የሰው ልጅ የስልጣኔው ደረጃ ከፍታ ላይ ለመድረስ ምርምርና ፈጠራ መነiው፤ ሳይንስ ደግሞ መንገዱ ነው። ህይወትን ለማቅለል፣ የአ‘‘ር ስልትን ለመቀየር፣ ጊዜን በተiለ ለማዘመን ምርምርና ፈጠራ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። በምርምር ችግሮች ሲፈቱ፤ በፈጠራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሲፈልቁ ተመልክተናል። እኛ የቴክኖሎጂዎቹ ተጠቃሚና ተግባሪዎች ሆነን ዛሬ ላይ ተገኝተናል።
አሁን ላይ በሰከንድና በሰከንድ ሽርፍራፊዎች በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር ካለ ሰው ጋር ሀሳብ መለዋወጥ ቀሏል። በሰዓታት ጊዜ ውስጥ የፈለጉበት ደርሶ ያሻን ፈፅሞ መመለስ ተችሏል። መገናኛው የፈጠራው ሙያ ፈጠራ፤ መጓጓዣው ያስገኘው ውጤት ምርምር ነው። ዛሬ ላይ ያለተክኖሎጂያዊ ቁሳቁስ ርዳታ አንድ ነገር በቀላሉ ለመከወን ያዳግታል። ሳይንሳዊ የምርምር ስራዎች ያስገኙልንን የፈጠራ ውጤቶች መገልገላችን ለተግባራችን ስኬት፤ ለሙያችን ደግሞ እገዛ ፈጥሮልናል።
የፈጠራ ስራዎች የማህበረሰቡን ችግር በመቅረፍና አዳዲስ መፍትሄ በመጠቆም ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው። በሀገራችን የምርምርና የፈጠራ ባለሙያዎች እየተበራከቱና አዳዲስ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን እያበረከቱልን ይገኛሉ። በፈጠራ ስራቸው ነገ ለሀገር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግርን መቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ተግባራዊ የማድረግ ስራ ላይ ይገኛሉ።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ የእደገት መሰረት የስልጣኔ መንገድ ነውና ሀገራት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰሩበት ይገኛሉ። በኢትዮጵያም ዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ነው። በተሰጠው ትኩረት ውጤት ከማግኘቱ ጋር ተያይዞ በግል ጥረትና ብርቱ ትግል የምርምርና የፈጠራ ስራዎች በመስራት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችንና ስራቸውን በዚህ አምዳችን ማቅረባችን ይታወሳል።
ዛሬም በፈጠራ ስራቸው ስኬታማ የሆኑ አንድ መምህር ስለ
ፈጠራቸው ምንነት፤ የፈጠራ ስራው አሁን ያለበት ደረጃና በፈጠራ ስራቸው ያገኙትን ውጤት፤ እንዲሁም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን አቅርበን የሰጡንን ምላሽ በዚህ መልክ አቅርበንላችኋል።
መምህር አለሙ ይባላሉ በአማራ ብሄራዊ ክልል ደሴ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት መምህርና የፈጠራ ባለሙያ ናቸው። አቶ አለሙ ለተማሪዎቻቸው በቀለም ትምህርት ያላቸውን እውቀት ከማስቀሰም ባሻገር በፈጠራ ሙያ ያላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ ከፍተኛ እገዛና ድጋፍ በማድረግ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። መምህር አለሙ በፈጠራ ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ ተወዳድረው አሸንፈዋል።
መምህሩ፤ ካዩትና ከተመለከቱት አካባቢያዊ ችግር በመነሳት የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች ሰርተዋል። በምርምር ሙያ የተለየ ስልጠና ሳያገኙና የተማሩበትም የትምህርት መስክ ማህበራዊ ሳይንስ መሆኑ ሳያግዳቸው በሳይንሱ ዘርፍ የተለየ ክህሎትና ተደጋጋሚ ጥረት የሚያስፈልገው የፈጠራ ስራ ለመስራት ችለዋል።
የፈጠራ ባለሙያው ለምርምርና ፈጠራ ስራ ምቹ ሁኔታና አጋጣሚ በሌለበት አካባቢ እንደመኖራቸው ወደ ምርምር ስራ ገብቶ ለመስራት ብርቱ ጥረት ማድረግ ነበረባቸው። በተደጋጋሚ ሙከራ በዘርፉ ያለውን ፈተና ተቋቁሞ የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የፈጠራና የምርምር ስራዎች በመስራት ተግባራዊ አድርገዋል። አቶ አለሙ በምርምርና ፈጠራ ስራዎቻቸው የተመለከቱትን አዲስ ነገር መልሶ በመስራት፤ አዳዲስ ቁሶችን በመፍጠርና በተደጋጋሚ በማሻሻል ያላቸውን ጊዜ ያሳልፋሉ።
መምህርና የፈጠራ ባለሙያ የሆኑት አቶ አለሙ፤ የባለ ብዙ ፈጠራ ባለቤት የሆኑበት ምክንያት ጠንካራና ብርቱ ሰራተኝነታቸውና ለሙያው ያላቸው ፍቅር መሆኑ ልብ ይሏል። ይህ ፍቅር ውጤት አስገኘ፤ ይህ ጥረት ፍሬ አፈራና የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች ባለቤት መሆን አስቻላቸው። ቁጥራቸው አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችን በመሰብሰብ የምርምርና የፈጠራ ስራ እንዲሰሩ በመርዳት ላይም ይገኛሉ።
የፈጠራ ስራው ምንነት
የፈጠራ ባለሙያው መምህር አለሙ እስካሁን የሰሩዋቸው የፈጠራ ስራዎች በርካታ ሲሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ ሆነው እውቅና ያገኙባቸው የኤፍ ኤም ማሰራጫ፣ እስካባተር መኪና ሞዴል፣ ገልባጫ መኪና፤ እንጨት መቁረጫ ግሬደር፤ ቀላል ሞተር፤ በውሀ ሀይል የሚሰራ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የመምህሩን የፈጠራ ስራዎች ለማሳየት እነዚህን በዋናነት ጠቀስን እንጂ፤ በሌሎች የፈጠራ ባለሙያዎች የተሰሩትን ማሻሻልና በአዲስ መልክ መስራት የተካኑበት ሙያ ነው። በዚህ ረገድ በየጊዜው ማሻሻያዎች እንደሚያደርጉም ይገልፃሉ። በፈጠራ ስራ መስክ ወደፊት ብዙ ስራዎችን ለመስራት እቅድ መያዛቸውና አሁንም በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ይገልፃሉ።
ለፈጠራ ስራው ያነሳሳቸው ምክንያት፡-
የምርምርና የፈጠራ ስራ መነሻው ያጋጠመን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ሙከራ፤ አሊያም ያለውን ለማሻሻልና የተሻለ ጥቅም እና አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚከወን ተግባር ነው። በተለይም፤ አንድ ምርምር አድርጎ በማህበረሰብ የሚከሰት ችግር መፍታትና መፍትሄ ማስቀመጥ ፍላጎት መኖር ለምርምር ስራው ጋባዥ ምክንያት ነው። የመምህር አለሙ ወደ ምርምር ስራ መግባት ምክንያትም ከዚህ የተለየ አይደለም።
ወደ ምርምር ስራ ከመግባታቸው በፊት በጋዜጠኞች ማህበር ታቅፍው የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያርጉም ለስኬት በር ይሆነኛል ያሉት ተግባር ውጤት ያጡበታል። ሙከራቸውን ሳያቋርጡ እዚያው አካባቢ ባለ የደራሲያን ማህበር ቢሳተፉም በመስኩ ተፅዕኖ የመፍጠር ህልማቸው አልሰምር ይላቸዋል። ጥረታቸውን ቀጥለው በምርምርና ፈጠራ መስክ ሙከራዎችን ለማድረግ ቆረጡ። አሁን ፍላታቸው ሰምሮ፤ የሰሩት ስራ ውጤታማ ሆኖ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ ለመሆን በቁ። ለዚያውም ከሶስት ያለነሰ ጊዜ አሸንፈው የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኑ።
በፈጠራ ስራው የተገኘ እውቅናና ሽልማት
መምህሩና የፈጠራ ባለሙያው አቶ አለሙ በምርምርና ፈጠራ ስራቸው ከተለያዩ አካላትና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት፣ ከወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት፣ ከዞን፣ በክልል ደረጃ፣ የምርምርና የፈጠራ ስራ ከሚሰሩ ተቋማት፣ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከፌዴራል መስሪያ ቤቶች ያገኟቸው የተለያዩ የምስክር ወረቀቶች፤ የገንዘብ፣ የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማቶች ተጠቃሾች ናቸው።
በፈጠራና በምርምር ስራ ያገኙት እውቅናና ሽልማት አበርትቷቸው፤ በፈጠራ ስራቸው የሚያገኙት በጎ ውጤት ይበልጥ አትግቷቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሚዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር ላይ በመካፈል ሁለት ጊዜ የወርቅ እና አንድ ጊዜ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
የፈጠራ ባለሙያው አቶ አለሙ በተለያዩ የፈጠራና የምርምር ስራዎቻቸው ያገኛቸው ሽልማቶች በግል ተነሳሽነት ለሰበሰብዋቸውና ፈጠራና ምርምር ለሚያለማምዷቸው ከ40 ያላነሱ ተማሪዎቻቸው በማበርከት የምርምር ስራቸውን በትጋት እንዲሰሩ በመርዳት ላይም ይገኛሉ።
የፈጠራ ስራዎቹ አሁን ያሉበት ደረጃ
በተለየዩ ግለሰቦች የተፈጠሩና ብዙ አገልግሎት መስጠት ለለውጥም ምክንያት የሚሆኑ የፈጠራ ስራዎች ተግባራዊ ሳይሆኑና ወደ ምርት ሳይደርሱ የሚቀሩበት አጋጣሚ ብዙ ነው። የፈጠራ ወይም የምርምር ስራ ተግባራዊ ሆኖ ማህበራዊ ችግርን መቅረፍ ካልቻል መፈጠሩ በራሱ ምንም አይደለም። እንደ ሀገር የፈጠራ ስራ ወደህብረተሰቡ መድረስ እንዲችልና የተለየዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት እንዲችል ወደታች ማውረዱ አግባብ እንደሆነ ይታመንበታል። የፈጠራ ባለሙያዎች ክህሎት ማሳያና የአዕምሮ ውጤት የሆኑትን ፈጠራዎች በጥቅም ላይ ለማዋል መስራት ከባለ ድርሻ አካላት ይጠበቃል።
የፈጠራ ባለሙያና መምህር አለሙ የፈጠራ ስራዎች ውጤቶች በብዛት ቢመረቱና ወደስራ ቢገቡ ወይም ተግባር ላይ ቢውሉ ለሀገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንደሚሰጡ መተንበይ አይከብድም። ነገር ግን፤ የፈጠራ ባለሙያው ያለባቸው የገንዘብና የቁሳቁስ ችግር ምንም እንዳይራመዱ አድርጓቸዋል።
የመምህሩ የፈጠራ ስራዎች ተግባራዊነታቸው ተፈትሾ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጡ በተለያዩ ተቋማትና እውቅና ባገኙባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ የታመነባቸው ቢሆንም፤ በተሳተፉባቸው መድረኮች ሁሉ አስተያየት ቢሰጣቸውም ወደ ምርት መግባት የሚችሉበት አጋጣሚ ግን ሊፈጠርላቸው አልቻለም። እናም እርሳቸው ያለባቸው የቁሳቁስና የገንዘብ እጥረት ስራዎቹን ወደምርት እንዳይቀይሯቸውና ለማህበረሰቡ ማድረስ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። በዚህ አጋጣሚ ለፈጠራና ለምርምር ስራ እውቅናና ሽልማት ከመስጠት ባሻገር ለተመራማሪዎች ተስፋ ሊሆን የሚችል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ወሳኙ ጉዳይ መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው።
በፈጠራ ስራው የገጠማቸው ፈተና
ወደ ምርምር ስራ ለመግባት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው እሳቤ የቀዘቀዘ መሆኑ በራሱ ምርምርን እንዳይደፍሩት ያደርጋል። በመሆኑም፤ መምህር አለሙ ከሚያውቋቸውም ይሁን ከማያውቋቸው አንዳንድ የማህበረሰቡ አበላት የሚሰነዘርባቸውን ተስፋ አስቆራጭ አስተያየት መጋፈጣቸው አልቀረም። እነዚያን አሉታዊ አስተያየቶች ተቋቁሞ ከውጤት ለመድረስ ደግሞ ጥንካሬና ፅናት ይጠይቃል። እርሳቸውም፤ ወደ ምርምር ስራ ከገቡ በኋላ በዘርፉ የሚገጥመውን ፈተና ተቋቁመው ዛሬ የደረሱበት መልካም ውጤት ላይ ተገኝተዋል።
የፈጠራ
ስራዎቻቸው አሁን ባሉበት ደረጃ ከመገኘታቸው በፊት የፈጠራና የምርምር ስራ ለማካሄድ የገንዘብና የቁሳቁስ እጥረት፣ ምቹ የሆነ አካባቢያዊ
ሁኔታ አለመኖር፣ የመሳሰሉት ለፈጠራ ስራው የገጠሙት ዋንኛ ችግሮች እንደነበሩ ባለሙያው ይገልፃሉ። ለተመራማሪና ለፈጠራ ባለሙያዎች
ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለስራቸው ስኬት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚያሻው ጉዳይ መሆኑን እየገለፅን፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ
ፈጠራ ውጤቶች ተግባራዊ ሆነው የታሰበውን አገልግሎት ማበርከት እንዲችሉ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል እንላለን።
ተማሪዎች ቁጥር በጊዜና በጥራት ወደ ማዕከል አለመምጣት እንዲሁም የደብተር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ትልቅ ችግር ሆኗል። በአንደ መቶ ሺህ ብር መግዛት የሚቻለው 12 ሺህ ደብተር ብቻ ነው።
እንደ ኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ይሄን የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹን ተግባር የአንድ ሰሞን መፈናቀል አልያም የድርቅ ችግር ሲገጥምና ክረምት እየተጠበቀ የሚደረግ ብቻ ሳይሆን ዘላቂ ባህል አድርጎ ማስቀጠል የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።ተግባሩን በሁሉም ሥራዎች ዘላቂ ባህል አድርጎ የመቀጠል ሀሳብ አለ።አዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በሌሎቹ ከተሞችና የአገሪቱ ክልሎች ይሄው ባህል ዘላቂ በሆነና ችግሮችን መፍታት በሚያስችል መልኩ እንዲሠራበት ይደረጋል።
ትውልድ የሚገነባው ማሕበረሰቡ እስከሆነና የተሻለ ዕውቀት ያለው ተማሪ እስከተገኘ ድረስ ሀሳቡ ትውልድ መገንባት ያስችላል።አሁን ላይም የትምህርት ሚኒስቴርን መነሻ በማድረግ በክልል፣ በዞን በአጠቃላይ እስከ ትምህርት ቤት በተዘረጋው መዋቅር ድጋፍ በማሰባሰብ ተፈናቃይ ተማሪዎችን በመጪው አዲስ ዓመት ትምህርት የማስቀጠሉ ተግባር እየተካሄደ ይገኛል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ትምህርት ቤቶችን እያደሰ ዩኒፎርሞችንና ደብተሮችንም እያሰባሰበ ነው።አማራ ክልል ላይም ማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን በየክልሉ ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስፈልጉ ነገሮችን እየሰጡ ነው።ኦሮሚያ፣ ሶማሌና ሌሎች ክልሎችም ላይ መምህራን ከማሠልጠን አንስቶ የትምህርት ተቋማትን በመጪው አዲስ የትምህርት ዘመን ሳቢና ማራኪ ለማድረግ በትጋት እየተሠራ ነው።
በአማራ ዋግ ኽምራ፣ በትግራይ ሽራሮና ሌሎች አካባቢዎች በዳስ የነበሩ ትምህርት ቤቶችን በአማራና በትግራይ ልማት ማህበራት ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነቡ የማድረግ ሥራው ተጠናቅቋል።በአጠቃላይ በቀሪው የክረምት ጊዚያት ዕድሳቱና ማካካሻ ትምህርት መስጠቱ ሂደት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ መጀመሪያው ቀነ ገደብ ትምህርት ለመጀመር ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።
አዲስ ዘመን ነሀሴ 10/2011
ተገኝ ብሩ