የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሄደው ሦስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ህገ መንግሥቱ የፀደቀበትን ቀን ተንተርሶ በየዓመቱ ህዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተብሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር ተወሰነ፡፡
የመጀመሪያው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በ1999 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን፤ መሪ ቃሉም «ህገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳን የአብሮነታችን መገለጫ ነው» የሚል ነበር። ሁለተኛው በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልል አስተናጋጅነት በሃዋሣ ከተማ በ2000 ዓ.ም በድምቀት ሲከበር መሪ ቃሉም «ልዩነታችን ውበታችን፤ ውበታችን አንድነታችንና ጥንካሬያችን ነው» የሚል ነበር።
ሦስተኛው ደግሞ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ በ2001 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን፤ መሪ ቃሉም «ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን በማጠናከር ልማታችንን እናፋጥናለን» የሚል ነበር።
አራተኛው በምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች አዘጋጅነት ማለትም ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ በድሬዳዋ ከተማ በ2002 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን፤ መሪ ቃሉም «መቻቻል ለዴሞክራሲያዊ አንድነትና ልማት» የሚል ነበር ።
አምስተኛው በአዲስ አበባ በ2003 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን፤ መሪ ቃሉም «የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ህዳሴ ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ እናደርሳለን» የሚል ነበር።
ስድስተኛው ደግሞ በ2004 ዓ.ም በትግራይ ብሄራዊ ክልል አስተናጋጅነት በመቀሌ ሲከበር መሪ ቃሉ «ህገ መንግሥታችን ለብዝሀነታችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን» የሚል ነበር።
ሰባተኛው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት ባህር ዳር በ2005 ዓ.ም ተከብሯል። መሪ ቃሉም «ብዙም አንድም ሆነን በመለስ ራዕይ በህገ መንግሥታችን ለህዳሴያችን» የሚል ነበር።
ስምንተኛው ደግሞ በ2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ሲከበር መሪ ቃሉም «ህገ መንግሥታችን ለህዳሴያችን» የሚል ነበር።
ዘጠነኛው በ2007 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚከናወንበት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት በአሶሳ «በህገ መንግሥታችን የደመቀው ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን» በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
አስረኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በ2008 ዓ.ም በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በጋምቤላ ከተማ ሲከበር የነበረው መሪ ቃልም «በብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ የላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል ነበር።
11ኛው በ2009 ዓ.ም «ህገ መንግሥታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን» በሚል መሪ ቃል የተከበረው በምሥራቅ የአገራችን ክፍል በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት በሐረር ከተማ ነው።
12ኛው ባለፈው ዓመት 2010 ዓ.ም ‹‹በህገ መንግሥታችን የደመቀ ህብረ ብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
Your blog has helped me through some tough times and I am so grateful for your wise words and positive outlook
Your blog has helped me through some tough times and I am so grateful for your wise words and positive outlook
Your content always keeps me coming back for more!