አዲስ አበባ፦ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንት ማክሮን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሬዚዳንት ማክሮን ለይፋዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ መምጣትን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ በመጠናከር ላይ መሆኑን ጠቁመው ፤ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚያደርጉ ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልጸዋል፡፡
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 13 ቀን 2017 ዓ.ም