አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሶማሌላንድ ሕዝብ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄዱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ሚኒስቴሩ የሶማሌላንድ ብሔራዊ ምርጫ ኮሚሽን ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄዱ የሚያስመሰግን ነው ብሏል። ይህ ሂደት የሶማሌ ላንድን የአስተዳደር እና የዲሞክራሲ ሥርዓት ብስለት ያሳያል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የራሷ ምክር ቤት እና መንግሥት፣ ገንዘብ፣ ማዕከላዊ ባንክ፣ ጦር ሠራዊት ያላት ሶማሌላንድ በየአምስት ዓመቱ የሚደረግ እና በአፍሪካ በምሳሌነት የሚጠቀስ ምርጫ ታካሂዳለች። ዘንድሮም ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ምርጫ መካሄዱ ይታወቃል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ኅዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም