ሩሲያ የተንቀሳቃሽ ኑክሌር ሚሳይል ማስወንጨፊያ ሥርዓት ልምምድ አካሄደች

የሩሲያ ኃይሎች የያርስ ተንቀሳቃሽ የኑክሌር ሚሳይል ማስወንጨፊያ ሥርዓት ልምምድ ማድረጓ ተገልጿል።
ሩሲያ ይህን ልምምድ ስታደርግ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ሮይተርስ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ዘግቧል።
የሚሳይል ማስወንጨፊያ ሥርዓቱ (ላውንቸር) ሠራተኞች ከሞስኮ በምስራቅ አቅጣጫ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የቮልጋ ወንዝ ተፋስስ የማስመሰል ወይም ከጠላት እይታ የመሰወር እና የማንቀሳቀስ ልምምድ አድርገዋል ተብሏል።
ይህ ልምምድ የተካሄደው በነሀሴ ወር መጀመሪያ ላይ በሁለት የተለያዩ ግዛቶች የተካሄዱትን ተመሳሳይ ልምምዶች እና ሩሲያ በቤላሩስ ድንበር የታክቲካል ኑክሌር የጦር መሣሪያ ልምምድ ካደረገችበት ከሁለት
ሩሲያ የተንቀሳቃሽ ኑክሌር ሚሳይል ማስወንጨፊያ ሥርዓት ልምምድ አካሄደች
ወር ገደማ በኋላ ነው።
ሮይተርስ የሩሲያውን ኮመርሳንት ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የማስወንጨፊያ ሥርዓቱ በርካታ የተኳሾች ያሉት ሚሳይል የተገጠመለት እና እስከ 11 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚርቁ ኢላማዎችን መምታት የሚችል ነው።
ሥርዓቱ መኪና ላይ የሚገጠም ወይም መሬት ላይ ሊጠመድ የሚችልም ነው።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተችበት ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ወዲህ ብቻዋን፣ ከቻይ እና ሰሜን ኮሪያ ጋር በመሆን በርካታ ወታደራዊ ልምምጆችን አድርጋለች።
ሞስኮ፣ ሩሲያ እና ዩክሬንን ከምታዋስነው የቅርብ አጋሯ ቤላሩስ ጋርም የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድም ጨምራለች።
በዩክሬን እያደረገችው ባለው ጦርነት ምክንያት ከምዕራባውያን ጋር ፍጥጫ ውስጥ የገባችው ሩሲያ፣ በቤላሩስ የታክቲካል ኑክሌር ሚሳይል መላኳ ይታወሳል።
ይህ የሩሲያ ርምጃ ያሰጋት አሜሪካ ወደ አውሮፓ የረጅም ርቀት ሚሳይል እንደምትልክ በቅርቡ ገልጻለች።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You