አዲስ አበባ፡- የፍትህ ሥርዓቱን የሚያ ሻሽሉ እና የሚያዘምኑ አሠራሮችን እየዘረጋ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለጸ።
የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በተለመደው አካሄድ አገርን መገንባት፣ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ ሕገ-መንግሥታዊነት እንዲጎለብት ማድረግ አያስኬድም። የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥም ያስቸግራል። በመሆኑም ዘመኑ የደረሰበትን ደረጃ ያገናዘበ አሠራር ለመተግበር የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በተለመደው አሠራርና ልማዳቸው ከቀጠሉ ችግሮቻቸውን ሳይፈቱ ኅብረተሰቡንም ማስደሰት ሳይችሉ ይቀጥላሉ ያሉት አቶ ሰለሞን፤ በመሆኑም የዳኝነት ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዎችን በመ ተግበር ከዘመኑ ጋር ለመራመድ ጥረት እየተ ደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለዚህም የሕግ ማዕቀፎችን በመፈተሽ አዳዲስ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማካተት ማስፈለጉን ነው የጠቆሙት። በጀት፣ የማስቻያ ቦታዎች እጥረት፣ በቂ ሕንፃዎች አለመኖርና ምቹ የመስሪያ ቦታዎች አለመገኘት ተግዳሮት ሆነውብናል ያሉት አቶ ሰለሞን፤ ተግዳሮቶችን ሊፈቱ የሚችሉ ሁለት ረቂቅ ሕጎች ተዘጋጅቶ ለምክር ቤት መላካቸውን ተናግረዋል።
ለምክር ቤቱ የቀረቡት ሁለት አዋጆች የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ናቸው። ለምክር ቤቱ አባሪ ተደርጎ የቀረበው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቁ እንደሚያስረዳው፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በበጀት ምደባና አስተዳደር ፤ በሰው ሀብት ቅጥርና ምደባ እንዲሁም በአስተዳደር ራሳቸውን ችለው የሚሰሩበትን ሥርዓት መዘርጋት ማስፈለጉን ጠቁሟል።
የዳኝነት ነፃነት ከሚረጋገጥባቸው የበጀት ዝግጅት፣ በጀት የሚፀድቅበት ሂደትና አፈፃፀም እንደመሆኑ፤ የበጀት አሠራሩ የፍርድ ቤቶችን የሥራ አፈፃፀም በማያውክና አስፈላጊው በጀትና የሠራተኞች አስተዳደር ሥርዓት የሚዘረጋ መሆኑን አስረድተዋል።
የፍርድ ቤት መር አስማሚነትና የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር በአዋጁ እንዲካተቱ መደረ ጉን ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት መደበኛውን የክርክር ሂደት ሳይከተል በማስማማት ሙያ በተካኑ ባለሙያዎች /ኤክስፐርቶች/ እገዛ ጉዳዮች በአጭሩ እልባት እንዲያገኝ የሚደረግበት ሥርዓት እንደተካተተም ምክትል ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡላቸ ውን ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ወይም የሚጠናቀቁበትን የጊዜ ሰሌዳ ገደብ ባለማስ ቀመጣቸው አንድ ጉዳይ መች ተጀምሮ መች እንደሚያልቅ ግልጽ የጊዜ መጠን እንደሌለው ምክትል ፕሬዚዳንቱ አውስተው፣ የፍርድ ቤት ጉዳይ ማለቂያ ጊዜ ተገማች ያልሆነና ለመቆጣጠርም አስቸጋሪ እንደነበረም አስታውሰዋል። አዲስ በሚዘረጋው አሠራርም አንድ የፍርድ ሂደት መቼ ተጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ በግልጽ እንደሚታወቅ አመልክተዋል።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓቱ የተሳለጠና ጥራቱ የሚረጋገጥበት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችል አንቀጽ መካተቱም ተጠቁሟል። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በማንኛውም የፍርድ ቤት ደረጃ የሚቀርቡ የፍትሃብሔር ወይም የወንጀል ጉዳይ ክርክሮች አዳዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዲጂታል ወይም አውቶሜትድ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ሥርዓት ሊዘረጉ እንደሚችሉ በረቂቅ አዋጁ መካተቱን አቶ ሰለሞን አመልክተዋል።
ባለጉዳዮች ዶሴ ተሸክመው ፍርድ ቤት ከመምጣት ይልቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የክስ ዝርዝርም ይሁን ማንኛውም አቤቱታ በዲጂታል ስቶር ወይም በሶፍት ኮፒ ለፍርድ ቤቱ በማስገባት በዘመነ መንገድ እንዲስተናገዱ ለማስቻል እንደሚያግዝም ጠቁመዋል። የዳኞች ስነምግባር ኮድ ኦፍ ኮንዳክት እንደ አዲስ መጠናቱንም ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን ጥር 13/2012
ዘላለም ግዛው
nazilli apart otel
bursa evden eve taşımacılık |
ремонт телефонов москва дешево
ankara diş kliniği
https://avbusramizen.com/bursa-bosanma-avukati-2/
bursa görüntülü diafon
seo hizmeti
aydın çıkışlı turlar
ankara tercüme bürosu
aydın çıkışlı turlar
denizli çıkışlı turlar
aydın çıkışlı turlar
kristalize su yalıtımı |
Профессиональный сервисный центр по ремонту бытовой техники с выездом на дом.
Мы предлагаем: сервис центры бытовой техники москва
Наши мастера оперативно устранят неисправности вашего устройства в сервисе или с выездом на дом!
nazilli apart otel en uygun fiyatlarla konaklama yapabilirsiniz.
başkent namlı inşaat
Профессиональный сервисный центр по ремонту компьютеров и ноутбуков в Москве.
Мы предлагаем: срочный ремонт макбука в москве
Наши мастера оперативно устранят неисправности вашего устройства в сервисе или с выездом на дом!
cepte haber
ankara haberler
ankara olay haber
izmir gündem haber
ankara güncel haberler
ankara haberler
bursa hurdacıbursa halis hurda alımı
kars kaşar peyniri