የኮሮና ቫይረስ በመላው ዓለም የፍርሃትና የጭንቀት ምንጭ ከሆነ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ወራትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ በበሽታው ተይዘው በበሽታው ከመሰቃየት ባለፈ እየተሰቃዩ ያለበት ሁኔታ ላይ ናቸው፡፡ ችግሩን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ እስካሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ ለበሽታው መድሃኒትም ሆነ ክትባት ሊገኝለት እንደሚችል ተስፋ የመስጠት አመላካች ነገር አለመኖሩ ነው።
ከዚህ ይልቅ በሽታው አድማሱን በመላው ዓለም እያሰፋ ዘርፈ ብዙ በሆነ መልኩ መላውን ዓለም እየተፈታተነ መገኘቱ ነው። ችግሩ ደግሞ እንደኛ ባሉ ኢኮኖሚያዊ እና ሰብአዊ አቅማቸው በሽታውን ለመከላከል በራሱ ተግዳሮት ለሚሆንባቸው ሀገራት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የመሆኑ እውነታ ነው። እንደ አገር ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበርንበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመውጣት ያለንን አቅም አቀናጅተን መንቀሳቀስ በጀመርንበት ማግስት መከሰቱ ደግሞ እውነታውን ያከብደዋል።
መንግስት በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ ቫይረሱ ወደ ሀገር ውስጥ ቢገባ ሊደርስ የሚችለውን የከፋ አደጋ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። በአንድ በኩል በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን በህዝቡ ውስጥ ለማስረጽ የሚያስችሉ ሰፊ ስራዎች አከናውኗል፤ እያከናወነም ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ችግሩ ቢከሰት ሊመጣል የሚችለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት መታደግ የሚያስችሉ አቅሞችን ለመፍጠር ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።
አዋጁ ወረርሽኙን ለመከላከል ወሳኝ ነው! ለሰው ልጅ አራት መሠረታዊ ነገሮች ያስፈልጋሉ:: እነዚህም ምግብ፣ መጠለያ፣ አልባሳትና ውሃ ዋነኛ መሠረታዊዎች ናቸው:: ትምህርት፣ ስልክ፣ ሚዲያ፣ ጤና፣ ሥራ፣ ትራንስፖርት፣ ማብራት እና የመሳሰሉት ደግሞ ተጨማሪ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው:: ከተጨማሪ አስፈላጊዎች መካከል አንዱ የሆነው ትምህርት ብዙ ኩነቶችን ይዟል::
ትምህርት አንድ ሰው ከነበረበት የንቃተ-ህሊና ደረጃ የተሻለ ዜጋ እንዲሆን ይረዳዋል:: ከአላዋቂነት ወደ አዋቂነት ለመሸጋገርም ትምህርት ወሳኝ ነው:: የግልና አካባቢ ንፅህና፣ ማህበራዊ ግንኙነት፣ የሥራ ክህሎት፣ የአመጋገብ ሥርዓትና ግብይት በተሻለ መልኩ ለማከናወን ትምህርት ያስፈልጋል:: የሰው ልጆች በመደበኛና በኢ-መደበኛ መንገዶች ትምህርት ይቀስማሉ::
መደበኛ የትምህርት መቅሰሚያ መንገድ ተቋማዊ መሠረት ያለውና በህግና መመሪያ የሚተዳደር ነው:: ይህ መንገድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው:: ከጠቅላላ ትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት እስከ አንድ የትምህርት መስክ የሚገኝ የላቀ ዕውቀት ድረስ ይዘልቃል::
በኢ-መደበኛ መንገድ ተቋማዊ መሠረት የሌለውና በወጣ ህግና መመሪያ የማይተዳደር ነው:: ይሁን እንጂ ብዙ ዕውቀት የሚቀሰምበትና የትምህርት ማግኛ አንዱ መንገድ ነው:: በዕለት-ተዕለት ኑሮ ከራስና ከሌሎች ሰዎች የሚገኙ ተሞክሮዎችና ትምህርቶች በዚህ መንገድ ሥር ይካተታሉ:: በትምህርት ዕውቀት ይገኛል:: ዕውቀት ደግሞ በምድር ላይ በጥበብና ብልሃት ለመኖር ይረዳል:: ማንበብና መፃፍ ለሚችል ሰው ብዙ ዕውቀት ማግኛ መንገዶች አሉ:: የህትመትና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መንገዶች አሉ:: በማንበብ፣ በማዳመጥና በመመልከት ከእነዚህ የዕውቀት ማግኛ መንገዶች ዕውቀት መገብየት ይቻላል:: ማንበብ የተለያዩ የተፃፉ ምልክቶችን የመመልከትና ትርጓሜ የመስጠት ሂደት ነው:: ስናነብ አይኖቻችንን በመጠቀም የተፃፉ ምልክቶችን (ፊደሎችን፣ ሥርዓተ ነጥቦችንና በቃላት መካከል ያሉ ክፍተቶችን) ተመልክተን አዕምሮአችንን በመጠቀም እነዚህን ምልክቶች ወደ ቃላት፣ አረፍተ-ነገሮችና አንቀፆች በመለወጥ የሆነ ትርጉም እንዲሰጡን ያደርጋል::
ማንበብ በፀጥታና ድምፅ በሚሰማ መልኩ ሊከወን ይችላል:: ማንበብ ከአራቱ የቋንቋ ክህሎቶች ሦስተኛው ነው:: ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍ አራቱ ክህሎቶች ናቸው:: ማንበብ መረጃን የመቀበል ክህሎት ነው:: የላቀ የማንበብ ክህሎት የመናገር ክህሎትንይፈጥራል:: ማንበብ መረጃ የመስጠትና የመቀበል ምርታማ ክህሎት ነው:: ማንበብ በጥሞና ውስጥ በመሆን አንድ የተፃፈ መረጃ ወደ ውስጥ የማዋሃድ ክህሎት ነው:: አንብቦ አንድን ሀሳብ ለመረዳት በጥሞና ማንበብ ያስፈልጋል:: የአዕምሮ መረጋጋትና ጸጥ ያለ ስፍራ በጥሞና ለማንበብ ያስፈልጋሉ:: በተጨማሪም ለማንበብ የሚነበቡ የህትመትና የኢንተርኔት ፅሁፎች ያስፈልጋሉ::
አንባቢውም አዕምሮውን አረጋግቶ የሚነበብ ፅሁፍ አዘጋጅቶ ፀጥ ባለ ስፍራ ወደ ንባብ አለም ይነጉዳል:: በዚህም አንባቢና ተነባቢ በአንድ ስፍራ ተገናኙ ይባላል:: አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ-ዘመን እጅግ ብዙ የሚነበቡ የህትመትና የኢንተርኔት ፅሁፎች አሉ:: የአንባቢዎች ቁጥርም በዝቷል:: ምን እንኳን በብዛት የሚነበቡ ፅሁፎች ፋይዳነታቸው አጠያያቂ ቢሆንም የማንበብ ልምዱ አበረታች ነው::
ብዙ አንባቢዎችና ተነባቢዎች በበዙበት ዘመን ፋይዳ ያላቸው ፅሁፎች ብዙ ትኩረት አልተሰጣቸውም:: የጥላቻ፣ ወሲባዊ፣ የሃሰት፣ ዘረኝነት፣ የሴራና ክፉ ሃሳቦችን የያዙ ፅሁፎች ከሌሎች ሰፊ ፋይዳ ካላቸው ፅሁፎች የበለጠ በብዙ አንባቢዎች ተመራጭ እንደሆኑ የተለያዩ ጥናቶች/ፅሁፎች ይገልፃሉ::
አንድን ግለሰብ ከሌላ ግለሰብ፣ አንድን ቡድን ከሌላ ቡድን፣ አንድን ሀገር ከሌላ ሀገር እና አንድን አህጉር ከሌላ አህጉር የሚያጋጩ ፅሁፎች ከሚያፋቅሩ ፅሁፎች ይልቅ በሰፊው ተቀባይነት አላቸው:: የሃሰት ፅሁፎች ባደጉ ሀገራት ጭምር ሰፊ ተቀባይነት አላቸው:: ፅሁፎችን ተከትሎ የሚከሰቱ ቀውሶች ተጠያቂ አካል ማግኘት ደግሞ አይቻልም:: የሃሰት ፅሁፎች በሰፊው የሚገኙት ደግሞ የፀሃፊውን ማንነት ማወቅ በማይቻልበት መንገድ በኢንተርኔት ነው::
ኢንተርኔት በቀጥታ አፈላለግ መረጃን ከመረጃ ምንጭ ማግኘት የሚያስችል የዘመናችን ትልቁ ቴክኖሎጂ ነው:: በኢንተርኔት የትምህርት፣ የጤና፣ ማህበራዊ፣ ስፖርታዊ፣ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና የሥራ መረጃዎችን በቀጥታ በየጊዜው ከሚታደስ የመረጃ ምንጭ ይገኛል:: በዓለም-አቀፍ ደረጃ ለመረጃ ልውውጥ ሳንባ በመሆን ኢንተርኔት እያገለገለ ይገኛል:: የመረጃ ልውውጥን በሴከንዶች በማድረግ የልውውጥ ፍጥነትን በማሳደግ ኢንተርኔት የግዜ ብክነትን በመቀነስ የዘመኑ ልዩ ስጦታ ነው::
የህትመት ፅሁፎች በመፅሐፍ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔትና በተለያዩ መልኮች ሊቀርቡ ይችላሉ:: የተደራሽነትና የአንባቢያን ቁጥር ማነስ ችግር ሊገጥማቸው ቢችልም የህትመት ጽሁፎች በማንበብ ዕውቀት ለማግኘት ለሚሻ አንባቢ ትልቅ ጥቅም አላቸው::በሀገራችን ኢትዮጵያ የማንበብ ባህላችን ጥሩ የሚባል አይደለም:: ብዙ ሰዎች ከማንብብ ይልቅ አንድን ሀሳብ ከሰው መስማት ይመርጣሉ::
በማንበብ ከሚገኝ ሀሳብ ይልቅ በመስማት የሚገኝን ይመርጣሉ:: ሀሳብ አቅራቢው ግለሰብ የተሻለ የማንበብ ልምድ ከሌለው ፋይዳ ቢስ ሀሳብ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል:: አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሀሳብ ለማጋራት የተሻለ ግንዛቤ ወይም ዕውቀት ሊኖረው ያገባል:: ባለው የተሻለ ዕውቀት ለሌሎች ሰዎች ጠቃሚና አስተማሪ ሃሳቦችን ያጋራል:: የብዙ ሰዎችንም ግንዛቤ ያሳድጋል:: ንቃተህሊናው ያደገ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ሰፊ ርብርብ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል:: የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር ማንበብ ያስፈልጋል:: በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሰፊው ማንበብ የሰፊና ጠቅላላ ዕውቀት ባለቤት ያደርጋል:: ማህበራዊ፣ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ የጤና፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሙያዊ እና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዕውቀት ያለው ሰው ምክንያታዊ፣ ሚዛናዊና ብልህ ሰው ይሆናል:: ከተለያዩ ንባቦች የሚያገኛቸው ሀሳቦች አንድን ጉዳዩ በተለያዩ አቅጣጫዎች ስለሚያይ ፅንፈኛና ግትር አይሆንም::
ለምሳሌ፦ ማግኘት እንዳለ ማጣት፣ መስማማት እንዳለ መጋጨት፣ ማመን እንዳለ አለማመን፣ መጋባት እንዳለ መፋታት እና መኖር እንዳለ መሞትን ይረዳል:: አንባቢያን ሚዛናዊና ምክንያታዊ ናቸውና ስሜታዊ አይሆኑም:: አንድን ጉዳይ በብዙ አቅጣጫዎች የማየት አቅሙ ስላላቸውም በስሜት አይነዱም:: አንባቢያን የቀድሞውን የማወቅ፣ አሁን ላይ ያለውን የመረዳትና የወደፊት የሚሆነውን የመተንበይ አቅም አላቸው:: ከጊዜ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በመረዳታቸው ሰፊ የግንዛቤ አድማስ አላቸው::
አንባቢያን አንድን ጉዳይ አይተው እንዲሁ አያልፉም:: በአትኩሮ ያዩና ሁኔታውን በአዕምሯቸው አሰላስለው መሆን ያለበትን ጠቁመው ያልፋሉ:: አስተያየትም ይሰጣሉ:: አቅራቢያ ካሉ ሰዎች ጋር ይወያዩበታል:: አንዳንዴም ፅሁፎችን ያዘጋጃሉ:: ጠያቂና ሞጋች ናቸው:: ካልመረመሩ አንድን ሀሳብ በስሜት አይቀበሉም:: ስለአንድ ነገር በሰፊው ለማወቅ ለምን ይላሉ:: ማመን ሲኖርባቸው እንኳን ከብዙ የለምን ጥያቄዎች ቀጥሎ ነው::
እንግዲህ ከላይ መረዳት እንደምንችለው የተመ ጣጠነ ምግብ ለሰውነታችን እንደሚያስፈልግ ሁሉ የተመጣጠነ ንባብ ለአዕምሯችን ያስፈልጋል:: ማንበብ ዕውቀት በሰፊው ስለሚጨምር ሙሉ ሰው ያደርጋል:: ስለዚህ ጠቃሚ የሆኑ ፅሁፎችን አብዝቶ በማንበብ የላቀ ዕውቀት ያለው ሚዛናዊና ምክንያታዊ የሆነ ሰው መሆን ያስፈልጋል:: አበቃሁ::
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 1/2012
በላይ አበራ (አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ)
ለማወቅ ማንበብ እና በማንበብ ማወቅ፦ ማንበብና ማወቅ ምንና ምን?