የደም ግፊት ምንነት
በአማካኝ ሰውነታችን ከ 5-6 ሊትር የሚሆን ደም ይገኛል። ይህ ደም ለሰውነት የሚያስፈልጉ ንጥረነገሮችን እንደ ኦክስጅንና ምግብን ለማመላለስ የሚጠቅም የሰውነት ፈሳሽ ነው። ደም ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች የሚሰራጨው በልብና በደም ቧንቧዎች አማካኝነት ነው። ደም በልብ አማካኝነት በተወሰነ ግፊት መጠን ወደ ሰውነታችን ደም ትርምስ የተፈጨውም ደም በደም ቧንቧዎች አድርጎ ወደተለያዩ የሰውነት ክፍል እንዲድርስ ያደርጋል።
የደም ግፊት ከሚወስኑ ወሳኝ የሰውነት ክፍል ውስጥ ልብ እና የደም ቧንቧዎች ከፍተኛ እና ዋነኛ ሚና ይኖራቸዋል የልብ ምት መጨመር እና የደም ቧንቧዎች መጥበብ ለደም ግፊት
መከሰት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው:: የደም ግፊት መጠን ከእድሜ እድሜ ከቦታ ቦታ ቢለያይም በአማካኝ አንድ ሰው ይኖረዋል ተብሎ የሚጠቀሰው የደም ግፊት ልኬት በተለምዶ 120በ80 ነው ይህ የደም ግፊት ልኬት (normal )ተብሎ ሲወሰን ከዚህ ያነሰ የደም ግፊት መጠን ያነሰ ወይም በመጠኑ ከፍ ያለ ቢሆንም መጠነኛ ወይም ልከኛ ግፊት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ያክል የደም ግፊት መጠን 110በ70 ወይም 100 በ60 ልኬት ያለው ሰው ይህ ልኬት (normal ) ነው::
በተመሳሳይ የደም ግፊት 130በ80 ወይም 135 በ70 ያለውም ሰው እንዲሁ ልከኛ ወይም ኖርማል የሚባል ነው። ለመጠቅለል ያክል 120በ80 የሚባለው የደም ግፊት ልኬት አነስተኛው እና ከከፍተኛው ኖርማል ልኬት የተወሰደ አማካኝ ልኬት ነው። እንግዲህ ከዚህ በመነሳት የደም ግፊት ህመም ማለት ማንኛውም የደም ግፊት ልኬት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የሚፈጠር ህመም ነው። የልኬቱ መጠን ከጥናቶች፣ ከሀገር ሀገራት ቢለያይም የደም ግፊት መጠን ከ140 በ90 በላይ እና እኩል እንደ ደም ግፊት ህመም ይታያል።
የደም ግፊት መኖሩን እንዴት ማወቅ ይቻላል ?
የደም ግፊት ምልክት ከሚያሳዩ እና አደገኛ ከሚባሉ የህመም አይነት ውስጥ ይመደባል። በዚህም የተነሳ (silent
killer) እየተባለ ይጠራል። የደም ግፊት የራሱ የሆነ የህመም ምልክት ባይኖረውም በህመሙ ምክንያት ተያይዘው ከሚመጡ መዘዞች ጋር የሚኖሩ የህመም ምልክት ሊያሳይ ይችላል።
ምልክቶች
እነዚህም እንደ ደም ግፊት ምልክት ወይም መኖሩን የሚጠቁሙ ተብለው ሊወሰዱ ይችላሉ። ለምሳሌ የስትሮክ ህመም፣ የልብ ህመም ምልክቶች፣ የአይን ህመም ምልቶች፣ የኩላሊት ስራ መስነፍ ምልክቶች ወ.ዘ.ተ ናቸው። የደም ግፊት መኖሩን እና አለመኖሩን በቀላል ዘዴ ማወቅ የሚቻል ሲሆን ይህ በደም ግፊት መለኪያ መሳሪያ መለካት ነው። ህመሙን ለማወቅ ወይም ለማረጋገጥ በተደጋጋሚ መለካት አስፈላጊ ነው።
ምክንያቱም የደም ግፊት ከወትሮው በተለያዩ ምክንያቶች ከፍ ሊል ስለሚችል ነው። ይህ ደግሞ የተሳሳተ መረጃ ስለሚሰጥ ነው። ለምሳሌ ያክል አንድ ሰው በድንጋጤ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የሚኖረው የደም ግፊት ከፍ ሊል ይችላል። በተጨማሪም እንደ ቡና፣ ሲጋራ፣ እና የተለያዩ አደንዛዥ እፆች የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋሉ።
ከዚህ በመነሳት ሰዎች የደም ግፊታቸውን ለመለካት ሲያስቡ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች አለመኖራቸውን፣ አ ለ መ ጠ ቀ ማ ቸ ው ን እ ን ዲ ሁ ም ያሉ ከሆነ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ የሚገኘው ልኬት የተሳሳተ ሊሆን ይችላል። ሰዎች ከላይ የተጠቀሰውን አስወግደው (በግዜያዊነት) ነገር ግን የደም ግፊት ልኬቱ ከፍተኛ ከሆነ በተደጋጋሚ በመለካት የተገኘውን ልኬት እውነተኛነቱን ማረጋገጥ ይቻላል።
የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያ አይነቶች?
የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያዎች ለሁለት የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም ማንዋል (manual) ወይም በእጅ የሚሰራ ሲሆን ሌላኛው ዲጂታል የሚባለው ነው። ይህም ዲጂታል የሚባለው ኮምፒውተራይዝድ እና በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ነው። የኤሌክትሪክ ሀይሉን ከባትሪ ወይም በቀጥታ በሶኬት ገመድ ሊሠራ ይችላል። የሚያገኘው የደም ግፊት ልኬት መጠንንም በማሽኑ ላይ በተገጠመ ስክሪን የሚያሳይ ነው።
የዲጂታል የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያ የራሱ የሆነ ጥቅም እና ችግሮች ያሉት ነው። ከችግሮቹ በዋናነት የተሳሳተ ልኬት መጠቆሙ ነው። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የሀይል መቆራረጥ ነው። የሀይል መቆራረጡም በባትሪ መድም ወይም ለረዥም ጊዜ ማሽኑን ከመጠቀም የሚመጣ ነው።
ሌላኛው የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያ በአብዛኛው በሆስፒታሎች እና በጤና ተቋም የምናገኘው ነው። ይህ መለኪያ በክንድ ላይ በማስቀመጥ በእጃችን በሚገኘው ፊኛ መሳይ መሳሪያ አየር (pressure) በመስጠት ግፊቱን በሰዓት መቁጠሪያ መሳይ ወይም በሜርኩሪ ሲስተም በመጠቀም የተገኘውን ልኬት የሚያሳይ ነው። የዚህ ልኬት መሳሪያ ልኬቱ አስተማማኝ ተደርጎ ይወሰዳል ነገር ግን ይሄን ቢሆን የራሱ የሆነ ደካማ ጎኖች ያሉት ነው።
የደም ግፊት መምጫ ምክንያቶችን
የደም ግፊት መምጫ ምክንያቶች ተብለው ወይም አይነቶች ሁለት ናው። የመጀመሪያው (-) ወይም የመጀመሪያ አይነት የደም ግፊት የሚባው ነው። ይህ የደም ግፊት አይነት መምጫ ምክንያቱ የማይታወቅ ሲሆን የስርጭት መጠኑ ከጠቅላላ የደም ግፊት አይነቶች ውስጥ 90% ይሆናል።
ሌላው የደም ግፊት፣ ለደም ግፊቱ፣ መነሻ የሆነ ምክንያት ያለው ነው። ይህም ማለት ለደም ግፊቱ ለመፈጠር ምክንያት የሆነ ሌላ ሁለተኛ ህመም አለ ማለት ነው። ከነዚህም ህመሞች መካከል እንደ ኩላሊት ህመም፣ እንቅርት ህመም፣ አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች አንዳንድ የመድሃኒት ዓይነቶች ይጠቀሱበታል።
የደም ግፊት ህመም ህክምናዎች እና ቅድመ ጥንቃቄ
የደም ግፊት ህመም በዋናነት በሁለት መንገዶች ማከም ይችላል። አንደኛው የተለያዩ የደም ግፊት መድሃኒቶችን በመውሰድ ሲሆን ሌላኛው የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል የሚደረግ ህክምና ነው።
የደም ግፊት ህክምና እና ሁለቱን የህክምና አማራጮች በማጣመርም የሚደረግ ህክምና ነው። በመድሀኒት የሚደረግ ህክምና ዋናው አላማ የደም ግፊት በተለያየ መድሀኒት አይነቶች ግፊቱን መቀነስ ነው:: የመድሀኒቶቹ ስራ ወይም የልብ ምትን በተፈለገው መጠን የሚቀንሱ ወይም የደም ቧንቧዎችን የሚያሰፉ ሊሆኑ ይችላሉ።
አንድ ሰው ከአንድ በላይ የደም ግፊት መድሀኒት ሊወስድ ይችላል ይ ህ ን ን ም የ ሚ ወ ስ ነ ው ሀ ኪ ሙ ሲሆን የግፊት ቁጥጥሩን የመድሀኒት አይነቱንም ወይም መጠኑ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል። ከመድሀኒቶቹ ጎን ለጎን የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚህም የጨው መጠን በምግብ ውስጥ መቀነስ፤ የቅባት ምግብን መቀነስ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፥ ልከኛ የሰውነት ውፍረት መያዝ፤ የሲጋራና የአልኮል መጠጥን ማቆም የመሳሰሉት ናቸው።
ህመሙ ያለው ሰው በተወሰነ እና በቋሚነት የደም ግፊት ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሲሆን
ከእነዚህም ውስጥ:-
* የአይን ምርመራ
* የኮሌስትሮን ምርመራ
* የስኳር ህመም ምርመራ ከዋና ዋናዎቹ ውስጥ ናችው።
በተጨማሪ ማንኛውም የደም ግፊት ያለው ሰው መድሀኒቱን በአግባቡ እና በሰዓቱ እንዲሁም በሀኪሙ የታዘዘውን እውቅና ውጪ የደም ግፊት መድሀኒት አያቋረጥም ፧መጠን ወይም አይነት አይጨመርም አይቀነስም።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 24/2011