ዳግም ከበደ
ውበት እንደ ተመልካቹ ነው ይባላል ።አንዱ አካባቢ ለውበት የሚሰጠው ትርጓሜ ለሌላው አካባቢ ሊዋጥለት አይችልም ።አፍንጫ ስንደዶ፣ ጥርሰ በረዶ፣አይናማ፣ ስስ ከንፈር፣ ዞማ ጸጉር ብሎ ውበትን መግለጽ እንደማይቻል የዘመኑ የውበት ጠበብት ይገለጻሉ ።ምክንያቱም የአንዱን አካባቢ ከሌላው አካባቢ ውበት ለመለየት በአንድ መስፈርት ውስጥ ማስቀመጥ ፈጽሞ አይቻልምና ።ለዚህም ነው ውበት እንደ ተመልካቹ ነው የሚባለው፡፡
ከመብላትና ከመጠጣት ባሻገር የሰው ልጅ እርካታን ከሚጎናጸፍባቸው መንገዶች አንዱ ውበት ነው ።በየትኛውም ባህል ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ውበትን በተቀበሉት ልክ ይስማሙበታል ፤በተስማሙት ልክ ደግሞ ይደነቁበታል ።በመረጡትና በተሰማሙበት ልክም ቆንጆ ሆነው መታየትን ይፈልጋሉ ።አምረውና ተውበው ለመታየት ደግሞ ማህበረሰቡ ያመነበትን ወይም የተቀበላቸውን የመዋቢያ አይነቶች ይጠቀማሉ፡፡
የዓለማችን የውበት ጠበብም ስለውበት ብዙ ብላለች፤ በየዕለቱ ቀላል የማይባል ገንዘብ ውበትን ለመጠበቂያ ታወጣለች ።በየወቅቱ ቆነጃጅቱን እያወዳደረች ትሸልማለች…ሌላም ሌላም ።ለመሆኑ ውበት ምንድን ነው? ውበት በምን መስፈርት ይለካል? በምን ቋንቋ ይገለጻል? ውበት ከሥነ-ምግባር ምን ዝምድና፤ ከሃብት ጋርስ ምን ግንኙነት አለው?
ሥነ-ውበት (Aesthetics) የውበትን ጽንሰ ሃሳብ ምንነት፣ እሴቶች፣ አተያዮች እንዲሁም የመገምገሚያ መስፈርቶችን የሚያጠና ዐቢይ የፍልስፍና ዘርፍ ሲሆን የዛሬው ጸሁፌ ዋና ዓላማም ስለ ውበት አጭር ሐተታ ማቅረብ ይሆናል ።የሥነ-ውበት ፈላስፎች ውበት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ በአጠቃላይ የሰው ልጅን፣ ኪነ-ህንጻን፣ ስዕልን፣ ሙዚቃን፣ ቅርጻ-ቅርጽን፣ ቲያትርን፣ ስነጽሁፍን፣ ፊልምንና የመሳሰሉትን የሰው ልጆች የጥበብ ስራዎች እንዲሁም የተፈጥሮን መስህቦች አካቶ የሚያጠና ዘርፍ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
ውበት ማለት የአንድ ነገር የሚስብ፤ የሚያረካ ወይም የሚያስደስት ገጽታ ወይም ሁኔታ ማለት ነው። ውበት ውጫዊ ቅርጽን፣ ቀለምን፣ መጠንን፣ መልክን ወይም ደምግባትን አልያም ውስጣዊ ማንነትንና ሥነ-ምግባርንየሚመለከት ጉዳይ ሊሆን ይችላል ።ነገር ግን አስቸጋሪው ጥያቄ ማንን የሚስብ፣ ማንን የሚያስደስት ወይም የሚያረካ ነው የሚለው ነው – የውበቱን ባለቤት? ማህበረሰቡን? ማንን? የሚለውን ማለት ነው፡፡
የዓለማችን ሊቃውንት እነዚህን መሰረታዊ የሥነ-ውበት ጥያቄዎች ለመመለስ በሁለት ታላላቅ ጎራ ተሰልፈው ለበርካታ ዘመናት ተሟግተዋል፤ መጻህፍትን ጽፈዋል፤ የሰው ልጆችን የአስተሳሰብ አድማስም አስፍተዋል። በመጀመሪያ የምናገኘው የሁሉን አቀፎች ወይም የፍጹማውያኑን ርዕዮተ ዓለም ነው፤ ይህም ውበት መለካት ያለበት ነገሮቹ በራሳቸው ባላቸው ማንነት እንጂ ከእነርሱ ውጪ በሚገኝ ማንኛውም ነገር ላይ ማለትም በማህበረሰቡ ወግ፣ አመለካከት ወይም እምነት ላይ ተመስርቶ መሆን የለበትም የሚል አቋም የሚያራምድ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በታተመ «ባህል ወቱሪዝም» የተሰኘ መጽሔት ላይ «ሴቶችና የውበት ማድመቂያቸው ድሮና ዘንድሮ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሑፍ ስለቁንጅና እንዲህ ይላል….
«ለቁንጅና በዓለም ላይ ያልተደረገና ያልተሞከረ ጥረት የለም። የፈረንሳይ ንግስት ኢውጀኒ ገላዋን በታጠበች ቁጥር ለሰውነቷ ቆዳ ማሳመሪያና ማለስለሻ አንድ ቅርጫት ኢንጆሪ ያስፈልጋት ነበር። ቤድፎርድ የተባለች የሆላንድ ወይዘሮ ደግሞ ገላዋን ስትታጠብ አንድ ደርዘን ጠርሙስ ወተት አዘጋጅታ ከውሃ ጋር በመቀየጥ ለሰውነቷ የተለየ ውበት ለመስጠት ትጥር እንደነበር ይነገርላታል።»
ሁሉም የሰው ልጅ ለውበቱ የሚጨነቅ ቢሆንም ሴቶች የበለጠ ለውበታቸው ስሱ ናቸው። በአንጻሩ ደግሞ ወንዶች በሴቷ ፊት የሚታይ ጀግንነታቸው ብቻውን ውበታቸው እንደሆነ ተደርጎ ሲቆጠር እናያለን። በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በጦር ጀግንነት ፊትአውራሪዎች በበዙባት አገር።
ሥነጽሑፋዊ ሥራዎቻችንም የወንዶችን ሳይሆን የሴቶችን ውበት ነው በብዛት አድምቀውና አድነቀው የሚጽፉት። ቆንጆ መባልና ውብ ሆኖ መታየት ለራስ ያለን ግምት ከፍ ለማድረግ ይረዳል። በራስ መተማመን ይጨምራል። በሌሎች ዐይን ውስጥ ውብ ሆኖ መታየት ደስ ይላል። ለዚህ ታዲያ የውበት መጠበቂያና መዋቢያዎችን መጠቀም በየትኛውም ማህበረሰብ ዘንድ የተለመደና ማህበረሰቡ የሚቀበለው እውነታ ነው።
ይህን ያህል ስለውበት ለመንደርደሪያነት ከጠቃቀስን ወደ ስለ አፋር ወንዶች የጸጉር አሰራር በጥቂቱ ላስቃኛችሁ፡፡የአፋር ወንዶች ከሴቶቹ ይልቅ ለውበታቸው ይጨናቃሉ ።መጨነቅም ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜያቸውን ለሸጉራቸው ውበት ያጠፋሉ፡፡
ይኖርበታል። በየጊዜው ንጽኅናውን መጠበቅና ቅባት መቀባትም ይጠበቃል፡፡ጸጉሩ በሚፈለገው መጠን እንዲያድግ ማድረግ ያለበት ሁሉ አድርጎ በቂነው ብሎ ሲያስብ ወደ መጠቅለሉ ይገባሉ፡፡ለመጠቅለያነት የሚጠቀሙበትን ደግሞ የሰሊጥ እንጨት ያዘጋጃሉ ።
የአፋር ወጣትን ጸጉር ለመስራት ሌሎች ሁለት ሰዎች ያስፈልጉታል ።በሰሊጥ እንጨት ወይም በእስኪርቢቶ ቀፎ ለሁለት ይጠቀልሉለታል ።ከመጠቅለሉ በፊት ሞራ፣ና ቅቤ ወይም ቅባት ይቀባል፡፡ሞራው ነጭ እንደሆነ የሚያቆይ ሲሆን፣ ቶሎ እንዳይበታተንም ያደርገዋል፡፡ቅባቱ ከሌለ ቶሎ ይበላሻል ነጭ እንደሆነ አንድ ሳምንቴ ይቆያል ። መጨረሻ ላይም ሞራው ቀልጦ ይፈሳል፡፡
ዲረካሞ በወጣቶች ዘንድ እጂግ የሚወደድ ሲሆን ጥሩ የውበት መግለጫም ነው ።ወጣትነት ካለፈ ይህን አይነት መዋቢያ ስለማይጠቀም ጸጉሩን ይቆረጣል፡፡ከ30 አመት በላይ የሆነው ወንድ በኮልኮሎ እንዲዋብ ማህበረሰቡ አይፈቅድለትም ።በኮልኮሎ ስለሚያምር የአፋር ኮረዶች በጣም ይወዱታል ።
እንደ መውጫ
ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አሁን ላይ ለፋሽን ልዩ ቦታ የሚሰጡ ናቸው። ይህን ጉዳይ ከዚህ ቀደም በእንግድነት የጋበዝናቸው ሜካፕ አርቲስት አትክልት፣ ዲዛይነር ዮርዳኖስ እንዲሁም ኢንተርናሽናል ሞዴል ፈቲያ ገልፀውልን ነበር። ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ (ሃበሻ) መዘነጥ፣ ውበቱን መጠበቅ፣ መልበስን የሚወድ ማህበረሰብ መሆኑን መረዳት እንችላለን።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያውያን በባህላቸውና ባላቸው የራሳቸው የፋሽን ስልት ተውቦ ለመታየት ይጥሩ ነበር። የአፋር ወንዶችን እንደ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል። አሁን ላይ ደግሞ በተለየ መንገድ በማህበራዊ ድረ ገፅና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ይህን ልምድ በማስፋት የፋሽን ኢንዱስትሪው እንዲያድግ እየሰሩ መሆኑን ምልክቶችን አይተናል።
ኢትዮጵያውያን ለዓለም ልናስተዋውቀው የምንችለው ቋንቋ፣ ውበት አጠባበቅ፣ አለባበስ፣ አመጋገብና ሌሎች በርካታ ነገር እንዳለን ማሳየት ስንችል ነው። ይህን በፋሽን ኢንዱስትሪው አማካኝነት ለማስተዋወቅ ደግሞ ባለሙያዎቻቸን ተግተው ሊሰሩ ይገባል እያልን ሃሳባችንን እዚህ ላይ እንቋጫለን።
የአፋር ኮበሌዎች በብዛት ከሚጠቀሙበት የጸጉር አሰራር መካከል ቀዳሚው “ አይዲ ዲሪካሞ” ይሰኛል በአማርኛ “ኮልኮሎ” ይባላል ።የአፋር ኮበሌ (ጎረምሳ) በኮልኮሌ ለመዋብ ጸጉሩን ንጹህ አድርጎ ማሳደግ
አዲስ ዘመን ጥር 03/2013