በረሮዎች ከእናታቸው ተለያይተው ለሳምንት ያክል መቆየት ይችላሉ፡፡
• ሳይተነፍሱ ለአርባ ደቂቃ ያክል መቆየት እንደሚችሉ ይነገራል፡፡
• በረሮዎች 75 በመቶ የህይወት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት እረፍት በማድረግ እና ሙቀታማ ስፍራዎች ነው፡፡
• ለመተንፈስ አፍ አያስፈልጋቸውም፡፡
• በረሮዎች የፕሮቲን ጎተራ በመሆናቸው ግብፆችና ግሪኮች ከሻይ ጋር አብሮ በማፍላት ለህክምና አገልግሎት ይጠቀሟቸዋል፡፡
• በሰዓት እስከ ሶስት ማይል መሮጥ ይችላሉ፡፡
• አንድ በረሮ በተወለደ በ36 ቀናት ውስጥ ወደ ጎልማሳነት ይቀየራል፡፡
• ከተወለደ አንድ ቀን የሆነው በረሮ ልክ እንደ እናቱና አባቱ በሰዓት እስከ ሶስት ማይል መሮጥ ይችላል፡፡
• እንዲሁም በተወለደ በአንድ ቀን ውስጥ ራሱን ከአጥቂዎች መከላከልና መርዝ ማስተላለፍ ይችላሉ።
• አንዳንድ በረሮዎች በአልኮሎች በተለይ ደግሞ በቢራ ሽታ ይሳባሉ፡፡
• በረሮዎች ከ280 ሚሊዮን ዓመት በፊት እንደተፈጠሩ ይነገራል፡፡
• በመላው ዓለም ከ4000 በላይ የበረሮ አይነት አለ፡፡ በጣም የተለመደውና የሚታወቀው የጀርመን በረሮ በመባል የሚታወቀው የዝርያ አይነት ነው፡፡
• ደመ ቀዝቃዛ በመሆናቸው በረሮዎች ያለ ምግብ ለአንድ ወር መቆየት ሲችሉ ለመኖር የሚመርጡት ደግሞ በሞቃታማ ቦታዎች ስለሆነ ያለ ውሃ ከአንድ ሳምንት በላይ መቆየት አይችልም፡፡
• ለመኖሪያነት ደግሞ የምግብ ማብሰያ ቦታዎችን በተለይ ይመርጣሉ፡፡
• ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ቀዳሚ ምርጫቸው እንደሆነ ይነገራል፡፡
አዲስ ዘመን ሐምሌ 26/2012
ሞገስ ፀጋዬ