« ሴት ወደ ማጀት ወንድ ወደ ችሎት » ይሉት ብሂል ለረጅም ዘመናት እንደ መመሪያ ተቆጥሮ ሴቶች ወደ ወደዳኝነት ስራ ሳይቀርቡ ቆይተዋል። ዛሬም ድረስ በባህላዊ የዳኝነት፣ የግልግልና የሽምግልና ስርአት ያለው የሴቶች ተሳትፎ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በዘመናዊው አለም የፍርድ ቤት ስርዓትም ቢሆን እስከ ቅርብ ግዜ ከጥቂት ሴቶች በቀር ከሳሽ አልያም ተከሳሽ ሆነው ሲቀርቡ ካልሆነ ሊፈርዱና ሊወስኑ ችሎት ሲሰየሙ አይታይም። የዘርፉ ባለሙያዎች የሴት ዳኞች ቁጥር በሁሉም የዳኝነት እርከኖች ውስንነት ያለበት በመሆኑ በፌዴራልም ሆነ በክልል የማብቃትና የማቅረብ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ይናገራሉ።
«የሴት ዳኞችን ቁጥር በማብዛት ለህብረተሰቡ የተሻለ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቻላል፤ ለዚህ ደግሞ ማብቃት ይጠበቃል» የሚሉት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ናቸው። ፕሬዚዳንቷ እንደሚያብራሩት ሴቶች ለሙስናና ለጥቅማ ጥቅም ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ የተሻለ ፍትህ ይሰጣሉ ተብሎ ይታመናል። እስካሁን ግን በዳኝነት ስርዓት ውስጥ ያሉት ሴቶች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። እንደ ሀገር በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሴት ፕሬዚዳንት የተሾመው ለመጀመሪያ ግዜ ሲሆን በክልል ሁለት ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችን ሾሞ የሚያውቀው የትግራይ ክልል ብቻ ነው። ይሄ በከፍተኛው የዳኝነት ስርዓትና አመራር ያለውን ክፍተት የሚያሳይ ነው።
የትግራይ ክልል ከዚህ ቀደም ለስምንት ዓመት የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሩትንና በቅርቡ የተሾሙትን ጨምሮ ሁለት ግዜ እድሉን በመስጠት የሴቶችን ውጤታማነት ለማሳየት ችሏል። በመሆኑም እንደ ትግራይ ክልል ሁሉ ይህንን መልካም ተሞክሮ ለማስፋፋት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኩል በየደረጃው አስፈላጊው ሁሉ ይደረጋል የተጀመሩ ስራዎችም አሉ። በክልሎችም በኩል ከመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጀምረው ይህንን ተሞክሮ ማስፋፋት ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን ሴቶች ወደ ስልጣንና ኃላፊነት መምጣት ያለባቸው ለኮታ ማሟያ ሳይሆን ሰርተው እንዲያገለግሉ በመሆኑ ከመሾሙ በፊት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የማብቃት ስራ መሰራት እንዳለበትም ወይዘሮ መዓዛ ተናግረዋል።
ሴቶች ወደ ዳኝነት እንዲመጡ መስራት ሁለት ጠቀሜታ አለው፡፡ የመጀመሪያው ሴቶች ያላቸውን ከወንዶች እኩል ህዝብንና ሀገርን የማገልገል የዲሞክራሲያዊና የተሳትፎ የመብት ማክበር ሲሆን፤ በሁለተኛ ደረጃ ሴቶች ተፈጥሮ የሰጠቻቸውን ነገሮችን በጥልቀት የመመልከት ስጦታ መጠቀም ነው ያሉት ደግሞ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ ናቸው።
ዶክተር ፋና እንደሚያብራሩት፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ሀገር ሴቶች ወደ ህግ ትምህርት ቤት ሲገቡ ጀምሮ ለዳኝነት እንዲበቁ መስራት ይጠበቃል። በአንድ በኩል ወደ ህግ ትምህርት ቤቶች የሚገቡት ሴት ተማሪዎች ቁጥር ዝቅተኛ በመሆኑም ከሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ፍላጎቱ እንዲኖራቸው መሰራት አለበት። በሁለተኛ ደረጃ ከገቡትም መካከልም ቢሆን በህግ ትምህርት ቤት ቆይተው ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ አብዛኞቹ ወደ ዳኝነት ስርዓቱ ከመምጣት ይልቅ የሚያዘነብሉት ወደ ሌሎች ስራዎች ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የዳኝነት ስራ በችሎት አልያም በቢሮ ብቻ ተሰርቶ የሚያልቅ ባለመሆኑና ወደ ቤት ይዞ መሄድ፣ አምሽቶና ቅዳሜና እሁድንም መስራትን ስለሚጠይቅ ጫናው ብዙ በመሆኑ ነው። ይህም በወጣትነት ላሉ ሴቶች ቤተሰብ ከመመስረት ልጅ ከመውለድ ጋር በተያያዘ መሰናክል ይሆንባቸዋል። በመሆኑም ሊደረግ የሚገባው የማብቃት ክትትልና ድጋፍ እስከ መጨረሻው ሊዘልቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ወይዘሮ ጸሀይ መንክር በበኩላቸው ዛሬም ያለው የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ ቢሆንም በፊት ከነበረው ከቀን ወደ ቀን መሻሻል እየታየበት ነው ይላሉ። ወይዘሮ ጸሀይ የራሳቸውን ተሞክሮ በማንሳት እንደሚናገሩት በ2009 ዓ.ም እነሱ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመምጣታቸው በፊት (ገብተው የወጡ ቢኖሩም) በስራ ላይ የነበሩት ግን አንዲት ሴት ዳኛ ብቻ ሲሆኑ እሳቸውም በወራት ውስጥ ለቀዋል። በዛ ወቅት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ሰባት ሴት ዳኞች በአንድ ግዜ ተሹመው ወደ ስራ ገብተዋል። የእነዚህ ሴቶች መሾም ያመጣው ፋይዳ ግን በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰነ ሳይሆን እስከ ስር በመውረድ ለብዙ ሴቶች መነቃቃት የሰጠም ነበር ይላሉ።
ዛሬም ድረስ በማህበረሰቡም ውስጥ ለዳኝነት አይበቁም የሚል አመለካከት በስፋት አለ የሚሉት ወይዘሮ ጸሐይ፣ ወንድ ሁሉንም ነገር እንደሚችል እንደሚያውቅ ተደርጎ ይታሰባል ለሴቶች ሲሆን ግን ጥርጣሬ አለ። በዚህም ወንዶቹ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ስራው ላይ ሆነው ራሳቸውን ለማብቃት እድሉን ያገኛሉ። ከተሾሙም በኋላ በአመራሩም ሆነ በህብረተሰቡ በኩል ያለመቀበል አዝማሚያ አለ። በሌላ በኩል በራሳቸው በሴቶቹም በኩል ራሳቸውን የማብቃትና ወደ ዳኝነት የመምጣቱ ጥረት ክፍተት አለበት። ይህም የሆነው ተመርቀው ስራ ውስጥ ከገቡ በኋላ ራሳቸውን ለማሳደግ ሴቶች ተደራራቢ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ነው፡፡
ለማደግ እየሰሩ መማር ያስፈልጋል፡፡ ሴቶቹ ደግሞ እናት፣ ሚስት፣ ሰራተኛ ሆነው መማር ይከብዳቸዋል። ወደ ከፍተኛው አመራር እንዳይመጡም አንዱ መሰናክል ይሄ ነው። ለምሳሌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም ቢያንስ አስራ ሁለት አመት በህግ ጉዳይ መስራትና የመጀመሪያ ዲግሪ መያዝ ይጠበቃል። ይሄ ደግሞ የረጅም ዓመት ውጣ ውረድ የሚጠይቅ ነው። በእርግጥም ቦታው የግድ በተማሩና በበቁ ሰዎች ነው መሞላት ያለበት በመሆኑም ሴቶቹን ወደዚህ ለማምጣት ትምህርታቸውን አጠናቀው በስራ ላይ ያሉትን የዚህ ያህል ዓመት ድጋፍ እያደረጉ መጠበቅ ይገባል እንደ ማለት ነው።
እድሉ ከተገኘ በብቃትና በታማኝነት ረገድ ሴቶች የተለየ ችግር የለባቸውም የሚሉት ወይዘሮ ጸሀይ ሴት የያዘችው ዳኝነት የነብር ጭራን እንደመያዝ ነው ይላሉ። ሴቶች ጥንቃቄ ያደርጋሉ ይሄ ግን ፈርተው አይደለም። ሴት ስለሆነች ፍርድ የምታዘገይ አልያም ሴት ስለሆነች ፍርድ የምታጓድል የለችም። የተለየ ጥንቃቄ ለሚያስፈልጉ ጉዳዮች መረጃዎችን በማብላላት እውነታውን አፈላልጎ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ነው ይሄ ወንዶችም ቢሆን የሚያደርጉት ነው። በባህላዊው አካሄድ እንኳ ሴት ለሽምግልና እንኳ አትመረጥም ነገር ግን የበለጠ የማግባባት የማሳመን እድል ሴቷ አላት፡፡ ነገር ግን መንግስትና ህዝብ አሁንም ድረስ ይህን አቅም እየተጠቀሙበት አይደለም ይላሉ።
«የሴቶች ከዳኝነት የመገፋት ጉዳይ በኢትዮጵያ ብቻ ያለ አይደለም የየትኛውም ሀገር ታሪክ የሚያስተምረን ይሄንን እውነታ ነው። ነገር ግን እንደ ዳኝነቱ ሁሉ በስፋት የማይገቡባቸው መስኮች በርካታ በመሆናቸው መሰራት አለበት፤እንዳጠቃላይ በየዘርፉ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ነው» የሚሉት ደግሞ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ወይዘሮ እትመት አሰፋ ናቸው።
ወይዘሮ እትመት እንደሚሉት፤ በብዙ ሀገራት ያለው ተሞክሮ እንደሚያሳየው ለሴት ሲሰጥ የነበረው ዝቅተኛ የሆነው ነገር ግን አድካሚው የቤት ውስጥ ስራ ነው። ይሄ ደግሞ እድሉን እንዳያገኙና እንዳይበቁ መሰናክል ሆኖባቸው ኖሯል። ሴቶችን ማብቃት ዓለም አቀፍ ጥያቄ በመሆኑም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ወጥተዋል፡፡ ሀገራትም በየራሳቸው ህገ መንግስት የሴቶችን መብት የሚያስከብሩ የህግ አንቀጾችንም እየደነገጉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያም ህገ መንግስት አንቀጽ 35 የሴቶች የእኩልነት መብት የተረጋገጠ ሲሆን ይሄን ተከትለው የወጡ አዋጆችም አሉ፡፡ ነገር ግን አሁንም ውስንነት በመኖሩ ወደ ከፍተኛው አመራር እየቀረበ በመጣ ቁጥር እየቀነሰ ይሄዳል።
ይሄ ደግሞ ከስር ጀምሮ ለማስተማርና ለማብቃት የተሰራው ስራ ብቻ ሳይሆን ለሴቶች የተስተካከለ እይታ ባለመኖሩ እንደሆነ በቅርቡ በሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ አመራር ደረጃ የተሾሙ ሴቶች ለዚህ አንድ ማሳያ ናቸው። እነዚህ ሴቶች በአንድ ሌሊት ራሳቸውን ያበቁ አይደሉም፡፡ ከአመታትም በፊት ተምረው በቅተው የነበሩ ነገር ግን ያልታዩ ናቸው። ልዩነቱ ዛሬ የሚያያቸው አካል ማግኘታቸው ብቻ ነው። በተመሳሳይ አሁንም ያልታዩ ነገ የሚመለከታቸው ካገኙ የሚወጡ በርካታ ሴቶች ስላሉ የፌዴራሉ መንግስት ጅምር በራሱም በሌሎች ተቋማትና በክልሎች ዞንና ወረዳ ድረስ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 25/2011
ራስወርቅ ሙሉጌታ
Behandel obstipatie met medicijnen stada IJmuiden Les alternatives à la
médicaments disponibles en ligne
acquisto di farmaci marca Mylan Elan Sarandí Medikamente ohne ärztliche Verschreibung online bestellen
Medikamente ohne Rezept in Belgien Mochida Beringen prezzo di
farmaci con prescrizione in Italia
Sichere Bezugsquellen für Medikamente in der Schweiz
Nepenthes Piedras Negras indication du médicaments
en vente au Maroc
achat de médicaments en ligne Almus Brée (Bree) medicijnen discreet
verzonden
проста люби меня скачать,
ты просто люби люби меня скачать
полную версию сапар намазы қалай ниет етуге болады, сапар намазы шарттары 20 ғасырдағы ұлт азаттық көтерілістер,
ұлт азаттық көтеріліс себептері
сколько стоит обучение на юриста в казахстане,
сколько учиться на юриста после
9 класса в казахстане
онлайн гадания на месяц на картах бесплатно онлайн снятся ключ от квартиры венера слушать солнце
главные молитвы за детей чердак снится во сне
скачать песню магия ремикс предсказания гадания как называется гадание на суженого с 6 на 7 января с
зеркалом, гадание на рождество на будущее
бытовая магия читать полностью сонник к чему снится покойная тетя
сонник мужское семян фамилия володи из лето
в пионерском галстуке сонник толкование снов увидеть крысу
молитвы матроны о удаче сонник сжечь
книгу
стиральная машина процессор,
lg ai dd что это не заводится машина вызов мастера алматы, автоэлектрик алматы
24 часа тек алға әні, асыл тобы – тек алға
киім таңдау мәдениеті, киім кию мәдениеті
5 сынып ашық сабақ