ጥበብ ባለቤትዋን ስታገኝ ትፈካለች።ከጠቢብ ጋር ስትገናኝ እንደ ባቢሎን ወንዝ ጅረቶች ኩልል ብላ በመንቆርቆር ደስታን ታጎናፅፋለች። እርግጥ ግሩም ለትወና ትወናም ለግሩም ተባብለዋል። እርሱና ጥበብ በአጋጣሚ ተገናኝተውና ተሸናኝተው ልዩ ውህደትን ፈጥረዋል።በፈጣሪው ልቦና ተወልዶ፣ በምናብ ፈጠራ ተሰናስሎ የዓለምን ሌላ መልክ ሊገልፅ የተፃፈ የፊልም ጽሑፍ ከግሩም ኤርሚያስን ጋር ከተገናኘ ሕይወት ይዘራል።
ወታደር ሆኖ ፊልም ላይተውን ቢባል ወታደሩን ሆኖ የምታገኙት አዲስ አበባ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ተወልዶ ያደረው ግሩም ወታደር ሆኖ ፊልም መስራት ሳይሆን የእውነት ወታደር መሆንን አጥብቆ ይመኘው የነበረ የልጅነት ህልሙ ነበር። ህይወት በራስዋ ዑደት መርታ ዛሬ ትወና ላይ አንግሳው አረፈች።
ጥበብ ያማረ ዙፋን የሚሰጣት ስታገኝ በልዩ ግርማ ትነግሳለች።እስዋም ውለታ ቢስ አይደለችምና ስለስዋ ብዙ የሆነን መርጣ፣ የለፋላትን አክብራ፣ ያሳደጋትን ከፍ አድርጋ ልዩ ክብርን ትቸራለች። ፀባየ ሰናዩ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ከፊልም አለም ስራና ስኬቱ ባለፈ የእረፍት ጊዜ የትና በምን? እንዴትና ከማን ጋር ያሳልፋል? ማህበራዊና ቤተሰባዊ ህይወቱ ምን ይመስላል? … በሚሉት ዙሪያ ገባ ወግ እያወጋን ቆይታ አድርገናል።
የስኬት ማሳያዎች
ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ በትወና ተሳትፎ ባሳየው ድንቅ ችሎታ የተለያዩ ሽልማቶችን የግሉ አድርጓል።ከእነዚህም ውስጥ በአምስተኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ምርጥ ወንድ ተዋናይ (በትዝታህ)፣ በስምንተኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ምርጥ ወንድ ተዋናይ (በ400 ፍቅር)፣በሁለተኛው ጉማ አዋርድ ምርጥ ወንድ አክተር ምርጥ አክተር (በጪስ ተደብቄ)፣ በአስረኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፊስቲቫልና በጉማ አዋርድ በተመሳሳይ ምርጥ ወንድ አክተር (በላምባ)፣ የአድማጮች የዓመቱ ምርጥ አክተር በተከታታይ በዛሚ
90.7 እና በሸገር ኤፍ ኤም ለዛ አዋርድ ላይ ተሸላሚ በመሆን በፊልም መስክ በተከታታይ የነገሰ የጥበብ ፈርጥ ነው።
የመዝናኛ ምርጫ ስመ ጥሩ አርቲስ በናፍቆት የሚጠብቀው ከራስና ከቤተሰቡ ጋር በልዩ ሁኔታ የሚያሳልፈው ልዩ ቀን አለ፤እሁድ።እውቅና ሲጨምር ኃላፊነት ሲበረክት ብዙ ማረፍ ወደ ብዙ ትጋት ይቀየራል።ታታሪው ግሩም በእሁድ አይደራደርም ለራሴና ለቤተሰቤ የምሰጠው ልዩ ቀን ነው።“ከባለቤቴና ከልጆቹ ጋር የማሳልፈው መልካም ጊዜዬ
ነውና እጅግ እወደዋለሁ” ይላል።
አንዳንዴ ከከተማ ወጣ ያሉ ተፈጥሮዓዊ ቦታዎችና መዝናኛ ስፍራዎች በአብዛኛው ደግሞ ቤት ውስጥ የእረፍት ጊዜውን የሚያሳልፈው ግሩም ልቦለድ መጽሐፍቶችን ማንበብ፣ ፊልሞችን ማንበብ፣ ከሙያው ጋር የተገናኙ ነገሮችን ማገላበጥ ከቤተሰቡ ጋር ጨዋታና ውይይቶችን ማድረግ፤ ከልጆቹ ጋር አብሮ ማሳለፍ የዕረፍት ሰዓቱን ያማረ የሚያደርጉለት ተግባራቶቹ ናቸው።
በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳታፊ የሆነው ግሩም በእረፍት ቀኑ ከቤተሰብና ከወዳጆቹ ጥየቃ የሚተርፈው ጊዜ ከልጅነቱ ጀምሮ እጅጉን የሚወደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር ተለምዶዓዊ ተግባሩ ነው።ግሩም ከእውቅናው በፊት የነበረው ማህበራዊ ህይወቱ፣ ባህሪውና የአናኗር ልምዱ አሁንም በዚያው መልክ ያስቀጠለ በዝና ምክንያት ማንነቱን ያልዘነጋ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩለታል።
ምግብና ልብስ የለበሰው ሁሉ የሚያምርበት ግሩም ሲያሻው ጨርቅ ሱሪ ከሸሚዝ ጋር ሲፈልግ ካኔቴራ ከጅንስ ጋር ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ ይለብሳል።የልብስ ሳጥኑን ሲከፍት ይህ አሪፍ ነው ብሎ ያመነበትን ይመርጣል።በአለባበስ ሁለገብ ነኝ የሚለው አርቲስቱ ወቅቱን በጠበቀ ልብስ መዘነጥም ልምዱ መሆኑ ይናገራል።
ከአያቱ ጋር ያደገው ግሩም ድጋሚ የመፈጠር ዕድል ቢያገኝ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሌላ መሆንን ፈፅሞ አይፈልግም። ኢትዮጵያዊ የባህል ምግቦች ደግሞ ምርጫዎቹ መሆኑን ይናገራል።ከልጆቹ ምግብ አብስለህ አብላን ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢቀርብለትም ሆኖለት አያውቅም።ባለሙያ ሚስቱ እንዳሰነፈችውና በእርስዋ ተከሽኖና ጣፍጦ የሚቀርብለት ምግብ ለምዶ ማብሰል ቀርቶ መሞከር እንኳን እንደሚያዳግተው ይናገራል።ጥሬ ስጋ (ቁርጥ)፣ ሽሮ በቃሪያ አልያም ደግሞ ጎመን በሚጥሚጣ ብቻ ምግቦቹ የሚያቃጥሉ ነገሮች ቀመም ተደርገው ከቀረቡ ግሩም አጣጥሞ የሚመገባቸው መሆኑን ደጋግሞ ይነግሮታል።
የአርቲስቱ መልዕክት “እኛ ኢትዮጵያዊያን ውስጣችን የታነፀው በትብብር መንፈስ ነው። አንድነትና ትስስራችን በአብሮነት እንዳይላቀቅ ሆኖ የተጋመደ ነውና አንዳችን ስላንዳችን በመተሳሰብ ይህን ጊዜ ማለፍ ግድ ይለናል።” ምክንያታዊ መሆን እጅጉን የሚያምነው ግሩም “የምታወራው ከሌለህ እጅህን አታውጣ”የሚለው አባባል እነደ ህይወት መርሁ ይጠቀምበታል። አበቃሁ ቸር ይግጠመን።
አዲስ ዘመን ግንቦት 9/2012
ተገኝ ብሩ
“የምታወራው ከሌለህ እጅህን አታውጣ” ግሩም ኤርሚያስ