማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር ጠቅሳ፣ ይህን ክፍተት ለመሙላት አካዳሚው ከኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ ፣ በጣሊያን ሀገር ከሚገኘው ዩኒቨርሳል አርት አካዳሚ ጋር በመተባበር መመሥረቱን ጠቁማለች ::
በመግለጫው ላይ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌዜ፣ የዩኒቨርሳል አርት አካዳሚ የጣሊያን ተወካይ እና የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) ተወካዮች ተገኝተዋል::
ዲዛይነር ማሕሌት እንዳብራራችው፤ ትምህርት ቤቱ ከፋሽን ዲዛይን እውቀት በዘለለ ሠልጣኞች ያላቸውን አቅም በመጠቀም በፋሽን ኢንዱስትሪ ገቢ ማግኘት እና ውጤታማ መሆን የሚችሉባቸው ሀሳቦችም ተካተዋል:: ሥልጠናው ሠልጣኞች ከፋሽን ዲዛይን፣ ከፋሽን ቢዝነስ፣ ከፋሽን ፎቶግራፍ፣ ከፋሽን ስታይሊንግ፣ ከፋሽን ቴክኖሎጂ እና ከመሳሰሉት በመረጡት መስክ ሥልጠናውን እንዲከታተሉ ተደርጎ መዘጋጀቱንም ጠቁማለች::
በመግለጫው ላይ እንደተጠቆመው፤ የትምህርት ሥርዓቱ የሀገር በቀል ባሕላዊ እውቀትን ከዓለም አቀፉ ጋር በማስተሳሰር ተዘጋጅቷል:: ትምህርቱ የሚሰጠው በጣሊያን ባለሙያዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ባለሙያዎች ሲሆን፣ ዲዛይነሮች፣ የቢዝነስ አማካሪዎች፣ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ይሳተፉበታል:: ከፍተኛ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎች ወደጣሊያን ሀገር በመሄድ የተሻለ ሥልጠና እንዲያገኙ እንዲሁም በአፍሪካ እና በኤሽያ በሚደረጉ ዓለም አቀፍ የልምድ ልውውጦች ላይም እንዲሳተፉ ይደረጋል::
የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) ተወካይ እንደገለጹት፤ የሀገር ውስጥ እውቀት እና ዕድሎችን ከዓለም አቀፉ ጋር ለማስተሳሰር ይሠራል፤ ድርጅቱ ቴክኒካል የሆኑ የመሣሪያ ድጋፎችን በማድረግ ያግዛል::
የጣሊያኑ ዩኒቨርሳል አርት አካዳሚ ተወካይ በበኩላቸው የፋሽን ኢንዱስትሪ ለጣሊያን ዋነኛ ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ ከዚህ ልምድ ልትወስድ ይገባል ብለዋል::
አካዳሚው ሠልጣኞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው የፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር ማስተዋወቅ ያስችላል፤ ኢትዮጵያውያን የፋሽን ዲዛይነር ሠልጣኞች በሌላው ዓለም ላይ በመሥራት እና አቅማቸውን በማሳየት ለውጥ ማምጣት የሚችሉበትን ዕድልም ያመቻቻል::
ትምህርቱ የሦስት፣ የስድስት ወራት እና የአንድ ዓመት በሚል እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ እስከ 120 ተማሪዎች መያዝ እንደሚችልም ተገልጸል:: የትምህርት ቤቱ የፋሽን ፈጠራ ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ተማሪዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲመራመሩና ለወደፊቱ የዘርፉ ኢንዱስትሪ ሥራ እንዲያዘጋጁ ያስችላል ::
ተማሪዎች ሥልጠናቸውን ጨርሰው ሲመረቁ የራሳቸውን ቢዝነስ ማቋቋም፣ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በሥራ ቅጥር በመሥራት ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ፣ በውጭ ሀገር ተጨማሪ ትምህርቶችን ለመከታተል እንዲሁም ሽርክና መፍጠር አልያም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆኑ በማድረግ በኩልም የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸውም ተጠቁሟል::
ትምህርት ቤቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተደራሽነቱን የማስፋት እቅድ እንዳለው ጠቅሳ፣ ሥልጠናውን ለመውሰድ ወደ አካዳሚው የሚመጡ ሠልጣኞችን ለመቀበል አካዳሚው የራሱ የሆነ ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉትም ዲዛይነር ማሕሌት አስታውቃለች::
ሠራተኛው ጭራሽ እየሳቀ ያበሽቀው ጀመር:: በነገራችን ላይ ነገሮችን ንቆ መተው ትልቅ ጥቅም አለው:: ያንን ተሳዳቢውን በጣም ነው የሚያናድደው:: ሠራተኛው ሥራውን መሥራት ጀመረ:: ባለጉዳዩ ሲለፈልፍ ቆይቶ ትቶት ወጣ:: ግልግል ሆነ ማለት ነው!
እንግዲህ አንዳንዱ ሰው እንዲህ ነው:: የባንክ ሠራተኛው ጨዋ ባይሆን ኖሮ፣ ነገሩን ንቆ ባይተወው ኖሮ እነዚህ ሰዎች እስከመደባደብ ይደርሱ ነበር:: ሲደባደቡ ያየ ሰው ጥፋቱ የማን እንደሆነ ካላወቀ በሁለቱም ይፈርድ ነበር:: አንዳንድ ሰዎች በጣም ግርም ይላሉ:: ከይቅርታ ይልቅ ስድብ ይገዛቸዋል:: ይቅርታ ሲባሉ የተፈሩ ይመስላቸዋል::
ምንም እንኳን ችግሩ ያለው ከሁለቱም (ከአገልጋይም ከተገልጋይም) ቢሆንም ታጋሽነትና የሠለጠነ አሠራር የሚጠበቀው ግን ከአገልግሎት ሰጪዎች ነው:: ምክንያቱም ኃላፊነት ላይ የተቀመጡት የተሻለ ብቃት ኖሯቸው ነው:: ተወዳድረው ነው:: ሀገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ነው:: ሀገራዊ ኃላፊነት ሲባል የግድ በከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ብቻ መሆን የለበትም:: የአንድ ተቋም የጥበቃ ሠራተኛ ለዚያ ሥራ ኃላፊ ነው:: ሥራውም ሀገራዊ ሥራ ነው:: ሀገረ መንግሥት ሲባል የግድ ዳር ድንበሩ ብቻ አይደለም:: የአሠራር መዋቅሩ ጭምር ነው:: ስለዚህ አንድ ሀገር ሠለጠነች የሚባለው የአሠራር ሂደቱ የሠለጠነ ሲሆን ነው::
ሰዎች ሥነ ምግባርን መማር ያለባቸው በኃላፊነት ላይ ካሉ ሰዎች ነው:: በአገራችን የምናየው ነገር ግን በቁጣ መጀመር ነው:: ከአንድ ሳምንት በፊት ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ጋር በተያያዘ ጉዳይ አንድ የቀበሌ አገልግሎት ተቋም ሄጄ ነበር:: እርግጥ ነው በግሌ ለማማረር የሚያበቃ መጉላላት አላጋጠመኝም:: ያስተዋልኩት ችግርም የዚያ ቢሮ ሠራተኞች የተለየ ችግር ሳይሆን እንደ ሀገር የሠለጠነ አሠራር ባለመስረጹ ያጋጠመ ነው::
የተሰጠው ቅጽ ግልጽነት የለውም:: መጠይቆቹ አሻሚ ናቸው:: ቅጹን የሚሞሉ ሰዎች ‹‹እዚህ ላይ ምንድነው የሚሞላ?›› እያሉ አገልግሎት ሰጪዎችን ለመጠየቅ ይገደዳሉ:: ይህኔ ነበር በሁለቱም በኩል መሰለቻቸት የሚታየው:: አገልግሎት ሰጪዎቹ ሥራ እያቋረጡ ያን ሁሉ ሰው ማስረዳት ይሰለቻቸዋል:: ተገልጋዮች ደግሞ በግምት ቢሞሉት በኋላ ‹‹ትክክል አይደላችሁም›› ሊባሉ ነው::
በሌላው በጣም በተደጋጋሚ የማስተውለው ችግር ግን የትኛው ጉዳይ የት እንደሆነ አለማወቅ ነው:: አገልግሎት ሰጪዎች ሲጠየቁ ባለጉዳዩ የዚያ ቢሮ ነዋሪ የሆነ ይመስል ‹‹እንዴት ይሄን አታውቅም?›› የሚል ድምጸት ባለው ቁጣ ‹‹ማነው እዚህ ነው ያለህ?›› ብለው ይቆጣሉ:: ባለጉዳዩ የጠየቀውን ቢሮ በትህትና ከመጠቆም ይልቅ እነርሱ ጋ አለመሆኑን ብቻ በቁጣ የሚናገሩ አሉ:: ምንም እንኳን እንዲህ የሚያደርጉት በጣም ጥቂቶች ቢሆኑም በእነዚህ ጥቂቶች ምክንያት ግን ተቋሙ ይወቀሳል:: ተቋሙ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሀገራዊ አገልግሎቱም ይወቀሳል::
በሥራ ጫና ምክንያት መሰላቸት እንደሚኖር ይታመናል:: አንዳንዶቹ ግን በሚያስቅ ሁኔታ ወንበራቸው ላይ ጀርባቸውን አስደግፈው እያሽከረከሩ ስልካቸውን በመጎርጎር ላይ ሆነው ነው ባለጉዳይ ሲመጣ በቁጣ የሚጀምሩት:: ታዲያ እነዚህ አያናድዱም?
ቢቻል ሁሉንም በትዕግስትና በትህትና ማስተናገድ፤ ሰው ናችሁና በሥራ ጫና ምክንያት መዋከብ ቢኖርም ቢያንስ ግን በሠለጠነ መንገድ የሚስተናገደውን ሁሉ ባታደነባብሩ:: የቅድመ ቁጣ አገልግሎት አትስጡ!
ሰሚራ በርሀ
አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም