ሰሞኑን የአልሸባብ የሽብርተኛ ቡድን በኬንያ ዱስ ሆቴልና በአቅራቢያው በሚገኘው አንድ የቢሮ ህንጻ ላይ የቦምብ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ኤዲተርና የጋዜጣው የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ ፕሬዚዳንት ኪሚኮ ዴ ፍሪታስስ ታሙራስ በፃፈችው ዘገባ ላይ የሞቱና የተጎዱ ሰዎች ምስሎች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ በዚህም ኬኒያውያን ቁጣቸውን ገልፀዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቲዊተር ገፃቸው ላይ ስለደረሰው ጭካኔ የተሞላ ጥቃት ጋዜጣው የሸፈነበትን መንገድ ተቃውመዋል፡፡ ብዙዎቹም ጋዜጣው የሞቱና የተጎዱ ሰዎች ምስሎችን በዚያ መልኩ መጠቀሙ ሰብአዊነት የጎደለው ዘገባ መሆኑን በመጥቀስ እንደዚህ አይነት ምስሎች ላይ ማተኮር አስፈላጊ አለመሆኑን ፅፈዋል፡፡
በምስራቅ አፍሪካ ዘጋቢ ካላቸው የሚዲያ ተቋማት መካከል የአሶሼቲቭ ፕሬስ ፎቶ አንሺ ካላሊል ሴኖንሲ አንዱ ነው፡፡ በዚህ ካሜራ ማን ከታተሙ ምስሎች አንዱ በጥቃቱ የተጎዳው ሰው ይሰራበት የነበረው ጠረጴዛ ላይ ወድቆ የሚያሳይ ምስል ነው፡፡ በተለይም ምስሎቹ እንዲታተሙ የፈቀዱ አዘጋጆች ምስሎቹ በቀጥታ እንዲወጡ ያደረጉት ጥቃቱ ገና በቁጥጥር ስር ሳይውል እና ጥቃቱ ከተፈፀመበት ህንፃ ማንም ሰው መውጣት ሳይጀምር በመሆኑ የዚህ አይነት ተግባር ሃላፊነት የጎደለው ስራ መሆኑን ያመላክታል፡፡
በወቅቱ በሚያስገርም ሁኔታ የሟቾቹ ቤተሰቦች ሳይነገራቸው በፊት ምስሎቹ ለህትመት በቅተው ነበር፡፡ የዘ ኒው ዮርክ ታይምስ አዘጋጆች ኬንያውያን ስለ ጋዜጣው የሰጡትን ትችት ከቁብ የቆጠሩ አይመስልም፡፡ በዚህም መግለጫ ለመስጠት ዝግጅት አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጦቹ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡና ለሰሩት ስራ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ ይህም ሁኔታ እጅግ የከፋ እና አደገኛ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ከጋዜጦቹ ምላሽ አንዱ የታተሙት ምስሎች በናይሮቢ ላይ የተፈጸመው ክስተት የተለየ መሆኑን ለማሳየት እና ምን ያክል ሰዎቹ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት መሆኑን ለማስረዳት ነው የሚል ነው፡፡
ጋዜጦቹ በጽሑፎቻቸው መልስ በሚሰጡበት ጊዜ ‹‹የጥቃቱ ሰለባዎች እና በጥቃቱ ለተጎዱ ሰዎች ከፍተኛ ክብር እንሰጣለን›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ‹‹ለአንባቢዎች በወቅቱ የተፈጠረውን አሰቃቂ አደጋ በምስል አስደግፎ መንገር ያስፈልጋል›› ብለው ያምናሉ:: የመረጡዋቸው ምስሎች ስሜታዊነት የሚፈጥሩ ሳይሆን ትክክለኛውን ሁኔታ የሚገልፅ ነው፡፡› እና በዓለም ሁሉ እውነታውን ለማሳየት ተመሳሳይ አተገባበር እንደሚጠቀሙ አስረግጠው ተናግረዋል:: ነገር ግን ኬንያውያን የጋዜጦቹን ምላሽ አልተቀበሉም፡፡ ብዙ ጊዜ ከጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ በመነሳት የምዕራባዊያን ዜና ድርጅቶች በሀገራቸው ውስጥ ምን እንደሚከሰት በተለያየ መንገድ ከፋፍለው ያመላክታሉ:: በአብዛኛው የእነሱ ቃላት እና ምስሎች ጉዳት የደረሰባቸው አገራት ወይም ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡
ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ የተሰነዘረበት ተቃውሞ ስለ አንድ ፎቶ ወይም ታሪክ አይደለም፡፡ ነገር ግን በጣም አሰቃቂ እና ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊቶች በማጉላት ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የምዕራባውያኑ አዝማሚያ በመከተል በተለይ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ ብዙ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ሌሎች ደግሞ የዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በምዕራቡ ዓለም አሰቃቂ ወንጀሎች እና የሽብር ጥቃቶች ላይ ምንም ዓይነት አስደንጋጭ ምስሎች ያላካተቱ ዜናዎችን መስራቱን ያስታውሳሉ፡፡ እንዲሁም በናይሮቢ ጥቃት ከደረሰ በኋላ በኢራቅ ኢስላማዊው የሽብርተኛ ቡድን በሶሪያ ውስጥ ባደረሰው የቦንምብ ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ኬንያውያን ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ይህንን አደጋ በተመለከተ ያወጡት ዘገባ የሞቱ አሜሪካዊ ፎቶ ከማውጣት ይልቅ በናይሮቢ ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ሽፋን መስጠታቸው ተስተውሏል፡፡
በዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ጽሑፍ ላይ የተሰጠው አፀፋዊ ምላሽ በዋናነት ያተኮረው በኪሚኮ ዴ ፍሪታስስ-ታሙራስ ላይ ነው፡፡ ምንም እንኳን ፎቶግራፎቹ ሲመረጡ ሙሉ ቁጥጥር እንደሌላቸው ብትናገርም የምስራቅ አፍሪካ የዜና ማእከል አዛዥ እንደመሆኗ በቀጣይ በሚወጡ ጽሑፎች ውስጥ ከሚቀርቡት ፎቶዎች ላይ ስልጣን ሊኖራት ይገባል ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ፡፡ በመጀመሪያ የወጡት ምስሎች ለሟች ቤተሰቦች አክብሮት ለማሳየት ሲባል እንዲጠፉ ጠይቀዋት ነበር:: ፎቶዎቹ እንደማይወገዱ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ ደግሞ አንዳንድ የቲዊተር ተጠቃሚዎች ከኬንያ እንድትባረር የሃሽታግ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ በተጨማሪም ኬንያውያን በቼንጅ ኦርግ ድረገፅ ላይ ፊርማ በማሰባሰብ ኪሚኮ ዴ ፍሪታስስ-ታሙራስ ካለችበት እንድትፈለግና በፈጸችው ድርጊት ምክንያት ማናቸውም የነዋሪነት ማረጋገጫ እንድትከለከል ጠይቀዋል፡፡
ጋዜጠኞችን ወደ ሀገራቸው ለማባረር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ቀደም ብሎ የውጭ ጋዜጠኞች የነጻ ፕሬስ ዋጋን ከኬንያ መማር ያስፈልጋል የሚሉትን አባባል ውሸት አድርጎባቸዋል፡፡ የሴታዊነት አቀንቃኟ ጄል ፒቮቪች የኬኒያውያን ፍሪታስስ ታሙራን ከአገር ቤት የማስወጣት ጥያቄ “ፀረ-ዴሞክራሲያዊ” እና በነፃው ፕሬስ ላይ የተሰነዘረ ጥቃት መሆኑን ተናግራለች፡፡ የኬኒያውያን “ፀረ-ዲሞክራሲ” ባህሪ ላይ የተላለፉት ክሶች በተመለከተ ብዙዎች በመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ላይ ተመስርቶ ብሄራዊ የዘረኝነት ምልክት ነው ይላሉ፡፡ ይህን ሁኔታ ደግሞ የዜና ድርጅቶች እና የውጭ ሀገራት ተወካዮች አተገባበራቸው ላይ የሚሰነዘሩትን ነቀፋዎች ለማስወገድ የሚያስችላቸው የመከላከያ መልስ ሆኖላቸዋል፡፡
የኬንያ ታዋቂ ጸሐፊ ኪግሮ ማቻሪያ በኬንያውያን ቁጣ የውጭ መገናኛ ብዙሃን እየሰጡት ያለው ትችት ላይ ትክክለኛ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በቲውተር ላይ በተደረገላቸው ቃለመጠይቅ ትክክለኛ የሆነ አመለካከት ያላቸው ጋዜጠኞች ትክክለኛውን ሀሳብ ሳይሸራርፉና ሳይፈሩ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ በጋዜጠኝነት ፖሊሲ ላይ ተቀምጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፕሬስ ነጻነት ከውጭ ጋዜጠኝነት ነጻ መሆን አለበት፡፡ ይህ የሚሆነው በአገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች የሚፈለጉትን እንዲያደርጉ ነው:: ከዚህ ውስጥ አንዱ ለግጭትና ስለ ዴሞክራሲ እድገትና ድክመት በነፃነት መናገርን ያካትታል፡፡
ተፅዕኖ ፈጣሪ የፊልም ሠሪ፣ ሙዚቀኛ እና የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ጂም ቹቹ ኬንያውያን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሰጡት ምላሽ በመደገፍ በሀገሪቱ ውስጥ የውጭ መገናኛ ብዙሃን ለአፍሪካ የሚከተሉት የዘገባ ሁኔታን ተችታለች፡፡ የመገናኛ ብዙሀኑ አዘጋገብ የተመሰረተው በተጋነነ ተቋማዊ ልምዶች ነው፡፡ በአሜሪካ ትላልቅ የሚባሉ የመገናኛ ብዙኃን ጥቁር አሜሪካኖች ጥቃት ሲደርስባቸው በተለያየ መንገድ እንደሚያሳዩ በቂ ማስረጃዎች እንደነበሩ አክላለች፡፡ ‹‹ጥቁር ህዝብ በአሜሪካ ውስጥ ከሚገኘው ነጭ ዋጋ ያነሰ ነው፡፡›› ትላለች፡፡ ይሄንን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በፎቶ በተደጋጋሚ እንደሚለቀቁ ትገልፃለች፡፡ በአሜሪካ ነጮች እንደ አስፈላጊ እና ጥቁር ህዝብ ደግሞ አላስፈላጊነትን የሚገልፁ ባህሎች አሏቸው፡፡
የዘ ኒው ዮርክ ታይምስ አርታኢዎች በናይሮቢ ላይ የሰሩትን ዘገባ በቀጣይ በሚኖራቸው የዘገባ ስራ ላይ እክል መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ባለፈው ዓመት ላይ በዘ ኒዎርክ ታይም ጋዜጣ ላይ የተጎዱና የሞቱ ሰዎችን ምስል መጠቀም ጎጂ መሆኑን የሚገልፅ ፅሁፍ ወጥቶ ነበር፡፡ ፀሀፊዋ ሳራ ሴንቲልስ እንዳለችው ማንኛውም መገናኛ ብዙሀን የሚጠቀሙት ፎቶና ቪድዮ በተለይ የሚረብሹ ምስሎች መጠቀም ለሌሎች አገራት ፖለቲካዊ ትርፍ መስራት መሆኑን ትናራለች፡፡ በአሜሪካ ጥቁር ህዝቦች በፖሊስ እየተገደሉ ሲሆን የሞቱና የተጎዱ ሰዎችን ፎቶ መጠቀም ይበልጥ ሁኔታዎችን እንደሚያባብስ ትገልፃለች፡፡
ሴንቲሊስ እንደምትለው ከሆነ፤ የሞቱ ሰዎችን የሚመለከት የሚወጡ እውነታዎችን ሌሎች የሚጠቀሙበት በመሆኑ ነባር ታሪኮችን መርዟል፡፡ በምእራቡ ዓለም ያሉ የሽብርተኝነት ሰለባዎችን እና በሌሎች ሀገሮች ላይ የሚገኙ የችግሮቹ ሰለባዎች በተመሳሳይ ክብደት አይታዩም፡፡ ለአብነትም በአፍሪካ የሚገኙ የሽብርተኛ ሰለባዎች ሕይወት ዋጋ አይኖረውም የእነሱ ሞት አብዛኛውን ጊዜ ተፅእኖ አይፈጥርም፡፡ እናም በሞታቸው ዙሪያ መታየት ያለበት ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ እነዚህን ሙግቶች ለህትመት ማገጃነት ማቅረብ በተለይ እንደ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ያሉ ተቋማትን በምሳሌነት በማቅረብ እና ለሞቱት ቤተሰቦች አክብሮት እንዲሰጥ የታተሙ ምስሎችን ወይም ታሪኮችን መቃወም እንዲሁም አጠቃላይ እገዳውን መደገፍ ማለት አይደለም:: ነገር ግን በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ በተቀመጡበት ሀገራት ውስጥ ስላለው ሁኔታ ሪፖርት ሲያደርጉ የአቀራረባቸውን ሁኔታ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
የውጭ ጋዜጠኞች አባላት እንደ ዜና ድርጅት ተወካይነታቸው በምዕራቡ ዓለም ውስጥ አፍሪካውያን የሚታዩበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ከፍተኛ ኃይል አላቸው:: ይሁን እንጂ, ሪፖርቶቻቸው በአብዛኛው ይህን ከግንዛቤ የከተተ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሥራቸው ከምዕራባዊ የዜና ማሰራጫዎች ጋር እና በምዕራቡ ዓለም አካላት የመጡ እውነታዎችን የሚያንፀባርቅ ነው::
አዲስ ዘመን ጥር 20/2011
መርድ ክፍሉ