ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ፣ የህንፃ ግንባታ ጥበብ፣ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ሀገረ መንግስት፣ ሀገር በቀል ባህል፣ ጥበብና የሰው ዘር አመጣጥን የሚያሳዩ ምድረ ቀደምት መካነ ቅርሶች፣ ሀብቶችን በአንድነት የያዘች ሀገር ነች። እነዚህ የሰው ልጅን የስልጣኔ ደረጃ ዛሬም ድረስ በማሳየት ህያው የሆኑ ሀብቶች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርትና የባህል ድርጅት በዓለም የሰው ልጆች የደረሱበትን ደረጃ የሚያሳዩ ቅርሶች በሚል እውቅና የተሰጣቸው ናቸው።
cheap jerseys
custom football uniforms
mlb custom jerseys
custom baseball jerseys
cheap custom jerseys
custom cheap jerseys
custom bowling jerseys
custom team jerseys
custom designs
custom football jerseys
custom nba jerseys
custom jersey maker
design jersey
best nfl jerseys of all time
custom basketball jerseys
nfl jersey
customized basketball jerseys
custom baseball jersey
custom softball jerseys
custom bowling jerseys
customize jersey
custom nfl jerseys
design your own jersey
best custom retro bowl jerseys
customize football jersey
nfl custom jersey
custom soccer jerseys
custom dodgers jersey
custom jerseys football
nike custom jersey
custom apparel
custom jersey
custom hockey jerseys
custom football uniforms
baseball jerseys custom
custom mlb jerseys
custom basketball uniforms
baseball uniforms
customized football jerseys online
custom jersey
custom nfl jersey
እስካሁን ኢትዮጵያ 13 የሚደርሱ የባህል፣ የተፈጥሮና መካነ ቅርሶችን በማስመዝገብ ከዓለምም ሆነ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ተርታ መሰለፍ ችላለች። ከተመዘገቡት ሀብቶች መካከልም የኮንሶ ባህላዊ መልከዓ ምድር፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሀውልት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ይገኙበታል።
ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች እንዳመለክቱት፤ ሀገሪቱ አሁንም ቀሪው ዓለም ያልተመለከታቸው በዩኔስኮ ለመመዝገብና እውቅናን ለማግኘት በመንገድ ላይ ያሉ ሀብቶች አሏት። በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ ከሰፈሩ ሀብቶች በተጨማሪ አምስት የተፈጥሮ፣ የታሪክ እና የቅርስ ሀብቶች በጊዜያዊ መዝገብ ላይ ሰፍረው በቋሚነት በዓለም ቅርስነት በዩኒስኮ ለመመዝገብ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ (እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008 የተመዘገበ)፣ የድሬ ሼህ ሁሴን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ስፍራ፣ የሶፎመር ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርስ፣ የመልካ ቁንጥሬና ባጪልት አርኪዮሎጂካል ስፍራ እንዲሁም የጌዲዮ ባህላዊ መልክዓ ምድር የሚሉት ይገኙበታል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ይፋ ባደረገው መረጃ ከላይ ካነሳናቸው ቅርሶች በተጨማሪ በኢትዮጵያ በስፋቱ ቀዳሚ የሆነውና በውስጡ አያሌ ቅርሶች፣ ገዳማት፣ ቀደምት ስልጣኔን የሰነዱ መዛግብትን በጉያው የያዘው “የጣና ሐይቅ ገዳማት እና በዙሪያው የሚገኘውን ባሕረ ሸሽ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መልክዓ ምድርን” በዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ተግባራዊ ስራ መጀመሩን ገልጾልናል። የክልሉ መንግስትና የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ ሆነው በ10 ወር ውስጥ ሰነዱን አዘጋጅተው ዩኒስኮ ከሚልከው “ቱ ጂ ቱሪዝም ኤንድ ሆስፒታሊቲ ኮንሰልታንሲ ሰርቪስ ጋር” ስምምነት ፈፅመዋል። ይህ ሀብት በዩኒስኮ ለመመዝገብ ይሁንታን ሲያገኝ ቀደም ብለው እውቅናን ካገኙት የመስህብ ሀብቶች ውስጥ እንደሚካተት ይጠበቃል።
በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ረዘም ያሉ ዓመታትን የሰሩ ባለሙያዎች መካነ ቅርሶቹ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘታቸው ተገቢ መሆኑን ቢያምኑም ዋናው ግብ ግን እርሱ ብቻ እንዳልሆነ ሲገልጹ ይደመጣሉ። እነዚህ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት፤ በዓለም ቅርስነት የሚመዘገቡ ሀብቶችን በቅድሚያ ለአገሬው ዜጋ በሚገባ ማስተዋወቅ ይገባል። ከሁሉም በላይ ግን ሀብቶቹን (በሁሉም ክልሎች ላይ የሚገኙ መካነ ቅርሶችን) ማልማት፣ ከጉዳት መጠበቅና ከተደቀነባቸው ስጋት የመከላከል ሥራ ያለማቋረጥ መስራት ይኖርበታል።
እነዚህ አካላት ለዚህ ሃሳብ እንደ ምሳሌነት የሚያነሱት የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቦ መቆየቱን ጠቅሰው፣ በውስጡ ያሉት ተፈጥሯዊ ሀብቶች በመጥፋት ስጋት ላይ መሆናቸውን ያመለክታሉ። ይህንንም ሀብት ራሱ የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ድርጅት አደጋ ውስጥ ካሉ ቅርሶች ዝርዝር ከትቶት ነበር ሲሉም ያስታውሳሉ። ይህንን ቅርስ ከዚያ ስጋት ለመውጣትና የመልሶ ቅርስ ልማት ለማድረግ 22 ዓመታትን የፈጀ ጥረት ጠይቆ እንደነበር እንደማይዘነጋ አስታውሰዋል። በዚህ ምክንያት ቅርሶችን ከማስመዝገብም ባልተናነሰ ተከታታይ የጥበቃና ልማት ሥራ መስራት ተገቢ መሆኑን አንስተው፣ ይህ ካልሆነ ግን የሀገር ገፅታን ከማበላሸትም ባለፈ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ፍሰት እንዲቀንስ እንደሚያደርግ ነው የሚያስጠነቅቁት።
የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንም ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ፣ ተለይተው እንዲታወቁ ከማድረግ በተጨማሪ ሀብቶቹን ከጉዳት የመጠበቅ፣ የመጠገንና ተከታታይ የልማት ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል፤ ማህበረሰቡ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የጉዳዩ ባለቤቶች ግንዛቤው እንዲኖራቸው የማድረግ ኃላፊነትም ወስዷል። ይህንን በተመለከተም ከሰሞኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመካነ ቅርስ ልማትና ተጠቃሚነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በመድረኩ በመካነ ቅርስ ልማትና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከአማራ፣ ከትግራይ፣ ከአፋርና ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማትና ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የመካነ ቅርስ ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀሐይ እሸቴ እንደሚሉት፤ መካነ ቅርሶችን በጋራ ለማልማትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሀገሪቷን ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች በመሰነድና በማደራጀት ለጥናትና ምርምር አገልግሎት እንዲውሉ በማድረግ እና በማልማት ለቀጣዩ ትውልድ ተጠብቀው እንዲሸጋገሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል። ባለስልጣኑ ሀገራችን ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ቅርሶችን ለማልማት የሚያስችሉ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን ደረጃ በደረጃ የማውጣትና የማሻሻል ተግባራት እያከናወነ ነው።
በፌዴራል፣ በክልል፣ በወረዳ፣ በቅርሱ ባለቤቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ በግሉ ዘርፍ ውስጥ በተሰማሩ የቅርስ አስተዳደር አማካሪ ኮሚቴዎች እንዲሁም ቅርሶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ ባለድርሻ አካላት በመካነ ቅርሱ ነባራዊ ሁኔታ፣ ጥበቃ፣ ልማትና አስተዳደር ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ቅርሶቹን ከአደጋ መታደግ እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚ ይገለፃል። ይህንን አስመልክቶ ሃሳባቸውን የሚሰጡት ወይዘሮ ፀሐይ፤ ቅርሶችን ጠብቆና ተንከባክቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እና አልምቶ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እስካሁን ድረስ የተሰራው ሥራ በቂ ነው ማለት እንደማይቻል ይናገራሉ። የሀገሪቷን ቅርሶች በማልማት የአካባቢውን ማህበረሰብ እና ሀገሪቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻልና ለዚህም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋራ ተቀራርቦ መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባሉ።
“የቅርስ ባለ ድርሻ አካላት በቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ሥራ ሰፊ ተሳትፎ ልናደርግ ይገባል” የሚሉት ዳይሬክተሯ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተጀመረው ዘርፉን የማሳደግ እና የመለወጥ ተግባር ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች፣ ከቅርስ ባለይዞታዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከነዚህ ተግባራት መካከል አንዱ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችና የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት የቅርሶች ጥበቃ እና ልማት ተግባራትን በቅንጅት ማከናወን አንዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ከሰሞኑ የተደረገው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አንዱ መሆኑን ነው የገለጹልን።
“ያለፈውን ዘመን ከጠበቅን በሚመጣው ላይ አሻራችንን እናሳርፋለን” የሚሉት ዳይሬክተሯ፣ ተቀናጅቶ የመስራት አቅጣጫ በፌዴራል በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚተገበሩበትን የቅርስ ማሰባሰብ፣ ማደራጀት፣ ጥበቃ እና ልማት ሥራዎች በተናበበ መልኩ ለመስራት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያስችላል ይላሉ።
እሳቸው እንዳሉት፤ የቅርስ ልማት የአብዛኛውን የህብረተሰብ ፍላጎት እና ተጠቃሚነት መሰረት ያደረገ እንዲሆን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በቅርሱ አካባቢ የሚኖሩ እና የቅርሱን እሴቶች የራሳቸው የማንነት መገለጫ እና ኩራት እንደሆነ የሚያምኑ እና የቅርሱን አስተዳደር እና ጥበቃ ዓላማ እና ግብ የሚጋራው የአካባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎ ከምንም በላይ ያስፈልጋል።
“የሰው ልጆች ሁሉ ውድ ሀብት በሆኑ ቅርሶች ላይ የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍና ቅርሶችን ጠብቆና ተንከባክቦ ከቅርሶቹ በሚገኝ እሴት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል” የሚሉት ወይዘሮ ፀሐይ፣ ከሰሞኑ በተካሄደው ሁሉንም ክልሎች ያሳተፈ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና መድረክ ላይ የመካነ ቅርስ ልማት ፅንሰ ሀሳብና አተገባበሩ፣ በአፍሪካና በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተሰሩ በምሳሌነት የሚጠቀሱ የመካነ ቅርስ ልማት ስፍራዎች፣ የኢትዮጵያ መካነ ቅርስ እሴቶችን የማልማት ፈተናዎችና እድሎች በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ጥናታዊ ወረቀቶች ቀርበዋል። በዚህም “የመካነ ቅርስ መርሆዎች ምን እንደሆኑ፤ መካነ ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ፣ በመካነ ቅርስ የሀገሪቷና የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት፣ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ማሳደግ፣ ብሔራዊ ኩራትን ከፍ ማድረግ፣ ብሔራዊ ማንነትንና ትስስርን፣ ማህበራዊ አብሮነትና ቅርሶችን ታሳቢ በማድረግ እንዴት እናልማቸው የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች” የተነሱበት የምክክር መድረክ መሆኑን ነግረውናል።
እንደ መውጫ
በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የልማት እና የከተሜነት ፍላጎት በቅርሶች አካባቢ የሚካሄድ የልማት ሥራ እንዲጨምር ማድረጉን በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እያመለከቱ ይገኛሉ። እነዚህን የልማት ሥራዎች ከቅርሶች ደህንነት ጋር በማጣጣም ለሀገሪቱ የተሟላ እድገትና ቀጣይ ልማት የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። በቅርሶች አካባቢ የሚካሄዱ የልማት ሥራዎች በተለያዩ አካላት ባለቤትነት የሚከናወኑ በመሆኑ ለቅርሶች ደህንነት ስጋት ስለሆኑ ቅንጅታዊ አሰራርን ይፈልጋሉ። በመሆኑም ስለ ቅርሶች ጉዳይ በሕግ ኃላፊነት የተሰጠው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በቅርሶች አካባቢ የሚካሄዱትን የልማት ሥራዎች ከሚመሩት አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ዘለቄታዊ ልማትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በቅርሶች ላይ የተደቀነውን ይህንን ስጋት ለመቅረፍ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተከታታይ ምክክር እና ውይይቶችን ከክልሎች ጋር እያደረገ ይገኛል።
ከላይ ካነሳነው መረጃ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የሚገኙ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገቡ ሀብቶች በልዩ ልዩ ምክንያቶች አደጋ ተደቅኖባቸዋል። ከእነዚህ መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጉዛራ ቤተ መንግስት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግስት እና ሌሎችም ሀብቶች ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ ሀብቶች ውስጥ አብዛኞቹን ለመጠበቅ፣ ለመጠገንና ሊያጋጥማቸው ከሚችለው ስጋት ለመታደግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። ይህን ሥራ የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን እንደሚመራው ይታወቃል። ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የቅርስ ባለአደራ ምክር ቤት ከዓለም አቀፍ የግልና መንግስታዊ ድርጅቶች ጋር በመተባባር የሚያከናውናቸው የቅርስ ጥበቃና ልማት ሥራዎችም ተጠቃሽ ናቸው።
ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃርም የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በቅርስ ዙሪያ በተለይም ቅርስን በመመዝገብ የተለያዩ የጥናትና የምርምርና ሥራዎችን በማካሄድ ሰፊ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዞን፣ የወረዳ፣ የሃይማኖት ተቋማትም ጭምር ቅርስን የመንከባከብና የመደገፍ ኃላፊነት እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ተከታታይ መድረኮችን በማዘጋጀት ምክክር እያደረገ መሆኑንም መረጃዎች ያሳያሉ። ኢትዮጵያ ያሏትን ቅርሶች በሚፈለገው ደረጃ በመመዝገብ፣ በማሰባሰብና በማደራጀት በመንከባከብ ለትውልዶች ለማስተላለፍ እንዲሁም በኢኮኖሚ የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ለማድረግ በቅንጅትና በመናበብ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ተግባር መሆኑን እነዚሁ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዳግም ከበደ
አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2015