
የጉዞው የባህር ውስጥ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኒኮ ቪንሰንት ተልእኮው እስካሁን ከተሰራው እጅግ ውስብስብ እና በርካታ የዓለም ሪከርዶችን የሰበረ ነው ብለዋል::
በፈረንጆቹ 1915 የሰጠመችው ኢንዱራንስ የተሰኘችው የሰር ኢርነስት ሻክልተን መርከብ ስብርባሪ አንታርክቲካ ጫፍ ወደል ባህር መገኘቱን ፎክላንድስ ማሪታይም ሄሪቴጅ አስታውቋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በፈረንጆቹ 1915 ከበረዶ ጋር ከተጋጨች በኋላ ሰጥማ የነበረችው መርከብ ከ3008 ሜትር ጥልቅ ላይ ተገኝታለች፡፡ መርከቧ ያለችበት አሁን የታሪክ ቦታ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
የአርኪዮሎጂስቶችን፣ አዋቂ የአካባቢ ፊልም ሰሪዎችን እና ሳይንቲስቶችን ያቀፈው የጉዞው ቡድን ከኬፕታውን ደቡብ አፍሪካ ተነስቶ በፖላር ምርምር እና ሎጂስቲክስ መርከብ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
በጉዞው ላይ የአሰሳ ዳይሬክተር የሆኑት መንሱን ቦውንድ፣ ቡድኑ “የኢንዱራንስ ምስሎችን በማግኘታችን እና በማንሳት ባለን መልካም እድል መደሰታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ይህ እስካሁን ካየኋቸው የእንጨት መርከብ ስብርባሪ ምርጡ ነው። ቀጥ ያለ፣ በባህሩ ወለል የሚኮራ፣ ያልተነካ እና ምንም ያልተነካ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የጉዞው መሪ ዶ/ር ጆን ሺርስ እንደተናገሩት ጉዞው “በኢንዱራንስ ግኝት የፖላር ታሪክ ሰርቷል፣ እና በዓለም ላይ እጅግ ፈታኝ የሆነውን የመርከብ አደጋ ፍለጋ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል ብለዋል፡፡
የጉዞው የባህር ውስጥ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኒኮ ቪንሰንት እንዳሉት ተልእኮው እስካሁን ከተሰራው እጅግ ውስብስብ እና በርካታ የዓለም ሪከርዶችን የሰበረ ነው።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን መጋቢት 2 /2014