በልጅነታቸው ወደአዲስ አበባ መጥተው ቢማሩም ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ግን የተወለዱባትን መንደር እና ቤተሰቦቻቸውን መጎብኘት ግን ይወዳሉ። በማህበራዊ አገልግሎት መሳተፍም ዝንባሌያቸው ነው። እናም በተወለዱበት አካባቢ መሬት ጭምር ገዝተው ትምህርት ቤት አሰርተዋል። ከስፖርት ጋር በተያያዘው አምራች ዘርፋቸው አማካኝነት ደግሞ አንቱታን ያተረፉ ባለሀብት መሆን ችለዋል።
የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ ድጋፍ በማድረግ በየአካባቢው ወጣቶች ትርፍ ጊዜያቸውን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያሳልፉ የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል። ሃቄ ስፖርት የሚለው ስም በተለይ የስፖርት አልባሳት እና ምርቶች መገኛ በመሆኑ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች ዘንድ ታዋቂ ነው።
የዚህ ስፖርት ምርቶች አቅራቢ ድርጅት ደግሞ የዛሬው እንግዳችን አቶ ብርሃኑ ንብረት ናቸው። ባለታሪካችን አቶ ብርሃኑ ሃቄ ይባላሉ። የሃቄ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ ድርጅት ባለቤት ናቸው። በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በምትገኘው አንደቡየ መድኃኔዓለም በተሰኘች ስፍራ በ1942 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት የመጀመሪያዋ ቀን ላይ ነው የተወለዱት። ዘጠኝ ልጆች ባሉበት ቤተሰብ የተገኙት አቶ ብርሃኑ ለቤተሰባቸው ሁለተኛ ልጅ ናቸው።
በልጅነታቸው ከብት በማገድ ቤተሰባቸውን ያገለግሉ እንደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩ አጎታቸው ጋር ሄደው እየሰሩ ለመማር የሚያስችላቸውን ዕድል አገኙ። እናም ገና የ14 ዓመት ዕድሜ ላይ እያሉ አዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ አጎታቸው ጋር መጡ።
መርካቶ ላይ ቀን ቀን ጋዜጣ እያዞሩ በመሸጥ ምሽት ላይ ደግሞ ፒያሳ ካቴድራል ትምህርት ቤት የቀለም ትምህርታቸውን እንደጀመሩ ያስታውሳሉ። በወቅቱ ታዲያ ጋዜጣ አዙረው በቀን ስልሳ ሳንቲም ትርፍ ያገኙ እንደነበር አይዘነጉትም። ከጋዜጣው በተጨማሪ ሎተሪም በማዞር ሰርተዋል።
በመቀጠልም መጽሐፍት እያዞሩ በመሸጥ በወጣትነታቸው የንግድ ሕይወትን ምንነት ማጣጣም ችለዋል። እንዲህ እንዲህ እያሉ ቀን መርካቶ እና አካባቢዋ ላይ ተሯሩጠው እየሰሩ ማታ እየተማሩ ሰባት ዓመታት አለፉ። መርካቶ ገበያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የጨርቃጨርቅ ነጋዴ ታዲያ ታዳጊውን ብርሃኑን ቀጠሩት። እናም ታታሪው ወጣት የመንገድ ላይ ሥራው ትቶ በሱቅ ንግድ ሠራተኝነት በወር 50 ብር እየተከፈለው ንግዱን ማቀላጠፉን ተያያዘው።
የተለያዩ በቦንዳ የታሰሩ አልባሳትን የሱቁ ባለቤት ገዝቶ ሲመጣ ብላቴናው ብርሃኑ ደግሞ ለነጋዴዎች በመሸጥ ሥራውን በትጋት ይወጣል። በዚህ ዓይነት ሥራ ስምንት ዓመታትን ሲቆይ ወጣቱ ብርሃኑ የግል ሥራውን ለመጀመር ልቡ ተነሳስቷል፡ ፡ የልቡን በልቡ በማድረግም ከሚያገኛት ላይ እየቆጠበ ገንዘብ ያጠራቅምም ነበር።
10 እና 20 ብሎ የጀመራት ቁጠባም ጥቂት ሺህ ብሮችን ስታስገኝለት አንድ አሮጌ የሹራብ መስሪያ ማሽን ገዝቶ የእራሱን ሥራ ለመጀመር ቆርጦ ተነሳ። መርካቶ ሲኒማ ራስ አካባቢም በ1965 ዓ.ም በ200 ብር አንዲት የንግድ ሱቅ ተከራይቶ የሹራብ አልባሳት ምርት ሥራን አሀዱ ብሎ ጀመረ።
ገበያው ሞቅ እያለ ሲመጣም አንድ ተጨማሪ የሹራብ መስሪያ ማሽን ተከራይቶ ሥራውን ማጧጧፍ ቀጠለ፡፡ አንድ ሁለት እያለም በአቶ ብርሃኑ ሹራብ ማምረቻ ውስጥ ከአስር በላይ ሠራተኞች ተቀጠሩ። በወቅቱም ወጣቱ ብርሃኑም በከተማዋ ውስጥ በሹራብ ምርቶች ታዋቂ ነጋዴ መሆን ችሎ ነበር። ገቢው ሲጠናከር እና ሥራው ሲደራጅ ግን በ1973 ዓ.ም ያልታሰበው ነገር ተከሰተ። በሲኒማ ራስ አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት የአቶ ብርሃኑ ሙሉ ማምረቻ ሱቃቸው ወደመ። ማሽኖች፣ የሹራብ መስሪያ ክሮች እና የተዘጋጁ ልብሶችም ጭምር በዚያ ክፉ ቀን የእሳት እራት ሆኑ። ይህ ጊዜ ለአቶ ብርሃኑ ፈታኙ ወቅት ነበር፡፡
በመሆኑም ባዶ ሱቅ ውስጥ እንደአዲስ ለመጀመር ተገደዱ። በጊዜው ለሠራተኛ እንኳን የሚከፍሉት ገንዘብ አጥተው እንደነበርም አይዘነጉትም። ተስፋ መቁረጥ እና እራስን መጣል ምርጫው ያላደረጉት የንግድ ሰው ግን ዳግም በአዲስ መንፈስ ለሥራ መነሳቱን መረጡ። መንግሥትም ጉዳታቸውን አይቶ የመስሪያ ሱቅ እዚያው አካባቢ አመቻቸላቸው። እርሳቸውም ማሽን ያላቸውን አምራቾች ሱቃቸው ውስጥ እንዲሰሩ በማድረግ የአልባሳት ሥራውን ዳግም «ሀ» ብለው አስጀመሩ።
በአዲስ መልክ የጀመሩት ምርት ደግሞ የስፖርት ቁምጣ አዘጋጅቶ ለንግድ ማቅረብ ነው። በዚህ ዘርፍ ጥቂት እንደተንቀሳቀሱ ጥሩ ገበያን ማግኘትም ቻሉ። የተለያዩ የስፖርት አልባሳትን በማዘጋጀትም ዳግም ንግዳቸውን ማደራጀት በመቻላቸው አዳዲስ ማሽኖችን ገዝተው ሥራቸውን አጠናከሩ። ለተለያዩ የሀገር ውስጥ የስፖርት ቡድኖች የሚሆኑ ማልያ እና የተለያዩ የስፖርት አልባሳትን በማዘጋጀት ሃቄ ስፖርት የተሰኘውን ድርጅታቸውን በሚገባ አስተዋወቁ። በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚዘጋጁ ውድድሮች ላይ የቆዳ ኳስ ምርቶችን በማዘጋጀትም የማቅረቡንም ሥራ ተያያዙት። በወቅቱ ታዲያ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንዳልነበረ ያስታውሳሉ።
በተለይ የቆዳ ኳስ ስፌቶችን በሚያዘጋጁበት ወቅት በተደጋጋሚ ጊዜ እጃቸው ተቆራርጦ ብዙ ደም ጊዜ ይፈሳቸው ነበር። ይሁንና ያሰቡትን ከግብ ለማድረስ ጽኑ ፍላጎት ነበራቸውና ጥቂት ሲሻላቸው ወደሥራቸው ተመልሰው ምርቱን ለገበያ ያቀርቡ እንደነበር የኋሊት ተጉዘው ያስታውሱታል። በአንድ ወቅት ግን በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ከነበሩት መንግሥቱ ኃይለማርያም ጋር የሚገናኙበት ዕድል ተፈጠረ።
በአዲስ አበባ ከተማ ኤግዚቢሽን ሲካሄድ አቶ ብርሃኑ የመረብ ኳስ እና የእግር ኳስ አልባሳት እና የኳስ ምርቶቻቸውን ይዘው ቀረቡ። በወቅቱ ደግሞ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ምርቶችን ሲጎበኙ የስፖርት ምርቶቹንም ይመለከታሉ። አቶ ብርሃኑንም እየተመለከቱ ጥሩ ሥራ እንደሆነ በመግለጽ «ምንድን ነው በሥራህ ላይ ያለብህ ችግር» የሚል ጥያቄ አቀረቡ። አቶ ብርሃኑም የማምረቻ ቦታ ችግር እንዳለባቸው በመናገራቸው በአፋጣኝ ንፋስ ስልክ አካባቢ የመስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ተወሰነ።
አቶ ብርሃኑ ከሲኒማ ራስ በተጨማሪ ማምረቻ ቦታ በማግኘታቸው፤ ንፋስ ስልክ አካባቢ ሰፋ ያለ ግንባታ አከናወኑ። እናም የቆዳ ኳሶችን፣ የስፖርት ሜዳ ብረቶችን፣ የሲልክ ስክሪን ህትመት እና የስፖርት ትጥቅ ማምረቻ ጋርመንት ከፍተው መስራት ጀመሩ። ከቀን ወደቀን እድገት እያሳየ የመጣው የስፖርት አልባሳት ሥራቸውም በመላ ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ የሃቄ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝን ስምና ዝና ከፍ አደረጉት።
የስፖርት ትጥቅ አምራቹ ነጋዴ ታዲያ በተለያዩ የስፖርት እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ ልምድ አላቸው። በተለይ በብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ከ10 ዓመታት በላይ በሥራ አስፈጻሚነት አገልግለዋል። የኤድመንተኑ የአትሌቲክስ ዓለም ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያን ቡድን መርተው የሄዱበት ጊዜም አይረሳቸውም። ከስፖርቱ ባለፈም በልማት ሥራዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉት ነጋዴ በተወለዱበት አካባቢ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብተዋል። በገጠር መንደሯ በልጅነታቸው የቀለም ትምህርት በማጣት የሚቸገሩ ሕፃናት የመማሪያ ደብተር እና እስኪርቢቶዎች ድጋፍ በማድረግ በርካቶች ወደአስኳላ እንዲያቀኑ የማስተባበር ሥራም ይሰራሉ። «ከበጎ አድራጎቱ ጎን ለጎን ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት የበኩሌን ለማበርከት ሁሌም ፍላጎቴ ነው» የሚሉት አቶ ብርሃኑ በየዓመቱ ለስፖርታዊ ውድድሮች በድርጅታቸው ስም የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ይሳተፋሉ።
የእርሳቸው ምርቶች ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቡድን ድረስ ያልገቡበት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይሁንና ምርቶቻቸው በዋናነት በትላልቅ ጨረታዎች እና የመንግሥት እንዲሁም የውጭ ድርጅቶችን አቅርቦት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ይናገራሉ። በየጊዜው ምርታቸውን ለማሻሻል ጥረት የሚያደርጉት አቶ ብርሃኑ ፍላጎታቸው በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የስፖርት ትጥቆችን እና ቁሳቁሶችን በብዛትና በጥራት በማቅረብ በውጭ ምንዛሬ የሚገባውን የውጭ ሀገራት ምርት ማስቀረት መሆኑን ይናገራሉ።
ለዚህም በድርጅታቸው ላይ ማስፋፊያ በማድረግ ጥራት ያላቸው የስፖርት አልባሳት ምርቶች ማዘጋጀት እንደጀመሩ እና በጥራት ጉዳይ እንደማይታሙ ያስረዳሉ። አሁን ላይ ሃቄ ስፖርት ከአዲስ አበባ ሁለት መሸጫ ሱቆች እና አንድ ማምረቻ ቦታ በተጨማሪ ሐዋሳ እና አቶ ብርሃኑ ሃቄ ሻሸመኔ እንዲሁም አዳማ ከተሞች ላይ ሱቆችን ከፍቶ እየሰራ ይገኛል። በድርጅታቸው ስር 140 ሠራተኞች ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ። ይሁንና የሥራ መደቡ እስከ 156 ሰው መቅጠር የሚችል አቅም ስላለው ተጨማሪ ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉ ያስረዳሉ።
በቀጣይ ደግሞ ተጨማሪ ማስፋፊያዎችን አድርገው ሥራቸውን ለማስፋት እና ምርቶቻቸውን በመላ ኢትዮጵያ ለማዳረስ ውጥን አላቸው። እንደ እርሳቸው በአሁኑ ወቅት የቻይና ምርቶች ገበያውን ተቆጣጥረውታል፡፡ በሀገር ውስጥ ጥራት ባላቸው ምርቶች የስፖርት እንቅሴቃዎችን ማድረግ ቢቻል ለሀገርም ኢኮኖሚ ጥቅም አለው። በመሆኑም የሀገር ውስጥ የስፖርት ትጥቆችን የመጠቀም ልምዱ ሊዳብር ይገባል የሚል እምነት አላቸው።
ለአራት አስርት ዓመታት የተጓዘው ድርጅታቸው ብዙ ውጣ ውረዶችን እና ፈተኛዎችን ቢያስተናግድም ነገ ግን ብሩህ መሆኑን እያሰቡ ለተሻለ ውጤት አልመው ከእንቅልፋቸው ሁሌም እንደሚነሱ አቶ ብርሃኑ ይናገራሉ። ለስፖርት ትጥቅ ምርት ብዙም ትኩረት በማይሰጥባቸው ጊዜያት እንኳን ጠንክረው በሥራ ማሳለፋቸውን በመግለጽ አሁን ላይ ድርጅታቸው የተመዘገበ 30 ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዳለው ይገልጻሉ።
ዘርፉም ለሀገር በርካታ ቢሊዮን ብሮችን ሊያስገኝ የሚችል በመሆኑ ጥሩ ድጋፍ ቢደረግለት ማደግ የሚችል ሙያ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ ብርሃኑ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በላይ በሥራ ቢያሳልፉም ደከመኝ ብለው ቤት አይቀመጡም። ይልቁንም ለሀገርም ሆነ ለእራሳቸው የሚበጅ የሥራ ሃሳብ ይዘው ድርጅታቸው ላይ ለውጥ ያመጣል የሚሉትን ሥራ ለመተግበር ቀንም ማታም ከመልፋት እንደማይቦዝኑ ይናገራሉ። ሥራ ማለት ለእርሳቸው ውጤት ያለው እና ለሌሎችም የሚተርፍ የሙያ መስክ ነው። በዚህ ረገድ ወጣቶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ለሀገርም ለወገንም የሚበጅ ትርፍ ማምጣት የሚችሉባቸው በርካታ ዕድሎች በመኖራቸው ጊዜያቸውን በአግባቡ ስለመጠቀም ሊያስቡ ይገባል የሚለው ደግሞ ምክራቸው ነው። ቸር እንሰንብት!!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 3/2012
ጌትነት ተስፋማርያም
«ሃቄ ስፖርት» የስፖርቱ ቤተሰብ ባለውለታ