ሩሲያ ኪቭ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በህንጻዎችና በኃይል መሠረተ ልማቶች ጉዳት ደረሰ

ሩሲያ በኪቭ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት በህንጻዎች፣ በመንገዶች እና በኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሷን የዋና ከተማዋ ወታደራዊ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት አስታውቋል።

አስተዳደሩ ይህን ያለው አየር ኃይሉ የድሮን ጥቃት ለመከላከል ጥረት ማድረጉን ከገለጸ በኋላ ነው። የኪቭ ወታደራዊ አስተዳዳሪ ሴርሂ ፖፕኮ በቴሌግራም ገጻቸው እንዳሉት፤ ከሆነ በከፍተኛ ቁጥር ከተለያየ አቅጣጫ ወደ ከተማዋ በቀረቡት ድሮኖች በተፈጸመው ጥቃት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

ፖፕኮ እሳት መነሳቱን እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ወደ ቦታው መላካቸውን የሚገልጸውን ቀደም ብሎ የተፖሰተውን የከተማ አስተዳደሩን መግለጫ አስተካክለዋል።

ፓፕኮ አክለውም ሁሉም ድሮኖች ተመተው ወድቀዋል ብለዋል። ወደ ኪቭ ምን ያህል ድሮኖች እንደተተኮሱ ግልጽ አይደለም።

የተመቱት ድሮን ስብርባሪዎች በሸቭቸንኪቭስኪ እና በሆሎሲቭስኪ መንደሮች ቢያንስ የአምስት ህንጻዎች መግቢያ በሮችን መጉዳታቸውን ፖፕኮ ተናግረዋል። ጦሩ በቴሌግራም ገጹ በእሳት የተጎዱ የህንጻ በሮችን እና የኃይል መስመሮችን የሚያሳዩ ፎቶዎችን ለጥፏል።

ኪቭ እና በዙሪያ የሚገኘው ግዛት በተደጋጋሚ የአየር ጥቃት የሚፈጸምበት እና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደዎሎች የሚያሰሙበት ነው። ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች 34 ወራትን አስቆጥራለች።

ዩክሬን የሩሲያን ኃይሎች ለማዛባት ኩርስክ በተባለው የሩሲያ ግዛት ጥቃት ብትከፍትም፣ የሩሲያ ኃይሎችን ወደፊት ከመገስገሰ ማስቆም አልቻለችም።

ሩሲያ በከፊል የያዘቻቸውን በምስራቅ እና ደቡብ ዩክሬን ያሉ አራት ግዛቶች ጠቅልላ ለመያዝ ዩክሬን ደግሞ የሩሲያ ኃይሎችን ከግዛቷ ለማስወጣት በማለም የሚያደርጉት ውጊያ ቀጥሏል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You