ሰላም ልጆች እንዴት ናችሁ፤ ትምህርት እንዴት ይዟችኋል? መቼም በጥሩ እየሄደ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጣችሁኝ አልጠራጠርም፡፡ አሁን ለፈተና እየተዘጋጃችሁ ስለሆነ ከእስከዛሬው የበለጠ እያጠናችሁ ነው፡፡ እናም ጥሩ ነው እንደምትሉ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ ልጆች በእርግጥ ማንበብ ያለባችሁ ፈተና ሲደርስ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የየቀኑን ትምህርት በጊዜው ማንበብ ይኖርባችኋል፡፡ ፈተና ሲደርስ ደግሞ ያንን መከለስ ብቻ ነው የሚሆነው ሥራችሁ፡፡ የዚህን ጊዜ በጣም ጥሩ ውጤት ማምጣት ትችላላችሁ፡፡male rose sex toycheap sex toys for menmens adult sex toysbest sex toysonline adult sex toy storegay sex toysbest sex toy for mensex toys for couplessex toys shopbest sex toys for couplesrose sex toylovense sex toybest mens sex toyssex toys for mentop couples sex toysmen sex toysrealistic ass sex toysex toy storebuy sex toys onlinebest sex toys for womenbuy sex toys onlinebest couples sex toysbest mens sex toyssex toys for mensex toys for salesex toys onlinesex toys for salesex toy siliconepopular sex toysthe rose sex toybest sex toys on amazoncouples sex toysfree sex toyslesbian sex toyssex toy storevibrators sex toysadam and eve sex toy storetop sex toysass sex toybest couples sex toysbest female sex toy
ልጆች ለመሆኑ በዘንድሮው ዓመት የስድስተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዳለ ታውቃላችሁ? አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ፈተና ከሚሰጡት መካከል ነው፡፡ እናም ይህንን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በምን መልኩ እየተዘጋጁ ተሞክራቸውን የሚያጋሩንን ልጆች ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ፡፡
አቤኔዘር ወንድወሰን ይባላል። የ13 ዓመት ልጅ ነው፡፡ የሚማረው የማሪያሮባቶ ካቶሊክ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን፤ ከላይ እንዳልኳችሁ የዘንድሮ የስድስተኛ ክፍል ተፈታኝ ነው። በትምህርቱ ጎበዝ ተማሪ ሲሆን፤ በትምህርት ቤት ውስጥ በተለያዩ ክበባት ውስጥ ይሳተፋል፡፡ ይህ ደግሞ በትምህርቱም ሆነ በቀጣይ ሕይወቱ ላይ በርካታ ለውጦች እንዲያስመዘግብ አድርጎታል፡፡ በምን ጉዳይ ላይ አቅም እንዳለው መለየት የቻለውም በዚህ ተሳትፎው ነው፡፡
ልጆች አቤኔዘር ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ተፈታኝ በመሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶችን አድርጓል፡፡ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ሲመቸው ብቻ የሚያጠናበትን ሁኔታ ቀይሯል፡፡ ጊዜ ወስዶ ማጥናት ያለውን ጠቀሜታ ስለተረዳ የአጠናን ዘዴውን በመቀየር የተለየ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ዛሬ የተማረውን ዛሬ እንጂ ለነገ እንዳይተው የሆነውም በዚህ ምክንያት ነው። ከትምህርቱ ጎን ለጎን ለፈተና ያግዙኛል ብሎ የሚያስባቸውን መጽሐፍት ያነባል፡ ፡ ለዚህ ደግሞ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ድጋፍ እንደሆነለት ይናገራል። የትምህርቱ ዝግጅቱና የመማር ማስተማሩ ሥራ ብዙ ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለትም ያስረዳል፡፡
ፈተናው የሚሰጠው ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ብዙዎች ስጋት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ሆኖም በሚገባ ከተጠናና ከተዘጋጀን ምንም የሚያስፈራ ነገር እንደሌለ ያምናል፡፡ እርሱም ምንም እንዳልፈራ ነው የነገረን፡፡ እስከዛሬ በነበረው ሂደት በትምህርት ቤታቸው ከስር ከስር የሚሰጣቸውን ትምህርት ያጠናል፡፡ ወርክሾፖችንም ይሰራል፡፡ አሁን ደግሞ ፈተናው ስለተቃረበ የክለሳ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ልጆች አቤኔዘር እናንተን የሚመክረው ነገር አለው። የመጀመሪያው ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ቢሆንም አትፍሩ የሚል ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፍራቻ ጭንቀትን ከዚያም ደግሞ የሚያውቅትን አለመስራትን ያመጣል ብሎ ማሰቡ ነው፡፡ እናም በተቻላችሁ መጠን ትምህርታችሁን ትኩረት አድርጉና ተዘጋጁ ይላል። በትምህርት ማንኛውንም ነገር መለወጥ ይቻላል። ማንም ሰነፍ ሆኖ አልተፈጠረም። የመጠቀምና የመስራት ጉዳይ ነው ልዩነቶችን የሚያመጣው። እናም በርትታችሁ የምታነቡና ትምህርታችሁን ወደ ተግባር የምትለውጡ ከሆናችሁ ያሰባችሁት ላይ ከመድረስ ማንም አያግዳችሁም ብሏችኋል፡፡ ለቤተሰቦቻችን ደስታ ለአገራችን ውለታ ለመክፈል በጣም ጎበዝ ተማሪና አትራፊ መሆን አለባችሁም ሲል ይመክራል፡፡
ናትናኤል መልካሙ እንደ አቤኔዘር ሁሉ የማሪያሮባቶ ካቶሊክ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይማራል፡፡ እርሱም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የስድስተኛ ክፍል ፈተና ይሳተፋል፡፡ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሚጀመረውን የስድስተኛ ክፍል ፈተና ስለሚወስድ ቅድመ ዝግጅቶችን አድርጓል። ዝግጅት የጀመረው ደግሞ ገና ትምህርት አሀዱ ሲባል ነው፡፡ በዋናነት ዝግጅቱን እያደረገ የነበረው ደግሞ ፈተና ይመጣበታል የተባለውን የስድስተኛ ክፍል ትምህርትን በሚገባ በክፍል ውስጥ በመከታተልና አጋዥ የሆኑ መጽሐፍትን በማንበብ ነው፡፡
ናትናኤል ከትምህርት በኋላም በተረፈችው ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር ያጠናል፡፡ ለዚህ ደግሞ አንድ ነገር እንዳገዘው ይናገራል፡፡ ትምህርት ቤታቸው የሚያደርግላቸው ልዩ ክትትል ሲሆን፤ ለአብነትም የቅዳሜ ትምህርትን ያነሳል፡፡ በቅዳሜ ትምህርት የተለያዩ አጋዥ የሆኑ ትምህርቶች ይሰጣቸዋል፡፡ ትምህርቱ ሲሰጥ ከሰኞ እስከ ዓርብ የተማሩትን የሚከለስበት በመሆኑ ለጥናት ነገሮችን ያቀልላቸዋል። በዚያ ላይ ምን ያህል እውቀት እንደጨበጡ ያረጋግጥላቸዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለፈተና ሳይጨናነቁ እንዲዘጋጁ ያግዛቸዋል፡፡
ልጆች ናትናኤል የመጀመሪያ የስድስተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ መሆናቸው ሲነገራቸው ፈርቶ እንደነበር ይናገራል፡፡ ፍራቻውን ያስወገዱለት ደግሞ መምህራኑ እንደሆኑ ያስረዳል፡፡ የተለያዩ ፈተናዎችን በማውጣት ልምምድ እንዲያደርጉ አዘጋጅተዋቸዋል፡፡ ከዚያም ባለፈ ማንበብ ያለባቸውን ነገር ይነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህም በህብረትም ሆነ በተናጠል ሳይጨናነቁ እንዲያጠኑና እንዲሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ እናም ተማሪዎች የተፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ውጤታማ መሆን አለባቸውና ይህንን ያድርጉ ሲል ይመክራል፡፡ በተለይም ተፈታኞች ቢጠቀሙበት ውጤታማ እንደሚሆኑም ያምናል፡፡ እርሱ በዚህ መንገድ እየተጓዘ እንደሆነም ነግሮናል፡፡
ልጆች የእነ ናትናኤል ተሞክሮ እጅግ ጠቃሚ ነው አይደል? እናንተም በራሳችሁ መንገድ የተሻለ ነው የምትሉትን የአጠናን ዘዴ በመጠቀም ለፈተና ልዩ ዝግጅት ማድረግ አለባችሁ፡፡ አቤኔዘር እንዳላችሁም መጨናነቅ የለባችሁም፡፡ ምክንያቱም ጭንቀት ውጤታችሁን ይገለዋል፡፡ አቅማችሁን ያዳፍነዋል፡፡ አይችሉም፤ ሰነፎች ናቸውም ያስብላችኋል፡፡ እናም በቂ ዝግጅት ካደረጋችሁ ፈተናውን እንደምትሰሩት አምናችሁ ወደፈተና መግባት አለባችሁ፡፡ መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ በመመኘት ለዛሬ የያዝነውን አበቃን፡፡
ጽጌረዳ ጫንያለው
አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2015