ሪህ(Gout) በመገጣጠሚያ ላይ በተለይ ደግሞ በእግር ትልቁ ጣት ላይ በድንገት የሚጀምር ከፍተኛ ህመም ስሜት፣እብጠትና መቅላት የሚመጣ የህመም አይነት ነው ፡፡ሪህ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ በብዛት የሚከሰት ቢሆንም ሴቶች ካረጡ በኋላ ለህመሙ ተጋላጭነታቸው እየጨመረ ይመጣል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የሪህ የህመም ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ያለማስጠን ቀቂያ በድንገት የሚከሰት ሲሆን በብዛት የሚጀ ምረው ማታ ላይ ነው፡፡
• ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚያ ላይ ህመም፡- ምንም እንኳ ሪህ በአብዛኛው የሚከሰተው የእግር አውራ ጣት ላይ ቢሆንም በእግር መዳፍዎ፣በቁርጭምጭሚትዎ፣ በጉል በትዎ፣ በእጅዎ መገጣጠሚያዎች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ህመሙ ከጀመረ የመጀመሪያዎቹ ከ4 እስከ 12 ሰዓታት ውስጥ በጣም ሊባባስ ይችላል፡፡
• ቀጣይነት ያለው የህመም/ምቾት ያለመሰማት ስሜት፡- ከፍ ያለው ህመም ካለፈ በኋላ የተወሰነ ህመምና ምቾት ያለመሰማት ከቀናት እስከ ሳምንታት ድረስ ሊቀጥል ይችላል፡፡
• የመቆጥቆጥና የመቅላት ስሜት፡ – በህመሙ የተጎዳው መገጣጠሚያ የማበጥ፣ ሲነካ የማመምና መሞቅ ስሜት እንዲሁም የመቅላት ባህሪ ይኖረዋል፡፡
• እንቅስቃሴ መገደብ፡- ህመሙ እየፀና ሲመጣ መገጣጠሚያው መታዘዝ/ መንቀሳቀሱን ይቀን ሳል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የህመም ምልክቶች ካሉት ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ህመሙ ከመጣ በኋላ ህክምና ሳይደረግ በራሱ ጊዜ ከጠፋ ህመሙ እየተባባሰና መገጣጠሚያውን ስለሚጎዳው መታከም ያስፈልጋል፡፡
የህመሙ ምክንያት
ሪህ የሚከሰተው ዩሬት ክሪስታል የሚባለው ኬሚካል መገጣጠሚያ ውስጥ ተጠራቅሞ የመቆጥቆጥ ስሜት/inflammation/ እንዲጀ ምር ወይም እንዲነሳ በማድረግ የህመሙ ምልክቶች እንዲመጣ ያደርጋል፡ ፡ ዩሬት ክሪስታል የሚመጣው በደማችን ውስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን ከሚፈለገው መጠን በላይ ከፍ ሲል ነው፡፡
ሰውነታችን ዩሪክ አሲድን ፕዩሪንስ የሚባሉ ኬሚካሎችን በሚሰባብርበት ወቅት የሚመረት ሲሆን ፕዩሪንስ በተፈጥሮ በሰውነታችን ውስጥና በተወሰኑ እንደ ስጋና የባህር ምግቦች ውስጥ ይገኛል። በተጨማሪም ከፍ ያለ ዩሪክ አሲድ በሰውነታችን እንዲኖር ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አልኮሆል(በተለይ ቢራ) እና እንደ ፍሩክቶስ ባሉ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች መጠጣት ናቸው፡፡
ዩሪክ አሲድ በደምዎ ውስጥ በመሟሟት ከሰውነትዎ በኩላሊት አማካይነት እንዲ ወገድ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን ሰውነታችን ከሚፈለገው መጠን በላይ ዩሪክ አሲድን ካመረተ አሊያም ኩላሊትዎ ከሚገባው በታች ከሰውነታችን እያስወገደች ከሆነ የዩሪክ አሲድ መጠን በሰውነታችን ውስጥ በመጨመር ዩሬት ክሪስታል በመገጣጠሚያ ውስጥ እንዲፈጠር በማድረግ የህመም ስሜቶች እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
በሰውነትዎ ውስጥ በጣም ብዙ ዩሪክ አሲድ ካለዎ ሪህ ሊከሰት ይችላል፡፡በሰውነትዎ ውስጥ የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ፤-
• አመጋገብ፡- አመጋገብዎ ውስጥ ስጋ፣ የባህር ምግቦችን/sea food/፣ በፍሩክቶስ የፍራፍሬ ስኳር የጣፈጡ መጠጦች፤ አልኮሆል (በተለይ ቢራ) ማዘውተር የዩሪክ አሲድ መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርጉ ለሪህ ህመም ተጋላጭነትዎን ሊጨምር ይችላል፡፡
• ውፍረት፡- ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ ሰውነትዎ ብዙ ዩሪክ አሲድ እንዲያመርት ስለሚያደርግና ኩላሊትዎ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ለሪህ ያጋልጥዎታል፡፡
• የውስጥ ደዌ ችግሮች፡- የስኳር ህመም፣ የልብ ችግር፣ ያልታከመ የደም ብዛት፣ ሜታቦሊክ ሲንድረምና የኩላሊት ችግር ካለዎ ለሪህ ተጋላጭነትዎ ይጨም ራል፡፡
• መድሃኒት፡- ለደም ብዛት ህክምና ሊሰጥ የሚችሉ እንደ ታያዛይድ ዳይዩሬቲክስና ሌሎች እንደ አስፒሪን ያሉ መድሃኒቶች የዩሪክ አሲድ መጠንን ሊጨምሩ ይችላሉ፡ ፡
• በቤተሰብዎ ውስጥ መሰል የጤና ችግር ካለ፡- አንዱ የቤተሰብዎ አባል መሰል ችግር ከነበረው እርስዎም በችግሩ የመያዝ/ የመጠቃት እድልዎ ከፍተኛ ነው፡፡
• እድሜና ፆታ፡- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በወጣትነት እድሜያቸው ሪህ ሊይዛቸው ይችላል፡፡ ሴቶች እድሜያቸዉ እየጨመረ ሲመጣና በተለይ ሲያርጡ ለሪህ ተጋላጭነ ታቸው እየጨመረ ይመጣል፡፡
• ከአደጋ በኋላ ቀዶ ጥገና በቅርቡ ተደርጎልዎት ከነበረ
ለሪህ ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች
• ፈሳሽ ካለ ናሙና ተወስዶ መመርመር፣ የደም ምርመራ፡ራጅ እና አልትራሳውንድ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የኑሮ ዘይቤና የቤት ውስጥ ህክምና
ምንም እንኳ ዋናው ህክምና መድሃኒት መጀመር ቢሆንም የተወሰኑ የኑሮ ዘይቤ ለውጥ ማድረግ ህመሙን ለመቀነስ ሊረዳዎ ይችላል፡፡
• የሚወስዱትን የአልኮል መጠጥና በፍራፍሬ ስኳር/ፍሩክቶስ/ የጣፈጡ መጠጦችን መገደብ፡- ከነዚህ ይልቅ ውሃ በብዛት በመጠጣት
• የፕዩሪን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ እንደ ቀይ ስጋ፣የባህር ምግቦችን ያለማዘውተር
• መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና ክብደትን መቀነስ ሪህን እንዴት መከላከል ይቻላል? የህመም ምልክቶች በሌሉበት ወቅት ተጨማሪ የህመም ስሜቶች እንዳይመጡ
• ፈሳሽ በብዛት መውሰድ፡- ውሃ በደንብ መጠጣት
• የአልኮል አወሳሰድዎን መገደብ፡-
• የፕሮቲን ምንጭዎን መጠነኛ ስብ ከሚሰጡ የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶች ማድረግ
•የስጋ፣የዓሳና የዶሮ ምግቦችን መመጠን
• ክብደት መቀነስ ናቸው፡፡
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሚያዝያ 26/2011