አገራችን የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ከገባች ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል። በነዚህ ዓመታትም በርካታ አዎንታዊና አሉታዊ ክስተቶች ተስተውለዋል። በአዎንታዊ መልኩ ከሚነሱ በርካታ ጉዳዮችም ውስጥ አንዱ ቀደም ሲል በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ ኃይሎች ያለምንም ገደብ በአገራቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ ዕድል መሰጠቱ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ እምርታ ተደርጎ ይወሰዳል።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 137 የፖለቲካ ድርጅቶች በአገሪቱ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።ከነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ታዲያ አብዛኞቹ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተገኘውን የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም ዴሞክራሲን ለማሳደግ እና ለሕዝባቸው የሚጠቅም አማራጮች ከማቅረብ ይልቅ በተለያዩ ተራ አሉባልታዎች ጭምር አጀንዳ እየፈጠሩ ሕዝብን ሲያደናግሩ ይታያሉ። አንዳንዶቹም የሚከተላቸውን ኃይል ለተሻለ አገራዊ ልማት ከመጠቀም ይልቅ ለብጥብጥና ለውዝግብ ሲጠቀሙ ይታያሉ።
እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ለሕዝብ የሚጠቅም አጀንዳ ከመያዝ ይልቅ በአንድ በኩል ብሔርን በመጠቀም ፅንፍ የያዘ አመለካከት በመርጨትና ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ላይ በማተኮር አገሪቷን የሚከፋፍሉ አጀንዳዎችን በስፋት ሲያራምዱ ቆይተዋል።ከፊሎቹ ደግሞ በአንድነት ስም ሁሉንም በአንድ ማዕድ ውስጥ በመጨፍለቅ ፍጹም አምባገነናዊ ሥርዓት ለመፍጠር ሌት ተቀን ሲጥሩ ሰንብተዋል።በነዚህ መካከል ሚዛናዊነት ቦታ ሲያጣና ሲብጠለጠል የቆየበትን ነባራዊ ሁኔታም ተመልክተናል።በዚህ የተነሳም እነሆ የአገራችን የፖለቲካ አየር ባለፉት ሁለት ዓመታት መስከን አቅቶት ሲገነፍል ቆይቷል።
ከዚህም አልፎ በጥቂት ኃይሎች ትግልና ጥረት የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስና በአቋራጭ ወደሥልጣን ለመውጣት የቋመጡ ኃይሎችም ተስተውለዋል።እነዚህ ኃይሎች በተለይ የሕዝብን የኋላ ታሪኮች በማንሳት ሕዝብና ሕዝብን ለማጋጨትና በሚነደው እሳት መካከል መሪ ለመጨበጥ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል።ቢያንስ የሕዝባቸው መሠረታዊ ችግሮች ምንድናቸው የሚለውን ካለመረዳት ወይም በግል ፍላጎታቸው የተነሳ ለሕዝብ የሚጠቅም አማራጭ ይዞ ከመቅረብ ይልቅ ስሜታዊነትን ዋነኛ የትግላቸው አቅጣጫ በማድረግ ይንቀሳቀሳሉ።
በተለይ ያለገደብ የተከፈተውን የፖለቲካ ምህዳርና ቴክኖሎጂው የፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚሰሩ ኃይሎች ተበራክተዋል።በዚህም ጥቂቶች ተሳክቶላቸው በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የዜጎች መፈናቀል እንዲፈጠር ማድረግ ችለዋል።
የእነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ዋነኛ የፕሮፓጋንዳ አካሄድ
በሕዝብ ቁስል ላይ ቤንዚን በመርጨት በላዩ ላይ እሳት መለኮስ ነው።በተለይ ድህነትና ሥራ አጥነት በስፋት በሚገኝባትና አብዛኛው ዜጎቿም ወጣት በሆኑባት አገራችን አንድ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ወይም ወጣቱ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆን ከማነሳሳት ይልቅ ለዓመታት የተበዘበዘ አድርጎ ሆድ እንዲብሰው በማድረግ ለግጭት ቅርብ እንዲሆን ማነሳሳት የፖለቲካ ስልታቸው አድርገው ሲሰሩም ይስተዋላል።
በጣም የሚገርመው እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ሕዝብን ለአመጽ እና ለግጭት ለማስወጣት የቻሉትን ያህል በኮሮና ምክንያት ሕዝቡ ቤት እንዲቆይ ማድረግ አለመቻላቸው ወይም አለመሞከራቸው ትዝብትን የሚጭር ነው።ከዚህ አንጻር እኔም ሆንኩ አብዛኛው ዜጋ የታዘበውን በጥቂቱ ላንሳ።
በአሁኑ ወቅት ዓለምን እያተራመሰ ያለው የኮሮና ቫይረስ እንደሆነ ይታወቃል።ይህ ቫይረስ በአጭር ጊዜ አገራትን በማዳረሱና የመዛመት አቅሙም ፈጣን በመሆኑ ዓለም በአንድ ቋንቋ እንዲያወራ ያደረገ የዓለማችን ችግር ነው።ይህንን በሽታ ለመከላከል ደግሞ መንግሥታት ከወሰዷቸው እርምጃዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው መንገድ ዜጎቻቸው እንዳይወጡ ማድረግን ነው።በዚህ የተነሳ ባለፉት ሁለት ወራት በርካታ የዓለም ሕዝቦች በቤታቸው ተከርችመው ከርመዋል።ፋብሪካዎች ተዘግተዋል፤ እንቅስቃሴዎችም ተገድበዋል።
ይህ ደግሞ በአንድ በኩል በርካታ ማህበራዊ ቀውስን ያስከተለ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቀላል የማይባል የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ ያለ ችግር ነው።አገራችንም የዚህ ዓለምአቀፍ ችግር አንዱ አካል በመሆኗ የዜጎቿን እንቅስቃሴ በመገደብ በርካቶች በቤት እንዲውሉ አድርጋለች።አንዳንድ የመንግሥት እና የግል ተቋማትም ተዘግተዋል።ትናንሽ የንግድ እንቅስቃሴዎችም በመቆማቸው አሁን የምንገኝበት ሁኔታ ከፍተኛ አገራዊ ስጋት ውስጥ ነው።
መንግሥትም የችግሩን መከሰት ተከትሎ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።በተለይ በአንድ በኩል በእንቅስቃሴው መገደብ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሽታውን በዘላቂነት ለመከላከል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።በዚህም እስካሁን ባለው ሂደት በሽታው እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል።ስኬትም አስመዝግቧል።
አሁን እየተከናወነ ያለው ሥራ የሰብዓዊነት ሥራ ነው። በዚህ የተነሳ በርካታ የመንግሥት ኃይሎች በየፊናቸው ርብርብ ሲያደርጉ ይስተዋላል።ችግሩ ደግሞ በነሐሴ ሊደረግ የነበረውን የምርጫ ሂደት እንዲራዘም አድርጓል።በአንጻሩ የመንግሥት ሥልጣን በመጪው መስከረም 30 የሚያበቃ በመሆኑ ይህ ክፍተት የሚፈታበትን መንገድ በሕገመንግሥታዊ አግባብ ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው።
በሌላ በኩል በዚህ የችግር ወቅት ድምጻቸው ጠፍቶ የከረመው ቁጥራቸው ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ኃይሎች ሰሞኑን መንቀሳቀስ ጀምረዋል።ኮሮና መምጣቱ ከታወቀበትና በተለይ ቫይረሱ በአገራችን መከሰቱን ተከትሎ
መንግሥት ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዩ ማድረጉን ተከትሎ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከቤት ተከትተው ከርመዋል።
የሚያሳዝነው ቀደም ሲል ሕዝብን ለተለያዩ ብጥብጦች ለማሰለፍ ብዙም ያልከበዳቸው እነዚህ ኃይሎች ሕዝብ በኮሮና እንዳይጠቃ ከቤት እንዲውል ማድረግ ግን አልቻሉም።ይልቁንም ሕዝብን ከውጭ ትተው ራሳቸው ገብተው ከቤት ተከተው ከርመዋል።ይህ ደግሞ ለሕዝብ ማሰቡ የት ጋር ነው የሚል ጥያቄን ያጭራል።
በዚህ የኮሮና ዘመን በየጊዜው አንዴ በማህበራዊ ሚዲያ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመደበኛው ሚዲያ ጆሯችን እስኪሰለቸው ድረስ ሲያደነቁሩን የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች ድምጽ መጥፋት የአንዳንድ እንስሳትን ተፈጥሯዊ ባህርይ እንድናስታውስ ያደርገናል።
አንዳንድ እንስሳት የመኖራቸው ህልውና በወቅታዊ አየር ጸባይ ይወሰናል።አንዳንዶቹ የክረምት ወቅት አይስማማቸውም፣ ሌሎቹ ደግሞ የበጋ ወቅት ይከብዳቸዋል።በዚህ የተነሳ እነዚህ እንስሳት እነዚህን ለነሱ የማይመቹ ወቅቶች ለማሳለፍ ራሳቸውን ደብቀው ያቆያሉ።ለምሳሌ አንዳንድ የእባብ ዝርያዎች የክረምት ወቅትን የሚሳልፉት ራሳቸውን በአሸዋ ውስጥ በመቅበር ነው።
ልክ እንደነዚህ እንስሳት ሁሉ እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶችም ኮሮና እስኪያልፍ ራሳቸውን ደብቀው ሕዝቡን የራስህ ጉዳይ ማለታቸው ግርምትን የሚያጭር ነው።ከዚህም አልፎ እውን እነዚህ ድርጅቶች ተሳክቶላቸው ሥልጣን ቢይዙ እንዴት ነው የሚመሩን? የሚል መሠረታዊ ጥያቄም ያጭራል።በኔ ግምት የፖለቲካ ድርጅት ዋነኛ ዓላማ ሕዝብን ማገልገል ነው።ሕዝብን ለማገልገል ደግሞ ሲመች ብቻ ሳይሆን በችግሩም ጊዜ ከጎኑ በመቆም መሆን አለበት።ታዲያ ኮሮና እንዲህ ካስተዛዘበን ሌላ አደጋ ቢከሰትስ እንዴት እንተማመን ይሆን?
በሌላ በኩል እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎች ከፖለቲካ ውጪ ሕይወት አልባ መሆናቸውንም ያሳያል። ለዚህ መነሻ የሆነኝ ደግሞ ሰሞኑን ለጥቂት ቀናት በኮሮና ምክንያት ጋብ ያለው የፖለቲካ ወሬ እንደ አዲስ ማንሰራራቱ ነው።ገና ከኮሮና ስጋት ባልተላቀቅንበት በአሁኑ ወቅት እነዚህ ኃይሎች አዳዲስ የፖለቲካ አጀንዳዎችን እየፈጠሩ በማህበራዊ ሚዲያና በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ብቅ ብለው በድፍረት መናገራቸው ምን ያህል እፍረት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው።ይህ ደግሞ ኮሮናን ለመከላከል የተጀመረውን ጥረት ሁሉ የሚያደናቅፍ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል።
እንደው ለመሆኑ በዚህ ወቅት በቤተመንግሥት የፒኮክ ቅርጽ ተቀመጠ ተብሎ ጩኸት መፍጠር ምን የሚሉት የፖለቲካ አጀንዳ ነው? ምርጫ ካልተካሄደ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ በአቋራጭ ለሥልጣን መንጠራራትስ ምን ዓይነት ህሊና ቢስነት ነወ።በአጠቃላይ በመንግሥት ጥረትና በፈጣሪ እርዳታ ኮሮና እስካሁን ብዙም ጉዳት ባለማድረሱ ከተደበቁበት ወጥተው የተለመደውን የፖለቲካ ጩኸታቸውን የጀመሩት እነዚህ ኃይሎች ተግባር የሚያስተዛዝብ ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝንም ጭምር ነውና ኧረ ጎበዝ እናስብ!!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 30/2012
ውቤ ከልደታ
ኮሮናን የማይደፍሩት የፖለቲካ አርበኞች