ቱርክ ከመላው አፍሪካ ማስፋፋት የምትፈ ልገውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ድርሻ በምስራቅ አፍሪካም በብርቱ ትፈልገዋለች። ለዚህም በምስራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ ከዚህ አንፃር ያላትን ተሳትፎ ጎልቶ የሚገለፀው ከመቶ ሚሊየን ያላነሰ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው። ኢትዮጵያም በበኩሏ ቱርክ ዋነኛ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ሸሪኳ ሆና እንድትቀጥል ያላትን ቁርጠኝነት ለማሳየት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ከኃላፊነታቸው ከመውረዳቸው ዋዜማ ላይ በቱርክ ባደረጉት ጉብኝት አረጋግጠዋል።
ታሪክ እንደሚመሰክረውም ቱርክ የአፍሪካን መንግሥታት በር ስታንኳኳ ቅድሚያ የሰጠችው ለምኒልክ ቤተ መንግሥት ነበር። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ የሚጀምረው በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ዘመን በ1896 /እ.ኤ.አ/ ላይ ነው። ከዚያም በ1912 ሐረር ላይ የኮንፂላ ጽሕፈት ቤት ያቋቋመችው ቱርክ በ1926 ላይ በአዲስ አበባ ከሰሃራ በታች የመጀመሪያ የሆነውን ኤምባሲዋን አዲስ አበባ ላይ ከፍታለች።
ታሪካዊ ግንኙነቱ ዛሬ ላይ በአዲሱ የቱርክ የፖሊሲ ቅኝት የበለጠ አድጎ አገሪቱ በአፍሪካ ካላት ስድሰት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትምንት ስምሪት ውስጥ በኢትዮጵያ ሁለት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ያህል ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ችላለች። ወደ 160 የሚደርሱ የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ተሰማርተው እየሠሩ ሲሆን፣ ለ30 ሺህ ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።
ቱርክ እና ኢትዮጵያ ከፍተኛ የንግድ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው። የውጭና የሀገር ውስጥ ንግድ ሚዛኑ ግን የተመጣጠነ አይደለም። ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ በየዓመቱ የ440 ሚሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ገበያ ሲኖራት ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ የምትልከው ግን ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ አላ ደገም።
የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸው ሲሆን በኃይል፣ በብረታ ብረት፣ በሴራሚክ ምርት እና በግንባታ ተሳትፎ የማድረግ ፍላጎታቸው በየጊዜው እያደገ ነው።
በቅርቡም በ750 ሚሊዮን ዩሮ በትግራይ ክልል ሕንጣሎ ወረዳ በ500 ሄክታር ላይ የኢዱስትሪ ፓርክ የመገንባት ዕቅድ አላት። ይሄ ፓርክ ከመቀሌ ኢንደስትሪያል ፓርክ አምስት እጥፍ ስፋት ያለው ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ የሚሠራ ነው።
ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ የብረታ ብርት ምርቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን፣ የአግሮ ኢንደስትሪ የምርት ውጤቶችንና የጨርቃ ጨርቅ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ታስገባለች። በአንፃሩ ኢትዮጵያ የቅባት እህሎችን፣ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን እና ቆዳ እና ጨርቃ ጨርቆችን ትልካለች።
ቱርክ ለኢትዮጵያ በትምህርት እና በስልጠና መስክም ትብብሯ የጎላ ነው። በመቶዎች ለሚቆ ጠሩ ተማሪዎች ስኮላርሺፕ በመስጠት ትብብር ታደርጋለች።
የቱርክ ዓለም አቀፍ የትብብር እና ትምርት ኤጀንሲ /TIKA/ አንዱ ቢሮ የተከፈተው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑም የትብብሩን ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ያመላክታል።
ኤጀንሲው በምሥራቅ አፍሪካ ለሶማሊያ 4 ሚሊዮን 572 ሺህ ዶላር ድጋፍ ሲሰጥ፣ ለኢትዮጵያ ለውሃ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የተወሰነው ደግሞ ለማህበራዊ ልማት የሚውል አንድ ሚሊዮን አሥራ አንድ ሺህ ዶላር እና ለጂቡቲ 113 ሺህ ዶላር ሰጥቷል። ሱዳን እና ኬኒያም ከቱርክ የሚሰጠውን የልማት ድጋፍ የሚያገኙት በዚሁ ኤጀንሲ በኩል ነው።
በተለይ ኬኒያ ከኢትጵ ቀጥሎ ከኢኮኖሚ አንፃር ቱርክ ትኩረት የምትሰጣት ሀገር በመሆኗ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኤጀንሲው ሥራ ኬኒያንንም በቅርበት የመደገፍ ስልት የሚከተል ነው። ቱርክ ኬኒያን ከራሷ ባሻገር ከምሥራቅ አፍሪካ የጋራ ማህብረሰብ (EAC)፣ ከምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የጋራ ገበያ (Comesa) እና ከደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህብረሰብ (SADC) ጋር ለመሥራት እንደ መግቢያ በር ታያታ ለች። በኢኮኖሚ ግንኙነታቸውም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ንግድ አሁን ላይ ከ160 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያላነሰ መሆኑ ይነገራል።
ከእስያ አህጉር ኢኮኖሚ ውስጥ በስድስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቱርክ ኢኮኖሚ ለአፍሪካ ቀንድ አገራት ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። ቱርክ በአካባቢው ኢኮኖሚ ውስጥ የድርሻዋን ለማንሣት የምትጣደፈውን ያህል የምሥራቅ አፍሪካ አገራትም ፖለቲካዊ ፍትጊያዎችን እና የውክልና ትንኮሳዎችን ማራቅ ከቻሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ቱርክን የበለጠ ለኢኮኖሚ ልማት ዋነኛ አጋር ልትሆናቸው እንደምትችል ግልፅ ነው። በተለይ የማዕድን፣ የግብርና እና የጨርቃ ጨርቅ ጥሬ ዕቃዎችንና ምርቶችን ወደ ቱርክ በመላክ የተሻለ ገቢ የማግኘት ዕድል አላቸው።
የቱርክ ባለሀብቶችም በቀጥተኛ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ቁጥራቸው እየጨመረ በመምጣቱ በሚከፍቷቸው ኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል በማስፋፋት የአገራቱን ሸክም መቀነስ ይችላሉ። ስለዚህም ከቱርክ ጋር በአካባቢው ሠላም እና መረጋጋት በሚያመጣ መንገድ ግልፅ እና ልማታዊ የንግድ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን በመፈፀም፣ የአፍሪካ ቀንድ አገራትን ሁሉ የሚያስተሳስሩ ድጋፍ እና ትብብሮችን በማጠናከር የሰመረ ግንኙነት መፍጠር ለቀጠናው ሀገራት የሚኖ ረው ፋይዳ ከፍ ያለ ይሆ ናል።
ዘመን መፅሄት መጋቢት
2011