መብራት በፈረቃ ነው ከተባለ ወዲህ ትውልዱ ስለጄኔሬተር እንጂ ስለጄኔሬሽን የሚያስብ አልመሰለኝም ነበር፤ ይህን ያህል ሰው በመገኘቱ ደስ ብሎኛል። ‹‹መፍትሔው ኢትዮጵያዊነት ነው›› የሚል ነው ርዕሱ፤ እኔ ደግሞ ኢትዮጵያዊ አራዳ በሚል ርዕስ ነው የማቀርበው።
ባቢሎናውያን በጥንት ዘመን አንዲት እናት ልጇ ሲታመምባት የታመመ ልጇን ይዛ አስፋልት ዳር ትወጣለች። አስፋልት ዳር ትወጣና አላፊ አግዳሚውን ታስተናግዳለች። በዚያ መስመር የሚያልፉ ሁሉ ልጅሽ ምን ሆኖ ነው እያሉ ይጠይቋታል። ከጠየቋት በኋላ የሚሏትን ታዳምጣለች፤ ልጇ ላይ ትሞክራለች። ማንም ሰው ዝም ማለት አይችልም፤ በራሱ ላይ ደርሶ ህመም ካጋጠመው ይናገራል፤ ወይም የሚያውቀው ሰው ታሞ ከሆነ በዚያ መንገድ መድሃኒቱን ያዳምጣል ማለት ነው።
አሁን ላለችዋ ኢትዮጵያ ሁላችንም ባለንበት መንገድ፤ እንዲህ እናት ኢትዮጵያ ከፊታችን ቆማ መድሃኒት እየጠየቀች ሆኖ ይሰማኛል። ለዚህ መፍትሔ ኢትዮጵያዊ አራዳነት መፍጠር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። እንዲህ አይነት ነገሮች በትክክለኛ ቦታ ሲነገሩና ውይይት ሲደረግባቸው ጥሩ ይሆናል። ያለቦታው ሲሆን ግን የተሳሳተ ነገር ያመጣል።
አንድ ወዳጄ ገጠር ለማስተማር ተመድቦ ነው። አንድ የአንደኛ ክፍል ተማሪ በመስኮት ዘሎ ይገባል። መምህሩ አየና ደነገጠ። መምህሩም ‹‹ምን እየሆንክ ነው! በሩ የተሰራው እኮ ለመግቢያ ነው!›› ሲለው ተማሪው ‹‹መምህር ማስተማርዎትን ይቀጥሉ›› አለ። ‹‹ምን መሆንህ ነው? በር አለ ነው እኮ የምልህ!›› ሲሉት ‹‹የሚቀርበኝን የማወቀው እኔ ነኝ›› አለ።
የተቸገርነው እንዲህ ህወገወጥ የሆነን ነገር እኔ ነኝ የማውቀው በሚሉ ሰዎች ነው። ጸጋዬ ገብረመድኅን ‹‹የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ›› በሚለው ግጥሙ ውስጥ ሁለት መስመር አለ።
ከልቤ ፍቅር በቀር የማወርስሽም ውል የለኝ
የኮሶ ሻጭ ልጅ ድሃ ነኝ! ይላል።
ኢትዮጵያዊ አራድ እንዲህ ይለዋል ብዬ አምናለሁ።
ከእሴትሽና ሀሴትሽ ሌላ
የምቀበልሽም ቅርስ የለኝ
ኢትዮጵያዊ የአራዳ ልጅ ነኝ
አራዳ በድሮው ጊዜ መሽቀርቀር የሚወድ፣ ሽቶ የሚቀባ፣ የሚያምር፣ ዘናጭ የሆነ፣ በየመሸታ ቤቱ የማይጠፋ፣ የሰዎችን ትኩረት መስረቅ የሚችል፣ ከዘመናዊነት ጋር መግባባት የቻለ ማለት ነበር። ስለአራዳነትም ብዙ ተዘፍኗል። በኋላ አራዳነት ይዞ መገኘት ነው ተባለ። አራዳ ገበያ ሆነ። አራዳ የሌለባቸው የኢትዮጵያ ከተሞች የሉም። ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ከተሞች አራዳ የሚባል አላቸው። አራዳ የተባሉበትም አሁን ካለው መንፈስ አንጻር ነው።
ኢትዮጵያዊ አራዳ የሚለየው መስዋዕትና ሰማዕት የሆነለትን ሰው ያውቃል። ይመረምራል፤ መርጦም ይከተላል። መስዋዕት መሆን ማለት ምን እየተደረገልን ነው ብሎ ማሰብ ነው። በእንግሊዝ አገር ኦሊቨር ክሬም ዌይ የተባለ ንጉሥ በነበረ ጊዜ አንድ ወታደር ጥፋት አጠፋ። ባጠፋው ጥፋት ሞት ተፈረደበት። በጥይት ተደብድቦ ይገደል ተባለ። ሰዓት ዕላፊ በሚታወጅበት ጊዜ ደወል ይደወላል።
ደወሉን ሲነኩት ድምጽ አልሰጥ አለ። ግራ ተጋቡ፤ በጥይት ተደብድቦ የሚገደል ሰው እየተጠበቀ ነው። ደወሉ እምቢ አለ። እየተሹለከለኩ ዙሪያውን ሲያዩ አንዲት የወታደሩ እጮኛ የሆነች ሴት ደውሉ ድምጽ እንዳይሰጥ አድርጋ ይዛዋለች። በጣም ደነገጡ፤ ንጉሡ ይህን ካዩ ዝም አይሉም ተባለና እሷን ይዘው ንጉሡ ፊት አቀረቧት። ሴትዬዋ ያለ እሱ መኖር አይሆንልኝም አለች። ለእሱ ባለሽ ፍቅር የተነሳ ራስሽንም እሱንም አትርፈሻል ብለው በነጻ አሰናበቷት። በዚች አገር መሆን ያለበት እንደዚህ ነው። የሆነ አደጋ ሲመጣ እንዳያጋጥም ጥብቅና መቆም ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያዊ አራዳ ጭስ ነው፤ መውጫ ቀዳዳ አያጣም። መውጫ ቀዳዳ አያጣም ማለት እጅግ አስቸጋሪ በነበሩበት ጊዜያት እንኳን ያጋጠማቸውን መከራ አልፈውት ይሄዳሉ። በአውሮፓውያን የሆነ ወረርሽኝ ተከስቶ ነበረ። ይህ ወረርሽኝ የአውሮፓን አንድ ሦስተኛ ህዝብ ጨርሷል። ያ ወረርሽኝ የተላለፈው በቁንጫ አማካኝነት ነው። ቁንጫው ከአይጥ ጋር እየዋለ ደም ይመጣል፤ ደም መጦ ደግሞ ሰው ይነክሳል፤ ሰውን ሲነክስ የመጠጠውን ደም ሰው ላይ እየረጨ ነው። በዚሁ ምክንያት 25 ሚሊዮን ህዝብ አለቀ።
ይቺ ቁንጫ አሁን ካለው የአገራችን ሁኔታ ጋር ከዘረኝነት ጋር ይመሳሰላል። ቁንጫው ዘረኝነት ነው፤ ዘረኝነቱ የሚያጠቃው ደግሞ ድሃ አገሮችን ነው። ዘረኝነት ልክ እንደ ቁንጫ አቅም የሌለው መስሎ ብዙዎችን የሚረብሽ፣ የሚያተራምስ፣ የሚበጠብጥ ነው። የሚገርመው ግን ከዚህ ሁሉ ፈተና ማለፍ የሚችሉት አይጦች ናቸው። አይጦች ያንን ባክቴሪያ ያስተላልፋሉ እንጂ አይተላለፍባቸውም። ይህኔ ‹‹አይጥ መሆን ነበር›› ትሉ ይሆናል። ግን ከንቱ ምኞት ነው የአይጥነት ሚና። የአይጥነትን ሚና አክቲቪስቶች ይዘውታል።
ንብረታችን ይወሰዳል፤ ሕይወታችን ይወሰዳል፤ ይህንን ነው የሚያስተላልፉልን። አባቶቻችን እንደሚሉት ‹‹ሞኝ የመከሩት ዕለት ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ይብሰዋል›› እኛ አገርም ይሄ ነገር ተባብሶ እያየነው ነው።
አራዳ ሰው ግን ነፍሱን ያጸዳል፣ ያነጻል። በእስልምና አስተምህሮት ‹‹ኢባዳ›› የሚባል ነገር አለ። ራስን ከክፉ ነገሮች ማራቅ፣ ለሰይጣን አለመገዛትና ንጹህ ሆኖ መገኘት። ይህንን አራዶች ያልፉታል፤ ያመልጡታል። ዘረኝነትን መከላከል ይችላሉ ማለት ነው። በነገራችን ላይ በዓለም ላይ አንድ ሺህ ስምንት አይነት የቁንጫ አይነቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ እንግዲህ ከመቶ ስምንት በላይ ፓርቲ ላላት አገር ስንት ስንት እንደሚደርሳቸው አስቡት።
ኢትዮጵያዊ አራዳ ከጨለምተኛነት የራቀ ነው። ከከሰመው ይልቅ የለመለመው ነገር ይታየዋል። አንድ የቡድሂዝም እምነት ተከታይ የሆነች ሴት ያደረገችው ነገር ነበር። እግዚአብሔርን እጅግ እንደምትወደው የሚያውቁ ሰዎች እየተከታተሉ ይጠይቋታል፤ ‹‹ታውቂዋለሽ እግዜርን›› ሲሏት ‹‹አዎ፤ በጣም እወደዋለሁ›› አለች። ‹‹እግዜርን ይህን ያህል የምትወጅው ከሆነ ሰይጣንን ምን ያህል ብትጠይው ነው›› ብለው ጠየቋት። ‹‹ሰይጣንን አልወደውምም አልጠላውምም›› አለች። ‹‹ለምን›› ሲሏት ‹‹ሰይጣንን ለመጥላት የማባክነውን ጊዜ እግዜርን ለመውደድ እጠቀምበታለሁ›› አለች።
እኛ ብዙ ጊዜ ሰማዕት ከሆነልን ክርስቶስ ይልቅ እሱን አሳልፎ ስለሰጠው ይሁዳ ያለን እውቀት ይበልጣል። አሳልፈው ስለሰጡ ሰዎች ነው የምናወራው። ከጨለምተኝነት መራቅ ማለት ድክመቱን አለመግለጽ ማለት አይደለም። የሚታየውን ብርሃን አጉልቶ ማውጣት ነው ዋናው ነገር።
ኢትዮጵያዊ አራዳ የሚናገር ሳይሆን የሚነጋገር፤ የሚደመጥ ሳይሆን የሚደማመጥ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚዘጋጀው ‹‹አዲስ ወግ›› የተሰኘው ፕሮግራም በጣም ስሜት ሰጥቶኛል። አንድ ጽሕፈት ቤት ባለሙያዎችን ጋብዞ፤ ሊቃወሙት እንደሚችሉ እያወቀ ‹‹እስኪ ምንድነው ጉድለቴ›› ብሎ ለማዳመጥ መቻል በእኛ አገር ያልተለመደ አዲስ ባህል ነው። መናገር ሳይሆን መነጋገር የሚለውን ማሳያ ይሆናል።
በአንድ ወቅት ሃያ ምናምን የሆንን የኪነ ጥበብ ሰዎች አዲስ የሚሰራውን ቤተ መንግስት እንድንጎበኝ ተጋበዝን። ሙዚየሙን ካየን በኋላ የተለያዩ ባለሙያዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊያገኟችሁ ይፈልጋሉ ተብሎ ከመካከላችን አንዱ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ አንድ ጥያቄ ሲያነሳ ዶክተር አብይ መልስ ሰጡ።
‹‹እንደሱ አይደለማ ማለት የፈለኩት›› ብሎ ዶክተር በድሉ ማስተካከያ ሰጠ። የአንደኛ ዓመት በዓላቸውን ሲያከብሩም ንግግር ካደረጉ ሰዎች አንዱ ዶክተር በድሉ ነበር። ብዙ ጊዜ የነቀፈንን የተቸንን የማቅረብ ልምድ የለንም። ‹‹በፌዴራሊዝም አልደራደርም ማለት ምን ማለት ነው? ይሄ ራሱ አምባገነንነት ነው›› ብሎ እንድናገር መፍቀድ ከዚህ በላይ መሰልጠን እኔ አይታየኝም። የምንተቸውን መስማት መቻል የመብቃት ምልክት ነው።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 17/2011
medicijnen: betrouwbare pijnverlichting zonder recept lek San Antero online apotheek om medicijnen te kopen in Frankrijk
любовный гороскоп водолею женщине на
август самое сильное магнитное поле у планеты, магнитное поле сатурна вам и не снилось
музыка из фильма минус один
сонник драка женщина с женщиной что
означает имя наима
к чему снится молочная пена сонник
учиться институт гороскоп любовный для мужчины водолея
сонник сниться молодой
человек приснился бассейн в который
я ныряла
сумісність знаків зодіаку в коханні близнюки чоловік і діва жінка гороскоп
народженого 17 червня
гороскоп на кінець липня лев щодня сниться риболовля
конфуций ілімі слайд, конфуций саясаттану
толық адам болу, толық адам абай қысқаша мазмұны карта мастеркард украина, не могу добавить карту мир
в samsung pay ұмж омж қмж презентация, слайд сабақ қорғау
A fascinating discussion is worth comment. I think that you need to publish more on this subject, it may
not be a taboo subject but typically people do not speak about these issues.
To the next! Many thanks!!
Hello it’s me, I am also visiting this website on a regular basis, this web page is
genuinely good and the users are really sharing
fastidious thoughts.
стальной союз павлодар, стальной союз алматы парниктік эффект уикипедия, парниктік эффект себептері көп нүкте ереже, үтір
қандай сөздер мен сөйлемдердің
арасына қойылады атырау мұнай өндіру зауыты, атырау мұнай эссе
cmsc 120 шолу, cmsc 120 бос орын есеп айырысу шоты, 3350 шоты арзан это, арты орысша jac – колёса, купить jac в алматы
поведение женщины при климаксе, шум в голове при климаксе қысқа мерзімді жоспардың алгоритмі, қысқа мерзімді жоспар 472 бұйрық вита плюс витамины отзывы, vito plus
от а до zn отзывы торегали тореали
ханшайым, торегали тореали
ханшайым текст