አዲስ አበባ፡- የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ወጥና ጠንካራ የሆነ የአፍሪካ የገበያ ሥርዓት ለመገንባት አጋዥ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሴክሬታሪያት 15ኛው የንግድ ሚኒስትሮች ካውንስል ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ ተካሂዷል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የታሰበውን ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወጥ የገበያ ሥርዓት ሊኖር ይገባል። ከዚህ አኳያም ነጻ የንግድ ቀጣናው በየሀገራቱ የተበጣጠሰውን የገበያ ሥርዓት በማስቀረት ወጥ ወደሆነና ጠንካራ የአፍሪካ የገበያ ሥርዓት ለመገንባት ይረዳል። እንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ የአፍሪካን ንግድ ያሳድጋል።
ነጻ የንግድ ቀጣናው የጋራ የሆኑት የአፍሪካን ግቦች ለማሳካት ትልቅ መንገድ እንደሚሆን ጠቁመው፤ ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሰላም ኮርስ እና የወልወል ድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ትናንት ተካሂዷል።
የመርሃ ግብሩ የክብር እንግዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እንደገለጹት፤ ወታደራዊ አመራሮች እና አሰልጣኞች ዘመኑ የሚጠይቀውን ወታደራዊ ብቃት፣ እውቀት እና ጥበብ ለማስተላለፍ የሚካሄደው የሠራዊት የአቅም ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የሀገርን ሉዓላዊነትና ሰላም ለማጽናት ጠንካራ የሠራዊት ግንባታ ይቀጥላል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ፣ ተመራቂ መኮንኖቹ ከነባሮቹ ጋር በመቀናጀት ኃላፊነታቸውንና ተልእኳቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
ተመራቂዎቹ እንደእሳት ተፈትነው የወጡ፣ በሽምቅ ውጊያ የበቁ፣ ውትድርናን ያጣጣሙና የሀገርና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ በላቀ አፈጻጸም የተመረጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መኮንኖቹ ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ የሆኑ እና ከፖለቲካ፣ ከሃይማኖት እና ከብሔር ውግንና የጸዱ መሆናቸው የተረጋገጠ እንደሆነም አመልክተዋል። የማህበራዊ ሳይንስ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ እና ወታደራዊ ጥበብ እና እውቀት ያላቸው መሆኑ የተመሰከረላቸው እንደሆኑ ጠቁመዋል።
ተመራቂዎቹ ጥብቅ ሥነ ምግባርን የተላበሱ መሆናቸውን የጠቆሙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ለአመራርነት የበቁ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ብቃት ያዳበሩ ናቸውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ላይ እንደምትገኝ በመጠቆም፣ አሁን ከተደረሰው በላይ ለመጎናጸፍ ተመራቂዎቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።
እየተመዘገበ ያለውን ልማት ለማደናቀፍ የውስጥ ጸረ ሰላም እና ጽንፈኛ ኃይሎች ውጭ ካሉ የኢትዮጵያን ሰላም መስፈንና ልማትን ከማይሹ ኃይሎች ጋር በማበር የሚንቀሳቀሱ መኖራቸውን ገልጸዋል። እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስበዋል።
ተመራቂ መኮንኖቹ የእነዚህን ጸረ ሰላም እና ጽንፈኛ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመመከት የሀገርን ሰላም ደህንነት ማስጠበቅ እና ጥቅም ማሳካት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችም በተቀነባበረ መልኩ የሚደረግ የሥነ ልቦና ጦርነትን ጭምር በመመከት የኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ እንዲሳካ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።
ተመራቂዎቹ የቀሰሙትን ወታደራዊ ሙያ ከነባር ሠራዊት ተሞክሮ ጋር በመደመር በፈተና ውስጥ ፈጥኖ በመወሰንና ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ብቃት ማዳበር እንደሚኖርባቸው አመልክተዋል።
ተመራቂ መኮንኖቹ በበኩላቸው፤ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ፣ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ እና ወታደራዊ ተልእኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል። የተመራቂ መኮንኖች ተወካይ ምክትል መቶ አለቃ በላቸው ካሳሁን መመረቃቸው እድልም ድልም መሆኑን ተናግረዋል።
ንጹህ የሀገር ፍቅር ስሜት በመላበስ እልህ አስጨራሽ የሆነውን ስልጠና መወጣት መቻላቸውን አመልክተው፤በስልጠናው ወታደራዊ እና ሥነ ልቦና ብቃት መላበስ እንደቻሉም ነው የገለጹት።
በሀገራችን ክብር የማንደራደር መሆናችንን ከአባቶቻችን ተምረናል ያሉት ምክትል መቶ አለቃ በላቸው፤ሰላም ለማሳጣት፣ ልማትን ለማደናቀፍ የሚጥሩ የጽንፈኞችን ቅዥት ለማምከን ቁርጠኞች ነን ብለዋል። የሚሰጣቸውን ሀገራዊና ወታደራዊ ተልእኮ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
ሞገስ ጸጋዬ
አዲስ ዘመን ህዳር 1/ 2017 ዓ.ም