በሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(ተመድ) ተልዕኮ በአገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ለማስቆም ከሱዳን ፓርቲዎች ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ ምክክር በትናንትው ዕለት ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን መንግሥት ማፍረሳቸውን ተከትሎ ሱዳን በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡
በሱዳን የሚገኘው የተመድ የተቀናጀ የሽግግር ዕርዳታ ተልዕኮ በሲቪል አስተዳደር ሽግግር ይደረግ በሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች የተስማሙባቸውን ጉዳዮች የያዘ ሰነድ ያዘጋጃል ተብላል፡፡
የተመድ የተቀናጀ የሽግ ግር ዕርዳታ ተልዕኮ ኃላፊ ቮልከር ፔርቴስ፣ ተልእኮው የተለያዩ አመለካከቶችን እና የውሳኔ ሃሳቦችን ከሱ ዳን ሕዝብ ለመስማት የሚያስ ችል በመሆኑ የምክክር ሂደቱን ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልጸ ውታል።
በፈረንጆቹ ጥር 10 የተመድ ልዑክ በሱዳን ያለ ውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት በሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ንግግር ሂደት መጀመሩ ይታወሳል።
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን በጥቅምት ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጁ እና ሉዓላዊ ምክር ቤቱን እና መንግሥትን ከፈረሰ በኋላ ሱዳን በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች።
በሉዓላዊ የሽግግር መንግሥቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አብደላ ሀምዶክ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ሱዳን በማያባራ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
የሱዳን ተቃዋሚዎች በአገሪቱ የሲቪል መንግሥት አስተዳደር እንዲዋቀር የሚጠይቁ ሰልፎች ሲያካሂዱ ቆይተዋል፤እያካሄዱም ይገኛሉ።
የሱዳን ጦር ከዚህ በፊት በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ 79 ዜጎች መገደላቸውን የሱዳን ሐኪሞች ማኅበር መግለጹም ይታወሳል።
ምንም እንኳ በሱዳን የሲቪል ወታደሩ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስተላለፍ የሚጠይቁ ሰልፎች ቢበረቱም፤ በጄኔራል አልቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር በበኩሉ በምርጫ ላልተመረጠ መንግሥት ስልጣን እንደማይሰጥ መግለጹ ይታወሳል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን የካቲት 9/2014