እአአ ህዳር 11 ቀን 2019 ዘሄግ ለሚገኘው ዓለምአቀፉ የጦር ፍርድቤት ጋምቢያ አንድ ወቀሳ አቅርባ ነበር። ይህ ወቀሳ ደግሞ በማይናማር እየተፈፀመ ስላለው ሰብኣዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ጋምቢያ ያቀረበችው ቅሬታ እንደሚያመለክተው በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ኢሰብኣዊ ድርጊቶች እአአ በ1948 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተደረሰውን ዓለምአቀፍ ስምምነት የጣሰ ነው፡፡
የአልጀዚራ ዘገባ እንዳመለከተው የጋምቢያ ፍትህ ሚኒስትር አቡበከር ታምቡዶ በሄግ በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ያቀረቡት ቅሬታ ማይንማር በገዛ ወገኖቿ ላይ ያደረገችውን የግድያ እርምጃ እንድታምን ማድረግ ነው፡፡ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት “የዘር ማጥፋት ዘመቻ በገዛ ዓይናችን እያየን ምንም ማድረግ ካልቻልን ለትውልዳችን አሳፋሪ ነው›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
“ጉዳዩን ለማጣራት ትንሿ የምዕራብ አፍሪካ አገር አስፈላጊ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥታ የሰብአዊ መብትን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስፋፋት ረገድ ግንባር ቀደም የመሆን አቅምን ማሳየት ችላለች” ሲልም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ለዚህም የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢስታቱ ቱራይ አገሪቱን ሲገልጿት “በአህጉሪቱ እና ከዚያ በላይ ባሉት የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ላይ ትልቅ ድምጽ ያላት ትንሽ ሀገር” ብለዋታል፡፡
በርግጥ ጋምቢያ በሰብኣዊ መብት አያያዝ ረገድ ከአፍሪካ በመልካምነት ከሚነሱ አገራት ግንባር ቀደም አገር መሆኗን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጭምር ምስክርነት የሰጣት አገር ናት፡፡
ከዚህ በፊት አንዳንድ የአፍሪካ መንግስታት በዓለም ዙሪያ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ቢመለከቱም ማይናማር በሮሂንግያ ህዝብ ላይ እየፈፀመች ያለውን የሚሰነዝሩትን ጥቃት በተመለከተ ግን ፈራ ተባ በሚል ስሜት እንደሄዱበት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ. 2007 በሮሂንግያ ጨምሮ በአገሪቱ በሚገኙት አናሳ ቡድኖች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በደንብ የምታውቅ ቢሆንም የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በዜጎቹ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እንዲያቆም ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ደቡብ አፍሪካ እአአ 2018 ላይ በተደረገ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በማይናማር የሚደረገው ሰብዓዊ መብት ጥሰት መቆም እንዳለበት ማሳሰቡ አይዘነጋም፡፡
በእርግጥ በማይናማር የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ ጥያቄ ማንሳት ባይቻልም ጋምቢያ በአፍሪካ የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ጠንካራ አመራርን ማሳየት ግዴታ ነበረባት፡፡ የጋምቢያ አስተዳደር የዴሞክራሲ ተቋማትን፣ መልካም አስተዳደርን እና ሰብአዊ መብቶችን ለማስፋፋት ቃል ቢገቡም የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ አገራት በተለይም የአፍሪካ ዋና ኃያላን አገራት በአጠቃላይ በአህጉሪቱ የሰብአዊ መብትን ለማስጠበቅ እየረዱ አይደለም፡፡ አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደዘገበው ከሆነ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ከአፍሪካ የሰብአዊና የሕዝቦች መብት (ከአፍሪካ ኮሚሽን)፣ ከአፍሪካ ሕፃናት መብቶች ኮሚቴ እና ከአፍሪካ ፍርድ ቤት ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ በዚህም የአፍሪካ የሰብአዊ መብት አስጠባቂ አካላት በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አሊ የ 2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ሲያሸንፉ እና ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ሩዋንዳን መልሰው እየገነቡበት ያለው እንቅስቃሴ ሰፋ ያለ ውዳሴ ቢያስገኝም አፍሪካ እያደገ በሚገኝ ሀይለኛ በሆነ ጨቋኝ መሪዎች እጅ ላይ እንደምትወድቅ ማሳዎች መኖራቸውን አልጀዚራ በዘገባው ጠቁሟል፡፡
ሰላማዊ የሆነ ስብሰባን እና የመደራጀት መብትን አስመልክቶ ልዩ ዘጋቢ የሆኑት ክሌመንት ንያሌትሶስሲ ቮውሌ እ.ኤ.አ. 2019 በጥር ወር በዚምባብዌ በተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ፖሊስ እና ወታደራዊው ኃይል ከመጠን በላይ ሀይል በመጠቀማቸው 17 የተቃውሞ ሰልፈኞች መገደላቸውን አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ክሌመንት ንያሌትሶስሲ ቮውሌ በግብፅ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ህገ-ወጥነት፣ የዘፈቀደ ግድያዎች እና አላግባብ እስር ላይ ልዩ ዘገባ ሰርተዋል፡፡ የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ሞት “በመንግስት የተደረገ ግድያ” እንደሆነ በመግለጽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቀጣይ ሊገደሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በግብፅ ያሉ ሌሎች እስረኞችም ለሞት የተጋለጡ ሊሆኑ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡
በኡጋንዳ የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሰቪኒ አስተዳደር ጋዜጠኞችን፣ ተማሪ የተቃውሞ ሰልፈኞችን እና የተቃዋሚ መሪውን ኪዛ ቤሲጊን በማሰቃየት እንዲሁም ታዋቂ ዘፋኝና ፖለቲከኛ የሆነውን ቦቢ ዊይን “የሀገሪቱ ብልጽግና ጠላት” የሚል ስያሜ እንዲሰጠው አድርገዋል። በቱኒዚያ ውስጥ የመናገርን ነፃነት በሚገድቡ ህጎች ጦማሪያን በማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎቻቸው ክስ ተመስርቶባቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በታንዛኒያ የፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሉ መንግሥት የሚዲያ መብቶችን፣ ሰብአዊ መብቶችን እና ዴሞክራሲን በመግታት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአንግሎፍሬንች ክልል ውስጥ አመፅ የተቀሰቀሰበት የካሜሩን የመንግስት ሃይሎች ዜጎችን መግደል፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ማቃጠል እና አሰቃቂ ቅጣቶችን በእስርቤቶች እየፈፀመ ይገኛል፡፡
የከፋ የፖለቲካ አመለካከቶች፣ ግድየለሽነት፣ አመፅ እና አለመቻቻል በመንሰራፋቱ ለዜጎች በቂ ጥበቃ አለመስጠት በአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የተለመዱ ናቸው፡፡ የአፍሪካ የአቻ ግምገማ ሜካኒዝም (ኤፒ አር ኤም) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ኤዲ ማሎካ በአፍሪካ አስተዳደር የበላይነት ሥነ-ሕንፃ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፤ በአፍሪካ የተፈጠሩ አለመግባባቶች እና በከባድ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ሊፈፀሙ የሚችሉ ኢሰብኣዊ ድርጊቶችን በተመለከተ ጭንቀታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአስተዳደር ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አህጉሪቱ ጠንካራ እና ግልፅ አቋም መውሰድ አለባት ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ የአስተዳደር ጉዳዮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሱ መምጣታቸው በተለያዩ መንገዶች እየተረጋገጡ ይገኛሉ፡፡
ማይናማር ሮሂንግያኖች ላይ ያደረገችውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ድምጽ ከሰጠ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ውሳኔው በአገራት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ አዲስ የፀሐይ ንጋት ማሳያ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የመቃወም መሰረታዊ መርሆዎች መሆኑን ገልፃለች፡፡ ሆኖም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በርካታ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሲከሰት እና በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና በግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ ኤል-ሲሲ አስተዳደር ጋዜጠኞችን፣ ተሟጋቾችን፣ ፖለቲከኞችን እና የተቃውሞ ሰልፎችን በማሰቃየት ላይ በነበሩ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ችላ ተብሏል፡፡
አዲስ ዘመን ኅዳር 22/2012
መርድ ክፍሉ