ዘመኑ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ አንገብጋቢ የሆነበት ወቅት ቢሆንም በርካታ የእንግሊዝ ቴሌቪዥኖች ስለ ውሾች ድመቶች እንዲሁም ስለ ፆታና ስለሼክስፒር በመዘገብ መጠመዳቸው አጀብ አሰኝቷል ።
ከቢቢሲ፣ አይ ቲ ቪ፣ ከቻናል 4 እና ከስካይ የወሰዱ መረጃዎችና የ40 ቻናሎችን ከመስከረም 2017 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የተላለፉ 128 ሺ 719 ፕሮግራሞችን የቃኘው ባፍታ ( የእንግሊዝ የፊልም የቴሌቪዥንና የጥበብ አካዳሚ) ያወጣው መረጃ እንዳመለከተው።
የአየር ንብረት ለውጥ 3 ሺ 125 ጊዜ ብቻ በቅንጭቡ ተጠቅሷል። ሌሎች ከአረንጓዴ ያማነት ጋር አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያላቸው ንፁህ አየር፣ የኤሌክትሪክ መኪና፣ የካርቦንልቀትና የምግብ ትርፍራፊ በጥቂት መቶዎች ተጠቅሰዋል።በዚህም ችግሮች የተጠቀሱ ቢሆንም መፍትሔያቸው ግን አልተዘገበም።
ነገር ግን ውሾች 105ሺ 245 ተጠቅሰው በቃለ መጠይቅም 68 ሺ 816 ጊዜ ሲተላለፉ ሻይ 60 ሺ 60፤ የስነ ፆታም ጉዳይ 56ሺ 307 ጊዜ፤ ስለ ኬክ 46ሺ43ጊዜ ስለድመቶች 14 ሺ 454 ጊዜና ስለሽርሽር 5 ሺ 949 ጊዜ ስለሼክስፒርም 5 ሺ 444 መጠቀሱ ተጠቁማል።
የአልበርት የአንዱስትሪ ተስማሚነት ኃላፊ አሮን ማቴዎስ እንደሚሉት “ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ የማኅበረሰብ ምላሽ ቅረፅ ለማስያዝ በወቅታዊ ጉዳዮችና የተፈጥሮ ታሪክ ፕሮግራም ላይ ብቻ ማተኮር አይገባም። በመሆኑም አዳዲስ ጉዳዮችን አክሎ ሌሎች መንገዶችንም በማየት ቀጣይነትና ሳቢነት ያላቸው ፕሮግራሞች ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 20/2011
ሀይለማርያም ወንድሙ